ትንቢተ ኢሳይያስ 32
32
በጽድቅ የሚተዳደር መንግሥት
1በጽድቅ የሚያስተዳድር ንጉሥ የሚነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ ሹማምንቱም በትክክል ይፈርዳሉ። 2ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ። 3ከዚህ በኋላ የሚያዩ ሰዎች ዐይኖች አይጨፈኑም፤ ለመስማት የሚችሉ ሰዎች ጆሮዎችም ያዳምጣሉ። 4ችኲሎች የነበሩ በትዕግሥት የሚያመዛዝኑ ይሆናሉ፤ ተብታባ አንደበት የነበራቸው አንደበተ ርቱዖች ይሆናሉ፤ ንግግራቸውም ግልጥ ይሆናል። 5ከእንግዲህ ወዲህ ሞኞች ጨዋዎች አይባሉም፤ ባለጌዎችም ክብር አይሰጣቸውም። 6ሞኞች የሞኝነትን ንግግር ይናገራሉ፤ አእምሮአቸውም በደልን ያሤራል፤ ስለ እግዚአብሔር ስሕተተኛ ንግግርን በማሠራጨት ክሕደትን ያስፋፋል። የተራቡትን አያጠግቡም። 7የባለጌዎች ሥራ ክፉ ነው፤ ምንም ያኽል የድኾች አቤቱታ ትክክል ቢሆን ውሸት በመናገር ድኾችን ለማጥፋት ክፉ ዕቅድ ያቅዳሉ። 8ጨዋ ሰው ግን የጨዋነት ሥራውን በታማኝነት ያቅዳል፤ በጨዋነቱም ጸንቶ ይኖራል።
በመቀማጠል ለሚኖሩ ሴቶች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
9እናንተ በምቾት የምትኖሩ ሴቶች ተነሥታችሁ ድምፄን ስሙ፤ እናንተ በኑሮአችሁ የምትተማመኑ ሴቶች ንግግሬን አድምጡ። 10እናንተ በኑሮአችሁ የተማመናችሁ ሴቶች ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተስፋ የሚያስቈርጥ ጭንቀት ይደርስባችኋል፤ ከወይንም ሆነ ከሌላው ተክል ሁሉ በቂ ፍሬ አታገኙም። 11እስከ አሁን ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ሆናችሁ በመቀማጠል ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን በፍርሃት ተንቀጥቀጡ! ልብሳችሁን አውልቃችሁ በወገባችሁ ላይ ማቅ ታጠቁ! 12ደስ የሚያሰኘው ለሙ መሬትና የወይን ቦታ ሁሉ ስለ ጠፋ ደረታችሁን እየደቃችሁ አልቅሱ። 13የእሾኽ ቊጥቋጦና ኲርንችት በሕዝቤ ምድር ላይ በቅሎአል፤ ሕዝቦች በደስታ ይኖሩባቸው ስለ ነበሩት ቤቶችና በደስታ ተሞልታ ስለ ነበረችው ስለዚህች ከተማ አልቅሱ! 14ቤተ መንግሥቱ ሳይቀር ወና ይሆናል፤ መናገሻ ከተማውም የተፈታ ምድረ በዳ ይሆናል፤ ቤቶችና የመጠበቂያ ማማዎች ይፈርሳሉ፤ የሜዳ አህዮች መራገጫና የመንጋ መሰማርያ ይሆናሉ።
የደኅንነት ተስፋ
15ነገር ግን እግዚአብሔር መንፈሱን በእኛ ላይ የሚያፈስበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ምድረ በዳው ለም ይሆናል፤ ለሙም መሬት ብዙ ፍሬ ይሰጣል። 16በምድሪቱ ሁሉ ላይ እውነትና ፍትሕ ይሰፍናል። 17የጽድቅ ሥራ ሰላምን ያስገኛል፤ ውጤቱም ዘለዓለማዊ የሕይወቱ ዋስትና ነው። 18የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሐሳብና ከጭንቀት ነጻ ይሆናሉ፤ ቤቶቻቸውም በሰላምና በደኅንነት የተሞሉ ይሆናሉ። 19በበረዶ ዝናብ ደኑ ተጨፍጭፎ ከተማይቱ እስከ መበላሸት ብትደርስም፥ 20በየውሃው ምንጭ አጠገብ ዘራችሁን ስለምትዘሩና ለከብቶቻችሁና ለአህዮቻችሁ በቂ መሰማርያ ስለምታገኙ በበረከት የተሞላችሁ ትሆናላችሁ።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 32: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997