የዮሐንስ ወንጌል 8
8
በምንዝር የተያዘችው ሴት
1ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። 2በማግስቱም ጠዋት በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ተመልሶ መጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱም ተቀምጦ ያስተምር ነበር። 3የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ስታመነዝር የተያዘች ሴት አመጡና በሕዝቡ መካከል አቆሙአት። 4ኢየሱስንም እንዲህ አሉት፦ “መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተይዛለች፤ 5እንዲህ ዐይነትዋ ሴት በድንጋይ ተወግራ እንድትሞት ሙሴ በሕጋችን አዞናል፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ?” #ዘሌ. 20፥10፤ ዘዳ. 22፥22-24። 6ይህንንም ያሉት በእርሱ ላይ የክስ ምክንያት እንዲያገኙ ሊፈትኑት ፈልገው ነበር፤ ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በመሬት ላይ ይጽፍ ጀመር።
7ደጋግመው በጠየቁት ጊዜ ቀና አለና፥ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት የመጀመሪያውን ድንጋይ በእርስዋ ላይ ይጣል!” አላቸው። 8ከዚህም በኋላ እንደገና ጐንበስ ብሎ በመሬት ላይ ጻፈ። 9እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ። 10ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ቀና ብሎ፥ “አንቺ ሴት ከሳሾችሽ የት አሉ? የፈረደብሽ ማንም የለምን?” አላት።
11እርስዋም “ጌታ ሆይ! ማንም የለም” አለች። ኢየሱስም “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ፤ ዳግመኛ ኃጢአት አትሥሪ” አላት። #8፥11 ብዙ የብራና ጽሑፎችና የጥንት ትርጒሞች 7፥53—8፥11 ያለውን አይጨምሩም፤ አንዳዶቹ ከዮሐ. 21፥24 በኋላ ያስገቡታል፤ ሌሎች ደግሞ ከሉቃ. 21፥38 በኋላ ያስገቡታል፤ አንድ የብራና ጽሑፍ ደግሞ ከዮሐ. 7፥36 በኋላ አስገብቶታል።
ኢየሱስ የዓለም ብርሃን መሆኑ
12እንደገናም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ እኔን የሚከተል ሁሉ የሕይወት ብርሃን ያገኛል፤ በጨለማም አይመላለስም” ሲል ተናገራቸው። #ማቴ. 5፥14፤ ዮሐ. 9፥5።
13ፈሪሳውያን “አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህ፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም” አሉት። #ዮሐ. 5፥31።
14ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ምንም እንኳ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ከየት እንደ መጣሁ፥ ወዴትም እንደምሄድ ስለማውቅ ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም። 15እናንተ በሥጋዊ አስተሳሰብ ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም ላይ አልፈርድም። 16ብፈርድም እንኳ የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነና እኔ ብቻዬን ስለማልፈርድ ፍርዴ እውነት ነው፤ 17የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል። 18ስለዚህ እኔ ስለ ራሴ እመሰክራለሁ፤ የላከኝ አብም ስለ እኔ ይመሰክራል።” 19በዚያን ጊዜ እነርሱ “አባትህ የት አለ?” ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም “እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁ ነበር” ሲል መለሰላቸው።
20ኢየሱስ ይህን ቃል የተናገረው በቤተ መቅደስ በገንዘብ መቀበያ ሣጥን አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነው። ታዲያ፥ ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።
ስለ አለማመን የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
21እንደገናም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም እኔን ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን ከነኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ እንጂ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም።”
22የአይሁድ ባለሥልጣኖችም “ ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ማለቱ ራሱን ሊገድል ይሆን?” ተባባሉ።
23ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም፤ 24የእኔን ማንነት ዐውቃችሁ ባታምኑ ከእነኃጢአታችሁ የምትሞቱ ስለ ሆነ ከነኀጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኳችሁ ስለዚህ ነው።”
25እነርሱም “አንተ ማን ነህ?” አሉት።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ከመጀመሪያ አንሥቼ እንደ ነገርኳችሁ ነኝ፤ 26ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።”
