መጽሐፈ ኢያሱ 19
19
ለስምዖን ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
1ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስቱም ለይሁዳ ነገድ እስከ ተመደበው ምድር ድረስ ገባ ያለ ነበር፤ 2እነርሱም ቤርሳቤህ፥ ሼባዕ፥ ሞላዳ፥ 3ሐጻርሹዓል፥ ባላ፥ ዔጼም፥ 4ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሖርማ፥ 5ጺቅላግ፥ ቤትማርካቦት፥ ሐጻርሱሳ፥ 6ቤትለባኦትና ሻሩሔን የተባሉትን ዐሥራ ሦስት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ትንንሽ ከተሞችንም ይጨምር ነበር።
7ከዚህም ሁሉ ጋር በተጨማሪ ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴርና ዐሻን ተብለው የሚጠሩትን አራት ከተሞች በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ያጠቃልል ነበር፤ 8በደቡብ በኩል እስከምትገኘው እስከ ባዕላትበኤር (ራማ) ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉትን ትንንሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የስምዖን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይዞ ነበር፤ #1ዜ.መ. 4፥28-33። 9የይሁዳ ነገድ ድርሻ በጣም ብዙ ስለ ነበር ለስምዖን ነገድ በይሁዳ ርስት ውስጥ ድርሻ ተሰጠው።
ለዛብሎን ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
10ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየወገናቸው ወጣ፤ እነርሱም የተቀበሉት ርስት እስከ ሣሪድ ይደርሳል፤ 11ድንበሩም ከዚያ በመነሣት ከዳባሼትና በዮቅነዓም ምዕራብ ከሚገኘው ወንዝ እየተዋሰነ በምሥራቅ በኩል እስከ ማርዕላ ይደርሳል። 12ከሣሪድም ባሻገር በምሥራቅ በኩል ወደ ኪስሎት ታቦር አልፎ እስከ ዳብራትና እስከ ያፊዓ ይደርሳል፤ 13እንደገናም በዚሁ በምሥራቅ በኩል ወደ ሪሞን በሚወስደው መንገድ ወደ ኔዓ አቅጣጫ ይታጠፍና ወደ ጋትሔፌርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ 14የሰሜኑም ድንበር መመለሻው የይፍታሕኤል ሸለቆ ሆኖ ወደ ሐናቶን አቅጣጫ ይታጠፋል፤ 15እርሱም ቃጣት፥ ናህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላና ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩትን ዐሥራ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላል፤ 16ስለዚህም እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞች ለዛብሎን ነገድ በየወገናቸው የተሰጡ ርስቶች ናቸው።
ለይሳኮር ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
17አራተኛው ዕጣ ለይሳኮር ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ 18የምድሩም ክልል ኢይዝራኤልን፥ ከሱሎትን፥ ሹኔምን፥ 19ሐፋራይምን፥ ሺኦንን፥ አናሐራትን፥ 20ራቢትን፥ ቂሽዮንን፥ አቤጽን፥ 21ሬሜትን፥ ዔንጋኒምን፥ ዔንሐዳንና ቤትጳጼጽን ይጨምራል፤ 22ድንበሩም መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ፥ ከታቦር፥ ከሻሐጹማና ከቤትሼሜሽ ጋር ይዋሰናል፤ እርሱም ዐሥራ ስድስት ከተሞችንና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ሁሉ ያጠቃልላል፤ 23ስለዚህም እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞችና ለይሳኮር ነገድ በየወገኖቻቸው ርስት ሆኖ በተሰጠው ምድር ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ለአሴር ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
