ትንቢተ ኢሳይያስ 36
36
በኢየሩሳሌም ላይ የሰናክሬም ዛቻ
(2ነገ. 18፥13-27፤ 2ዜ.መ. 32፥1-19)
1ሕዝቅያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ላይ አደጋ ጥሎ ያዛቸው። 2ንጉሥ ሕዝቅያስ እጁን እንዲሰጥ ይጠይቀው ዘንድ የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን፥ ከብዙ ሠራዊት ጋር ከላኪሽ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው፤ እርሱም ሄዶ የላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አካባቢ በሚገኘው በልብስ አጣቢው ቦታ አጠገብ ቆመ። 3እርሱንም ለመገናኘት የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የነበረው የሒልቅያ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊ የነበረው ሺብና፥ መዝጋቢ የነበረው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ወጡ። 4የአሦር ባለ ሥልጣን የነበረው ራፋስ ቂስ እንዲህ አላቸው፦ “ለንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ‘እነሆ፥ የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ለመሆኑ ይህን ያኽል ልበ ሙሉ የሆንከው በማን ተማምነህ ነው? 5ከንቱ ቃላት የጦርነት ስልትና ኀይል ይሆናል ብለህ ታስባለህን? ኧረ ለመሆኑ በእኔ ላይ ያመፅከው በማን ተማምነህ ነው? 6ምንአልባት ግብጽ ትረዳኛለች ብለህ ተስፋ አድርገህ ይሆናል፤ ነገር ግን በእርስዋ መታመን በሸምበቆ የመደገፍ ያኽል መሆኑን ዕወቀው፤ ተሰንጥሮ እጅህን ከሚወጋው በቀር ሸምበቆ ለምንም አይጠቅምህም፤ በግብጽ ንጉሥ የሚተማመንም የሚገጥመው ዕድል ይህንኑ የመሰለ ነው።’ ” #ሕዝ. 29፥6-7።
7የአሦራውያን ባለ ሥልጣን ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ ‘እኔ የምታመነው በአምላኬ በእግዚአብሔር ነው’ ትል ይሆናል፤ ታዲያ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በዚህ በአንድ መሠዊያ ብቻ እንዲያመልኩ ፈልገህ የእግዚአብሔርን መሠዊያዎችና የማምለኪያ ስፍራዎች ያፈራረስክ አንተ ሕዝቅያስ አይደለህምን? 8ስለዚህ በአሦር ንጉሠ ነገሥት ስም ሆኜ የሚበጅህን ነገር እነግርሃለሁ፤ ተቀምጠውባቸው ለመጋለብ የሚደፍሩ ሰዎች ካሉህ ሁለት ሺህ ፈረሶችን እሰጥሃለሁ። 9አንተ ከአሦራውያን ባለሥልጣኖች የመጨረሻውን ዝቅተኛ መኰንን እንኳ ለመቋቋም የምትችል አይደለህም፤ ይህም ሆኖ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይልኩልኛል ብለህ ተስፋ ታደርጋለህ። 10እኔስ ብሆን ይህንን አገር ለመውረርና ለማጥፋት የቻልኩት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እንዲያውም በአገሪቱ ላይ አደጋ ጥዬ እንዳጠፋት ያዘዘኝ እግዚአብሔር ራሱ ነው።”
11ከዚህ በኋላ ኤልያቄም፥ ሼብናና ዮአሕ የአሦራውያኑን ባለ ሥልጣን “እኛ ትርጒሙን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጽር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትንገረን” አሉት።
12የአሦራውያን ባለሥልጣንም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታዬ የአሦር ንጉሥ ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ዐይነ ምድራቸውን መብላትና ሽንታቸውን መጠጣት ያለባቸው ሕዝቡም ጭምር ስለ ሆኑ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሕዝቡ ሁሉ እንዲሰሙት ነው።”
13ስለዚህ የአሦር ባለ ሥልጣን ከተቀመጠበት ተነሥቶ ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ እያለ መናገር ጀመረ፦ “የታላቁን የአሦር ንጉሥ ቃል ስሙ! 14በሕዝቅያስ አትታለሉ፤ እርሱ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም፤ 15ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱ ያድነናል፤ ከተማችንም በአሦራውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚያግባባችሁን አትስሙት። 16ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ! የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ወደ እኔ ኑና ከእኔ ጋር ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላ የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጒድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ። 17ይህም የሚሆነው ንጉሡ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር የወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤ 18ስለዚህ ሕዝቅያስ ‘እግዚአብሔር ታደጋችኋል!’ እያለ በማሳሳት አያሞኛችሁ፤ ለመሆኑ ከሌሎች ሕዝቦች አማልክት መካከል አንድ እንኳ ከአሦር ንጉሥ እጅ አገሩን ለማዳን የቻለ ይገኛልን? 19ታዲያ ይህ ከሆነ የሀማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም አማልክትስ የት ደረሱ? ለመሆኑ ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ሊያድን ችሎአልን? 20የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከእኔ እጅ አገራቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”
21ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ። 22ከዚህ በኋላ የቤተ መንግሥት አዛዥ የነበረው የሕልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሐፊው ሼብናና የታሪክ መዝጋቢ የነበረውም የአሳፍ ልጅ ዮአሕ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስም ቀርበው የአሦርያውያን ባለሥልጣን የተናገረውን ሁሉ አስረዱ።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 36: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997