መጽሐፈ ኢያሱ 1
1
የከነዓን ድል መሆን
1የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ፥ የሙሴ ረዳት የነበረውን የነዌን ልጅ ኢያሱን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አነጋገረው፤ 2“እነሆ! አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል፤ እንግዲህ አንተና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እኔ ለእናንተ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ተዘጋጁ። 3ለሙሴ ቃል በገባሁለት መሠረት በእግራችሁ የምትረግጡትን ምድር ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ። 4ድንበራችሁ በስተደቡብ ካለው ምድረ በዳ ተነሥቶ በስተሰሜን እስከሚገኙት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች ድረስ፥ በስተምሥራቅ ከትልቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ፥ በመነሣት የሒታውያንን ምድር ሁሉ ጨምሮ በምዕራብ በኩል እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሆናል። 5አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤ #ዘዳ. 31፥6፤8፤ ዕብ. 13፥5። #ዘዳ. 11፥24-25። 6አይዞህ፤ በርታ፤ እኔ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል የገባሁላቸውን ምድር ለማውረስ ለእነዚህ ሕዝብ መሪ ትሆናለህ። #ዘዳ. 31፥6፤ 7፥23። 7አንተ ብቻ አይዞህ፤ በርታ፤ አገልጋዬ ሙሴ ለሰጠህም ሕግ ሁሉ እውነተኛ ታዛዥ ሁን፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ ማናቸውም ነገር እንዲሳካልህ ከዚህ ሕግ ከቶ ዝንፍ አትበል፤ 8ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል። 9በምትሄድበት ሁሉ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለምሆን አይዞህ! በርታ! አትፍራ! ብዬ አዝሃለሁ።”
ኢያሱ ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠው ትእዛዝ
10ከዚህ በኋላ ኢያሱ የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ 11“ወደ ሰፈር ሄዳችሁ ለሕዝቡ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ፦ ‘እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት የሚሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ከሦስት ቀን በኋላ ዮርዳኖስን ስለምትሻገሩ ስንቃችሁን አዘጋጁ።’ ”
12ኢያሱ የሮቤልንና የጋድን ነገዶች፥ እንዲሁም የምናሴን ነገድ እኩሌታ እንዲህ አላቸው፤ 13“አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ምድር ሰጥቶ ያሳርፋችኋል ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ። 14ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቈዩ፤ የጦር ልብስ ለብሰው ለውጊያ የተዘጋጁ ሰዎቻችሁ ግን ወገኖቻቸውን እስራኤላውያንን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው ዮርዳኖስን ይሻገሩ፤ 15እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ እንደ ሰጠው ለወንድሞቻችሁም ዕረፍትን እስኪሰጥና እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ርስት እስኪያገኙ አብራችሁ ዝመቱ። ከዚያ በኋላ ተመልሳችሁ መጥታችሁ፥ በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ማዶ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሰጣችሁ በገዛ ምድራችሁ ትቀመጣላችሁ።” #ዘኍ. 32፥28-32፤ ዘዳ. 3፥18፤ ኢያሱ 22፥1-6።
16እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “የነገርከንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን፤ 17ለሙሴ ሁልጊዜ ስንታዘዝለት እንደ ነበረ ሁሉ፥ ለአንተም እንታዘዛለን፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፥ ከአንተም ጋር ይሁን! 18የአንተን ሥልጣን የሚቃወምና ትእዛዝህን ሁሉ የማይፈጽም ቢኖር በሞት ይቀጣ፤ ብቻ አንተ በርታ!”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 1: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997