24አምስተኛው ዕጣ ለአሴር ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ 25የምድሩም ክልል ሔልቃትን፥ ሐሊን፥ ቤጤንን፥ አክሻፍን፥ 26ኣላሜሌክን፥ ዓምዓድንና ሚሽአልን ይጨምራል፤ በምዕራብም ከቀርሜሎስና ከሺሖርሊብናት ይዋሰናል፤ 27ወደ ምሥራቅም ይታጠፍና ድንበሩ ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ነዒኤል በሚወስደው መንገድ ከዛብሎንና ከይፍታሕኤል ሸለቆ እየተዋሰነ ወደ ቤትዳጎን ይዘልቃል። በሰሜንም ወደ ካቡል፥ 28ወደ ዔብሮን፥ ረሖብ፥ ሐሞንና ቃና አልፎ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል። 29ድንበሩ እስከ ተመሸገችው እስከ ጢሮስ ከተማ ይደርስና ወደ ራማ ይታጠፋል፤ ከዚያም መመለሻው የሜድትራኒያን ባሕር ሆኖ ወደ ሖሳ ይታጠፋል፤ እርሱም ማሐላብ፥ አክዚብ፥ 30ዑማ፥ አፌቅና ረሖብ ተብለው የሚጠሩትን ኻያ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ይጨምራል፤ 31ስለዚህ እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞች ለአሴር ነገድ በየወገኖቻቸው ርስት ሆነው የተሰጡ ድርሻዎች ናቸው።
ለንፍታሌም ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
32ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ 33ድንበሩም ከሔሌፍ በመነሣት በአዳሚኔቄብና በያሚኒያ በኩል መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ሆኖ እስከ ላቁም ድረስ እስከ ዳዕናኒም ወርካ ይዘልቃል። 34ከዚህ በኋላ ድንበሩ በምዕራብ በኩል ወደ አዝኖትታቦር ይታጠፋል፤ ከዚያም ወደ ሁቆቅ ይሄዳል፤ በደቡብ በኩል ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል አሴርን፥ በስተምሥራቅ ዮርዳኖስ የሚያዋስነው ይሁዳን ነው። 35እንዲሁም የተመሸጉት ከተሞች ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ራቃት፥ የገሊላ ባሕር፥ 36አዳማ፥ ራማ፥ ሐጾር፥ 37ቄዴሽ፥ ኤድረዒ፥ ዔንሐጾር፥ 38ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤትዐናትና ቤትሼሜሽ ተብለው የሚጠሩ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች በዙሪያቸው ታናናሽ ከተሞች ጋር በዚህ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፤ 39ስለዚህ እነዚህ ታላላቅና ታናናሽ ከተሞች ለንፍታሌም ነገድ በየወገናቸው ርስት ሆኖ በተሰጠው ምድር ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ለዳን ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር
40ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየወገኖቻቸው የተሰጠው የርስት ድርሻ ነበር፤ 41የምድሩም ክልል ጾርዓን፥ ኤሽታኦልን፥ ዒርሼሜሽን፥ 42ሻዓልቢምን፥ አያሎንን፥ ይታላን፥ 43ኤሎንን፥ ቲምናን፥ ዔቅሮንን፥ 44ኤልተቄን፥ ጊበቶንን፥ ባዕላትን፥ 45አይሁድን፥ በኔበራቅን፥ ጋትሪሞንን፥ 46ሜያርቆን፥ ራቆንና እንዲሁም በኢዮጴ ዙሪያ ያለውን ግዛት ጭምር ያጠቃልላል። 47የዳንም ሕዝብ ይህን ምድር ለመውረስ የማይቻል ሆኖ ባገኙት ጊዜ ወደ ላዪሽ ሄደው አደጋ በመጣል ከተማይቱን ያዙ፤ ሕዝብዋንም ፈጅተው የራሳቸው ይዞታ አደረጉአት፤ በዚያም ሰፈሩ፤ ላዪሽ ትባል የነበረችውን ከተማ ስሟን ለውጠው በቀድሞ አባታቸው ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤ #መሳ. 18፥27-29። 48ስለዚህ እነዚህ ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች የዳን ልጆች በየወገናቸው ርስት ናቸው።
ለኢያሱ ርስት ሆኖ የተመደበ የመጨረሻው ምድር
49እስራኤላውያን ምድሪቱን ተከፋፍለው በጨረሱ ጊዜ ለነዌ ልጅ ኢያሱ ከምድሪቱ ከፍለው ርስት ሰጡት፤ 50እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት።
51ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ለእስራኤል ሕዝብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። በዚህም ዐይነት ምድሪቱን አከፋፍለው ጨረሱ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 19: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997