የሉቃስ ወንጌል 14
14
ኢየሱስ እንደገና አንድ በሽተኛ በሰንበት ቀን መፈወሱ
1በሰንበት ቀን፥ ኢየሱስ ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምሳ ሊበላ ገባ፤ ፈሪሳውያን እርሱ የሚያደርገውን ለማየት ይጠባበቁት ነበር። 2በዚያን ጊዜ በሕመም ምክንያት መላ ሰውነቱ ያበጠበት አንድ ሰው በኢየሱስ ፊት ነበር። 3ኢየሱስም የሕግ መምህራንንና ፈሪሳውያንን “በሰንበት ቀን መፈወስ በሕግ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” ሲል ጠየቃቸው።
4እነርሱ ግን ምንም ሳይመልሱ ዝም አሉ፤ ኢየሱስ የታመመውን ሰው ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው። 5ቀጥሎም ኢየሱስ፦ “ከእናንተ በሰንበት ቀን ልጁ ወይም በሬው በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቅበት ወዲያውኑ የማያወጣው ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። #ማቴ. 12፥11። 6እነርሱ ግን ምንም መልስ መስጠት አልቻሉም።
ስለ ትሕትናና ስለ መስተንግዶ
7ኢየሱስ ለግብዣ የተጠሩ ሰዎች የክብር ስፍራ ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ አየ፤ ስለዚህ ይህን ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ 8“አንድ ሰው ለሠርግ ግብዣ ሲጠራህ በክብር ስፍራ አትቀመጥ፤ ምናልባት ከአንተ የበለጠ ክብር ያለው ሰው ተጠርቶ ይሆናል፤ 9ታዲያ፥ ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘ይህን ስፍራ ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል፤ ያን ጊዜ በታላቅ ኀፍረት ወደ ዝቅተኛው ቦታ ወርደህ ትቀመጣለህ። 10ነገር ግን ለግብዣ ስትጠራ ሄደህ በዝቅተኛ ስፍራ ተቀመጥ፤ በዚያን ጊዜ የጠራህ ሰው ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘ወዳጄ ሆይ! ወደ ከፍተኛው ስፍራ ወጥተህ ተቀመጥ’ ይልሃል፤ ያን ጊዜም በሌሎች ተጋባዦች ሁሉ ፊት ክብር ታገኛለህ። 11ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።” #ማቴ. 23፥12፤ ሉቃ. 18፥14። 12ኢየሱስ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የእራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ብድራቸውን ለመመለስ በተራቸው የሚጋብዙህን ወዳጆችህን፥ ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህን፥ ሀብታሞች ጐረቤቶችህንም አትጥራ፤ 13ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ሽባዎችን፥ ዕውሮችንም ሰዎች ጥራ። 14ይህን ብታደርግ እነርሱ ውለታ ለመክፈል ስለማይችሉ የተባረክህ ትሆናለህ። በጻድቃን ትንሣኤ ጊዜም እግዚአብሔር ይከፍልሃል።”
የትልቁ ግብዣ ምሳሌ
(ማቴ. 22፥1-10)
15በማእድ ተቀምጠው ከነበሩት አንዱ ኢየሱስ የተናገረውን ሰምቶ “በእግዚአብሔር መንግሥት በማእድ መቀመጥ የሚችል እንዴት የታደለ ነው!” አለ።
16ኢየሱስ ግን እንዲህ አለው፤ “አንድ ሰው ትልቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ፥ ብዙ ሰዎችን ጠራ፤ 17የግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ፥ ‘እነሆ፥ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ!’ ብሎ እንዲነግራቸው ጋባዡ አገልጋዩን ወደ ተጠሩት ሰዎች ላከው። 18ነገር ግን እያንዳንዱ ተጋባዥ ከግብዣው ለመቅረት ምክንያት መስጠት ጀመረ፤ አንዱ ‘መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ ስለዚህ መምጣት አልችልምና ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። 19ሌላው ‘አምስት ጥንድ በሬዎች ስለ ገዛሁ እነርሱን መፈተን አለብኝ፤ ስለዚህ መምጣት አልችልምና ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ። 20ሌላው ደግሞ ‘ሚስት አግብቼ ሙሽራ ስለ ሆንኩ ልመጣ አልችልም’ አለ።
21“አገልጋዩም ወደ ቤት ተመልሶ ይህን ሁሉ ለጌታው ነገረው፤ የቤቱም ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂድ፤ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ዕውሮችን፥ አንካሶችንም ጠርተህ አምጣልኝ’ አለው። 22አገልጋዩም ተመልሶ መጣና ጌታውን ‘ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ ያዘዝከኝን ሁሉ ፈጽሜአለሁ፤ ሆኖም ገና ትርፍ ቦታ አለ’ አለው። 23ስለዚህ የቤቱ ጌታ አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ገጠር በሚወስዱት ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂደህ ሌሎች እንዲመጡ አድርግ! 24ከእነዚያ ተጠርተው ከነበሩት ሰዎች አንዱ እንኳ ድግሴን አይቀምስም!’ አለ እላችኋለሁ።”
ኢየሱስን መከተል መሥዋዕትነትን እንደሚጠይቅ
(ማቴ. 10፥37-38)
25ብዙ ሕዝብ ከኢየሱስ ጋር ይሄዱ ነበር፤ እርሱም ወደ እነርሱ መለስ ብሎ እንዲህ አላቸው፦ 26“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም። #ማቴ. 10፥37። 27የራሱን መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ፥ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም። #ማቴ. 10፥38፤ 16፥24፤ ማር. 8፥34፤ ሉቃ. 9፥23።
28“ከእናንተ መካከል አንዱ ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለሥራው ማስፈጸሚያ ምን ያኽል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስቀድሞ የማያስብ ማነው? 29መሠረቱን ጥሎ የሕንጻውን ሥራ መፈጸም ያልቻለ እንደ ሆነ ግን በጅምር የቀረውን ቤት የሚያዩት ሁሉ ይዘባበቱበታል፤ 30‘እነሆ፥ ይህ ሰው ቤት መሥራት ጀምሮ መጨረስ አልቻለም’ እያሉ ያፌዙበታል።
31“ዐሥር ሺህ ወታደር ያለውን አንድ ንጉሥ ኻያ ሺህ ወታደር አስከትቶ ከሚመጣበት ሌላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ቢፈልግ መጀመሪያ ጠላቱን ለመቋቋም የሚችል መሆኑን ለማወቅ ተቀምጦ ይማከራል። 32የማይችል ከሆነ ግን ሊወጋው የሚመጣው ንጉሥ ገና በሩቅ ሳለ ይህ ንጉሥ የሰላም መልእክተኞችን ወደ እርሱ ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል። 33እንዲሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ለእኔ ሲል ያልተወ ማንም ሰው የእኔ ደቀ መዝሙር መሆን አይችልም።”
የማይጠቅም ጨው
(ማቴ. 5፥13፤ ማር. 9፥50)
34ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ጨው መልካም ነው፤ ጨው የጨውነቱን ጣዕም ካጣ ግን በምን ሊጣፍጥ ይችላል? 35እንዲህ ዐይነቱ ጨው ለእርሻ መሬትም ሆነ ለማዳበሪያ የማይጠቅም ስለ ሆነ ወዲያ አውጥተው ይጥሉታል፤ ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!”
Currently Selected:
የሉቃስ ወንጌል 14: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997