መጽሐፈ ኢያሱ 16
16
ለኤፍሬምና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት ሆኖ የተመደበላቸው ምድር
1ለዮሴፍ ዘሮች የተመደበው የምድሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኢያሪኮ አጠገብ ከዮርዳኖስ ወንዝ ይጀምራል፤ ይኸውም ከኢያሪኮ ምንጮች ምሥራቃዊ ጫፍ በመነሣት ወደ በረሓው ይዘልቃል፤ ከኢያሪኮም ተነሥቶ ወደ ኮረብታማው አገር በመውጣት እስከ ቤትኤል ይደርሳል። 2ከቤትኤልም ተነሥቶ አርካውያን የሚኖሩበትን ዐጣሮትአዳርን በማለፍ ወደ ሎዛ ይዘልቃል። 3ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል።
4የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን እንደሚከተለው ተቀበሉ።
የኤፍሬም ድርሻ
5የኤፍሬም ነገድ የርስት ድርሻ በየወገናቸው ይህ ነው፤ ድንበራቸው ከዐጣሮትአዳር በምሥራቅ በኩል ወደ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣል። 6ከዚያም አልፎ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል፤ ሰሜናዊ ድንበራቸውም ሚክመታት ነው፤ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ታአናት ሺሎ ታጥፎ በምሥራቅ በኩል በማለፍ ወደ ያኖሐ ይሄዳል። 7ከያኖሐም ተነሥቶ ወደ ዐጣሮትና ወደ ናዓራት በመዘቅዘቅ ኢያሪኮ ደርሶ መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ይሆናል። 8ይኸው ድንበር በምዕራብ በኩል ከታፑሐ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርስና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ ለኤፍሬም ነገድ በየወገኑ ርስት ሆኖ የተሰጠው ምድር ይህ ነበር። 9እርሱም በምናሴ ርስት ክልል ውስጥ ያሉትንና ለኤፍሬማውያን የተሰጡትን ከተሞችና መንደሮችንም ይጨምራል፤ 10እነዚህ ኤፍሬማውያን ግን በጌዜር የሚኖሩ ከነዓናውያንን አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህም ከነዓናውያን እስከ አሁን ድረስ በኤፍሬማውያን መካከል ይኖራሉ፤ ሆኖም ለኤፍሬማውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዳሉ። #መሳ. 1፥29።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 16: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997