የያዕቆብ መልእክት 5
5
ለሀብታሞች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
1አሁን ደግሞ እናንተ ሀብታሞች! ኑ አድምጡ፤ አሠቃቂ መከራ ስለሚመጣባችሁ እየጮኻችሁ አልቅሱ። 2ሀብታችሁ ሁሉ በስብሶአል። ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። 3ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ብዙ ሀብት አከማችታችኋል። #ማቴ. 6፥19። 4ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል። #ዘዳ. 24፥14-15። 5በምቾትና በደስታ በመኖር ልባችሁን ለዕርድ እንደ ተዘጋጀ ከብት አወፍራችኋል። 6ጻድቁን በሐሰት ፈረዳችሁበት፤ ገደላችሁትም፤ እርሱም አይቃወማችሁም።
የጌታን ዳግመኛ መምጣት በትዕግሥት መጠበቅ
7ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ጌታ እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ፤ ገበሬ መሬቱ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን ዝናብ እስከሚያገኝ እየታገሠ ክቡር ዋጋ ያለውን የመሬቱን ፍሬ ይጠባበቃል። 8እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ የጌታ መምጫ ጊዜ ስለ ተቃረበ በተስፋ ጽኑ።
9ወንድሞች ሆይ! በእናንተም ላይ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አትጨቃጨቁ፤ እነሆ ፈራጁ የሚመጣበት ጊዜ ደርሶአል። 10ወንድሞች ሆይ፥ በጌታ ስም የተናገሩት ነቢያት መከራን በትዕግሥት በመቀበል ምሳሌ መሆናቸውን ዕወቁ። 11ደግሞም እነዚያን በትዕግሥት የጸኑትን “የተባረኩ ናቸው” እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንዴት እንደ ታገሠ ሰምታችኋል። ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን መልካም ነገር አይታችኋል፤ በዚህም ጌታ መሐሪና ርኅሩኅ መሆኑን ተመልክታችኋል። #ኢዮብ 1፥21-22፤ 2፥10፤ መዝ. 103፥8።
12ወንድሞቼ ሆይ! ከሁሉም በላይ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በሌላ በምንም ነገር አትማሉ፤ ንግግራችሁ አዎ ከሆነ በእውነት አዎ ይሁን፤ አይደለም ከሆነም በእውነት አይደለም ይሁን፤ እንዲህ ካልሆነ ግን ይፈረድባችኋል። #ማቴ. 5፥34-37።
13ከእናንተ መካከል ችግር የደረሰበት ሰው ቢኖር ይጸልይ፤ ደስ ያለው ሰውም ቢኖር እግዚአብሔርን በማመስገን ይዘምር። 14ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው ቢኖር የቤተ ክርስቲያን ካህናትን (ሽማግሌዎችን) ወደ እርሱ ይጥራ፤ እነርሱም በሽተኛውን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። #ማር. 6፥13። 15እንዲህ ዐይነቱ በእምነት ላይ የተመሠረተ ጸሎት በሽተኛውን ያድነዋል፤ ጌታም ከበሽታው ይፈውሰዋል፤ የሠራው ኃጢአትም ቢኖር ይቅር ይባልለታል። 16ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤ 17ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ በጸለየ ጊዜ ለሦስት ዓመት ተኩል በምድር ላይ ምንም ዝናብ አልዘነበም። #1ነገ. 17፥1፤ 18፥1። 18እንደገና በጸለየም ጊዜ ሰማይ ዝናብ ሰጠ፤ ምድርም እንደገና ፍሬን ሰጠች። #1ነገ. 18፥42-45።
19ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ አንዱ ከእውነት መንገድ ቢወጣና ሌላው ወደ እውነት መንገድ ቢመልሰው 20ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ፥ የኃጢአተኛውን ነፍስ ከሞት እንደሚያድንና የብዙ ኃጢአቱንም ይቅርታ እንደሚያስገኝለት ይወቅ። #ምሳ. 10፥12፤ 1ጴጥ. 4፥8።
Currently Selected:
የያዕቆብ መልእክት 5: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997