ትንቢተ ኢሳይያስ 57:15-16

ትንቢተ ኢሳይያስ 57:15-16 አማ05

ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው። እኔ ዘወትር ሰውን አልወቅስም፤ ሁልጊዜም አልቈጣም፤ ይህን ባደርግ ኖሮ፥ የፈጠርኳቸው ሰዎች መንፈሳቸው ይዝል ነበር።