መጽሐፈ ኢያሱ 20
20
የመማጠኛ ከተሞች
1ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ኢያሱን፥ እንዲህ አለው፤ #ዘኍ. 35፥6-32፤ ዘዳ. 4፥41-43፤ 19፥1-13። 2ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ “በሙሴ አማካይነት ባዘዝኳችሁ መሠረት የመማጠኛ ከተሞችን ለዩ፤ 3ማንም ሰው ሳያውቅ በድንገት ሰው ቢገድል፥ ወደዚያ በመሄድ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው ይድናል፤ 4እርሱም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ፈጥኖ በመሄድ በከተማይቱ መግቢያ በር ወደሚገኘው ፍርድ ሸንጎ ቀርቦ የሆነውን ነገር ሁሉ ለመሪዎቹ ይገልጣል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ከተማይቱ እንዲገባ ይፈቅዱለታል፤ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡትና በዚያ ይቈያል፤ 5ሊበቀለው የሚፈልገው ሰው ቢያሳድደው፥ ሰውን የገደለው በድንገተኛ አጋጣሚ እንጂ በቂም በቀል ተነሣሥቶ ስላይደለ የከተማይቱ ሰዎች እርሱን አሳልፈው መስጠት አይገባቸውም፤ 6በሸንጎ ቀርቦ ፍርድ እስከሚቀበልና በዘመኑ ያለው ሊቀ ካህናት እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ በዚያች ከተማ ሊቈይ ይችላል፤ ከዚያም በኋላ ሸሽቶ ወደወጣበት ከተማ በመመለስ ወደ ቤቱ ይገባል።”
7ስለዚህም የንፍታሌም ይዞታ በሆነችው በኮረብታማዋ ምድር በምትገኘው በገሊላ፥ ቄዴሽ ተብላ የምትጠራውን፥ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሴኬምንና በኮረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለው ቂርያት አርባቅን መርጠው ለዩ፤ 8በምሥራቅ ዮርዳኖስ፥ ከኢያሪኮም በስተ ምሥራቅ ከፍ ብሎ በሚገኘው በረሓማ አገር፥ በሮቤል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ቤጼርን፥ በጋድ ግዛት ውስጥ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ግዛት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን መርጠው ለዩ፤ 9ለእስራኤል ሕዝብና በመካከላቸውም ለሚኖሩ መጻተኞች መማጸኛ ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ማንም ሰው በድንገተኛ አጋጣሚ ሰው ቢገድል፥ በሸንጎ ሳይፈረድበት እንዳይገደል ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው እጅ ያመልጣል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 20: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997