27እነርሱ ግን ስለ አብ እንደ ተናገራቸው አልገባቸውም። 28ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የሰውን ልጅ ከፍ አድርጋችሁ በምትሰቅሉት ጊዜ እኔ እርሱ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም አብ ያስተማረኝን እንደምናገር እንጂ በራሴ ሥልጣን ብቻ ምንም እንደማላደርግ ያን ጊዜ ታስተውላላችሁ። 29የላከኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ዘወትር የማደርገው እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ስለ ሆነ ብቻዬን አልተወኝም።”
30ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።
ከኃጢአት ባርነት ነጻ ስለ መውጣት
31ኢየሱስ በእርሱ ላመኑት አይሁድ እንዲህ አለ፤ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ትሆናላችሁ፤ 32እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።”
33እነርሱ ግን “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከቶ ለማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ፥ አንተ ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ የምትለን እንዴት ነው?” አሉት። #ማቴ. 3፥9፤ ሉቃ. 3፥8።
34ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው፤ 35ባሪያ ሁልጊዜ በቤት ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ሁልጊዜ በቤት ውስጥ ይኖራል። 36ስለዚህ ወልድ ነጻ ካወጣችሁ በእርግጥ ነጻ ትሆናላችሁ። 37የአብርሃም ዘር መሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ቃሌን ስለማትቀበሉ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። 38እኔ ከአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተ ግን ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”
39እነርሱም “አባታችን አብርሃም ነው” ሲሉ መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤ 40እኔ ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። 41እንግዲህ እናንተ የምትሠሩት የአባታችሁን ሥራ ነው።” እነርሱም “እኛ በምንዝር የተወለድን ዲቃላዎች አይደለንም፤ አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው” አሉት።
42ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንማ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የላከኝ እርሱ ነው እንጂ እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም። 43ስለ ምን ንግግሬ አይገባችሁም? ንግግሬን ለመስማት ስለማትችሉ ነው። 44እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል። 45እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም፤ 46ለመሆኑ ከእናንተ ‘ኃጢአተኛ ነህ’ ብሎ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆንኩ ታዲያ፥ ለምን አታምኑኝም? 47ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል የማትሰሙት ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ ነው።”
ኢየሱስ ከአብርሃም በፊት የነበረ መሆኑ
48አይሁድ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ጋኔንም አለብህ፤ ማለታችን ልክ አይደለምን?” አሉት።
49ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ ነገር ግን አባቴን አከብራለሁ፤ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ። 50ይሁን እንጂ እኔ የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የእኔን መከበር የሚፈልግና የሚፈርድ ሌላ አለ። 51እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ፈጽሞ አይሞትም።”
52አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤ 53ለመሆኑ አንተ ከሞተው ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያት ሞተዋል፤ ታዲያ፥ አንተ ራስህን ማንን ታደርጋለህ?” 54ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ዋጋ አይኖረውም እኔን የሚያከብረኝ አባቴ ነው፤ እርሱም ‘እናንተ አምላካችን’ የምትሉት ነው። 55ሆኖም እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ እኔ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንኩ ነበር፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። 56የአባታችሁ የአብርሃም ምኞት የእኔን ቀን አይቶ ለመደሰት ነበር፤ አይቶም ተደሰተ።”
57በዚህ ጊዜ አይሁድ፥ “አንተ ገና ኀምሳ ዓመት እንኳ አልሆነህም፤ ታዲያ እንዴት አብርሃምን አየሁ ትላለህ?” አሉት። 58ኢየሱስም “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ፤ አሁንም፥ ወደፊትም አለሁ።” አላቸው።
59ስለዚህ አይሁድ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረባቸውና ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ።
Currently Selected:
የዮሐንስ ወንጌል 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997