መጽሐፈ መሳፍንት 8
8
የጌዴዎን ድልና በቀል
1ከዚህ በኋላ የኤፍሬም ሰዎች ጌዴዎንን “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ እኛን ለምን አልጠራኸንም? በእኛ ላይ ለምን እንዲህ አደረግህ?” ሲሉ በምሬት ወቀሱት።
2እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ካደረግሁት እናንተ ያደረጋችኹት አይበልጥምን? የእኔ ጐሣ በሙሉ ከሠራው ሥራ የኤፍሬም ሰዎች የሠራችሁት ጥቂቱ ሥራ ይበልጣል። የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን? 3እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ገድላችሁ ድልን እንድትቀዳጁ አድርጓችኋል። ታዲያ እኔ ከዚህ ጋር የሚወዳደር ምን ሠራሁ?” እርሱም ይህን ባለ ጊዜ ቊጣቸው በረደ።
4በዚህም ጊዜ ጌዴዎንና የእርሱ ሦስት መቶ ሰዎች ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጥተው ተሻገሩ፤ ድካም ቢሰማቸውም እንኳ አሁንም ጠላትን በማሳደድ ላይ ነበሩ። 5ወደ ሱኮት በደረሱም ጊዜ ጌዴዎን ለከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “እስቲ ለሰዎቼ እንጀራ ስጡልኝ፤ እነርሱ እጅግ ደክመዋል፤ እኔም ዜባሕና ጻልሙናዕ የተባሉትን የምድያማውያን ነገሥታት በማሳደድ ላይ ነኝ።” #መዝ. 83፥11።
6የሱኮት መሪዎች ግን “ለአንተ ሠራዊት ምግብ የምንሰጠው በምን ምክንያት ነው? ዜባሕንና ጻልሙናዕን ገና አልማረክህም” አሉት።
7ጌዴዎንም “ደግ ነው! እግዚአብሔር በዜባሕና በጻልሙናዕ ላይ ድልን በሚያጐናጽፈኝ ጊዜ ከበረሓ በሚገኙ እሾኽና አሜከላ እገርፋችኋለሁ!” አላቸው። 8ጌዴዎን ወደ ጵኑኤልም ሄዶ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ ነገር ግን የጵኑኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ተመሳሳይ መልስ ሰጡት። 9ስለዚህ እነርሱንም “ድልን ተቀዳጅቼ በሰላም እመለሳለሁ፤ በዚያን ጊዜ የከተማ መጠበቂያ ግንባችሁን አፈርሳለሁ” አላቸው። 10ዜባሕና ጻልሙናዕ ከምሥራቅ ሠራዊት ከተረፉት ዐሥራ አምስት ሺህ ወታደሮቻቸው ጋር በቃርቆር ነበሩ፤ አንድ መቶ ኻያ ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ወንዶች አልቀው ነበር። 11ስለዚህ ጌዴዎን በበረሓው መንገድ አድርጎ በኖባሕና በዮግበሃ ምሥራቅ በኩል ወጣና የጠላት ሠራዊት ሳያስበው በመዝናናት ላይ እያለ አደጋ ጣለበት። 12ሁለቱ የምድያማውያን ነገሥታት ዜባሕና ጻልሙናዕ ሸሹ፤ ነገር ግን ጌዴዎን አሳዶ ማረካቸው፤ ሠራዊታቸውንም በሙሉ በድንጋጤ ላይ እንዲወድቁ አደረገ።
13የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በሔሬስ ዳገት በኩል ከጦርነት ተመለሰ፤ 14ከሱኮትም ሰዎች አንዱን ወጣት ይዞ መረመረው፤ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች የነበሩትን የሰባ ሰባት ሰዎችን ስም ዝርዝር ጽፎ ሰጠው። 15ከዚህ በኋላ ጌዴዎን ወደ ሱኮት ሰዎች መጥቶ “ ‘ዜባሕንና ጻልሙናዕን ገና አልማረክህም፤ ታዲያ አሁን በረሀብ ለደከሙት ወታደሮችህ ምግብ የምንሰጠው ለምንድን ነው?’ ብላችሁ አሹፋችሁብኝ ነበር፤ አሁን ግን ዜባሕና ጻልሙናዕ እነሆ በእጄ ይገኛሉ!” አላቸው። 16ከዚህ በኋላ እሾኽና አሜከላ ከበረሓ ወስዶ የሱኮትን መሪዎች ገረፋቸው። 17በጵኑኤል ያለውንም የከተማ መጠበቂያ ግንብ አፈረሰ፤ በከተማይቱ ውስጥ የሚገኙትንም ወንዶች ሁሉ ገደለ።
18ከዚህ በኋላ ጌዴዎን “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች እንዴት ያሉ ነበሩ?” ሲል ዜባሕንና ጻልሙናዕን ጠየቀ።
እነርሱም “አንተን ይመስሉ ነበር፤ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት።
19ጌዴዎንም “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፤ እናንተ እነርሱን ባትገድሉ ኖሮ እኔም ምሕረት አደርግላችሁ እንደ ነበር በእርግጥ እምላለሁ” አላቸው። 20ከዚህ በኋላ የበኲር ልጁን ዬቴርን “በል አሁን ግደላቸው!” ብሎ አዘዘው። ልጁ ግን ሰይፉን ሳይመዝ ቀረ፤ ገና ልጅ ስለ ነበር አመነታ።
21ከዚህ በኋላ ዜባሕና ጻልሙናዕ ጌዴዎንን “በል እንግዲህ አንተው ራስህ ግደለን፤ የሰው ኀይሉ እንደ ሰውነቱ ነው” አሉት፤ ስለዚህ ጌዴዎን እነርሱን ገድሎ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበረውን ጌጣጌጥ በሙሉ ወሰደ።
22ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ጌዴዎንን “አንተ ከምድያማውያን እጅ አድነኸናልና አንተና ከአንተም በኋላ ልጆችህ እንዲሁም የልጅ ልጆችህ ገዢዎቻችን ሁኑ፤” አሉት።
23ጌዴዎንም “እኔም ሆንኩ ልጄ የእናንተ ገዢዎች አንሆንም፤ የእናንተ ገዢ ራሱ እግዚአብሔር ነው” ሲል መለሰላቸው። 24እስማኤላውያን የጆሮ ጉትቻ ማድረግ ልማዳቸው ስለ ነበረ የጌዴዎን ወታደሮች ጉትቻዎቻቸውን ማርከው ነበር፤ ጌዴዎንም “እያንዳንዳችሁ የማረካችሁትን ጉትቻ ስጡኝ” ብሎ ለመናቸው።
25ሕዝቡም “በደስታ እንሰጥሃለን” አሉት። ልብስ አንጥፈውም እያንዳንዱ የወሰደውን የጆሮ ጒትቻ በዚያ ላይ አኖረ። 26ጌዴዎን የተቀበለው የጆሮ ጒትቻ ኻያ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ሆነ፤ ይህም ሌላውን ጌጣጌጥ፥ የአንገት ሐብልና የምድያማውያን ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ፥ እንዲሁም በግመሎቻቸው አንገት ዙሪያ ያለውን ጌጥ ሳይጨምር ነው። 27ጌዴዎንም ከዚያ ወርቅ ጣዖት ሠርቶ በትውልድ ከተማው በዖፍራ አኖረው፤ እስራኤላውያንም በሙሉ ከእግዚአብሔር ተለይተው ያንን ማምለክ ጀመሩ፤ ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ሁሉ መሰናከያ ወጥመድ ሆነ።
28በዚህ ዐይነት ምድያም በእስራኤላውያን ተሸነፈች፤ ዳግመኛም ለእስራኤላውያን የምታሰጋ አልሆነችም፤ ጌዴዎን እስከ ሞተም ድረስ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።
የጌዴዎን ሞት
29የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን ወደ ተወለደበት ቦታ ሄዶ በቤቱ ተቀመጠ። 30ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ 31በሴኬም የምትኖርም ቊባት ነበረችው፤ እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አቤሜሌክ ብሎ ጠራው። 32የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ በአባቱም በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፤ ይህም መቃብር የአቢዔዜር ጐሣ ከተማ በነበረችው በዖፍራ ይገኛል።
33ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት አጓድለው በዓሊም የተባሉትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤ ለባዓልበሪትም ሰገዱ። 34የእስራኤልም ልጆች በዙሪያቸው ከነበሩት ጠላቶቻቸው ሁሉ ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ። 35ለእስራኤል ያደረገውን መልካም ነገር ሁሉ ካለማስታወሳቸው የተነሣ ለጌዴዎን ቤተሰብ ባለ ውለታዎች ሆነው አልተገኙም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997