የሉቃስ ወንጌል 7
7
ኢየሱስ የመቶ አለቃውን አገልጋይ መፈወሱ
(ማቴ. 8፥5-13)
1ኢየሱስ ይህን ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ሄደ። 2በዚያም አንድ ሮማዊ የመቶ አለቃ ነበረ። እርሱም የሚወድደው አገልጋይ በጠና ታሞበት ለሞት ተቃርቦ ነበር። 3የመቶ አለቃው ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎችን “እባካችሁ ኢየሱስ መጥቶ አገልጋዬን እንዲፈውስልኝ ሄዳችሁ ለምኑልኝ፥” ሲል ላካቸው። 4እነርሱም ወደ ኢየሱስ ሄደው፥ “ይህን ልታደርግለት የሚገባው ሰው ነው፤ 5እርሱ ሕዝባችንን ይወዳል፤ ምኲራብም ሠርቶልናል፤” ሲሉ አጥብቀው ለመኑት።
6ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ የመቶ አለቃው ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወደ ቤቴ ትገባ ዘንድ ያልተገባሁ ነኝና ወደ ቤቴ ለመምጣት አትድከም። 7እኔም ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የበቃሁ ሰው አይደለሁም። ስለዚህ አንተ እዚያው ሆነህ አንድ ቃል ተናገር፤ አገልጋዬም ይድናል። 8እኔ ራሴ ለባለ ሥልጣኖች ታዛዥ ስሆን ከእኔ በታች የማዛቸው ወታደሮች አሉኝ። ስለዚህ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።”
9ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ ተደነቀ፤ ወደሚከተሉትም ሰዎች መለስ ብሎ፥ “በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ከቶ አላገኘሁም እላችኋለሁ፤” አላቸው።
10የተላኩትም ሰዎች ወደ መቶ አለቃው ቤት ተመልሰው በመጡ ጊዜ አገልጋዩን ድኖ አገኙት።
ኢየሱስ የአንዲት መበለትን ልጅ ከሞት ማስነሣቱ
11በማግስቱ ኢየሱስ ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ፤ 12ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር። 13ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና “አይዞሽ፥ አታልቅሺ!” አላት። 14ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደፊት ራመድ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ ቃሬዛውንም የተሸከሙት ሰዎች ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ!” አለ። 15የሞተው ቀና ብሎ ተቀመጠና መነጋገር ጀመረ፤ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለእናትዮዋ፥ “እነሆ፥ ልጅሽ፤” ብሎ ሰጣት፤
16ሁሉንም ፍርሀት ይዞአቸው፥ “ታላቅ ነቢይ ከመካከላችን ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያድን መጥቶአል፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
17የኢየሱስ ዝና በይሁዳ ምድር ሁሉና በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተሰማ።
ከመጥምቁ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ የተላኩ መልእክተኞች
(ማቴ. 11፥2-19)
18የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ እነዚህ ነገሮች ይህን ሁሉ ለእርሱ አወሩለት፤ እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ጠርቶ፥ 19“ያ ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ? ብላችሁ ጠይቁት፤” ሲል ወደ ጌታ ኢየሱስ ላካቸው።
20እነርሱም ወደ ኢየሱስ ሄደው “ ‘ያ ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ብላችሁ ጠይቁት ሲል መጥምቁ ዮሐንስ ወደ አንተ ልኮናል፥” አሉት።
21ኢየሱስ በዚያኑ ሰዓት ሰዎችን ከልዩ ልዩ በሽታና ደዌ ፈወሰ፤ ርኩሳን መናፍስትንም አስወጣ፤ የብዙ ዕውሮችን ዐይን አበራ። 22ኢየሱስ መልእክተኞቹን እንዲህ አላቸው፦ “ተመልሳችሁ ሂዱና ለዮሐንስ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ንገሩት፤ እነሆ፥ ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ቀጥ ብለው ይሄዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም ወንጌል ይሰበካል። #ኢሳ. 35፥5-6፤ 61፥1። 23በእኔ የማይሰናከል የተባረከ ነው።”
24የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ እያለ ይናገር ጀመር፦ “ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን? 25ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱና በድሎት የሚኖሩማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ፤ 26ታዲያስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይ ለማየት ነውን? አዎ፥ እላችኋለሁ፤ እንዲያውም ከነቢይ የሚበልጠውን ለማየት ነው። 27እርሱ ‘እነሆ! እፊት እፊትህ እየሄደ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥’ ተብሎ የተጻፈለት ነው። #ሚል. 3፥1። 28ሴቶች ከወለዱአቸው ሰዎች መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”
29ይህን በሰሙ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቀራጮችም እንኳ ሳይቀሩ በዮሐንስ እጅ ተጠምቀው ስለ ነበር የእግዚአብሔር ሥራ ትክክል መሆኑን ተገነዘቡ። #ማቴ. 21፥32፤ ሉቃ. 3፥12። 30ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ግን በዮሐንስ እጅ አንጠመቅም በማለት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ተቃውመው ነበር።
31ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? ምንስ ይመስላል? 32በአደባባይ ተቀምጠው የሚጫወቱ ልጆችን ይመስላል፤ እነርሱም እርስ በእርሳቸው እየተጠራሩ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ እናንተ ግን አላለቀሳችሁም፥’ የሚሉ ናቸው። 33እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላና የወይን ጠጅም ሳይጠጣ ቢመጣ ‘ጋኔን አለበት፤’ አላችሁት። 34የሰው ልጅ ደግሞ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፥ ‘እነሆ፥ ይህ መብልና መጠጥ የሚወድ ነው፤ የቀራጮችና የኃጢአተኞችም ወዳጅ ነው፥’ አላችሁት። 35የጥበብ ትክክለኛነት በልጆችዋ ይረጋገጣል።”
አንዲት ሴት የኢየሱስን እግር ሽቶ እንደ ቀባች
36ከፈሪሳውያን አንዱ ኢየሱስን ምሳ ጋበዘው፤ ኢየሱስም ወደ ፈሪሳዊው ቤት ገብቶ ምሳ ለመብላት ወደ ማእድ ቀረበ። 37በዚያች ከተማ አንዲት ኃጢአተኛ ሴት ነበረች፤ እርስዋም ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ምሳ መጋበዙን በሰማች ጊዜ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። 38ከኢየሱስ በስተኋላ በእግሮቹ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች እግሮቹን በእንባዋ ታርስና በጠጒርዋ ታብስ ነበር፤ እግሮቹን እየሳመች ሽቶ ትቀባቸው ነበር። #ማቴ. 26፥7፤ ማር. 14፥3፤ ዮሐ. 12፥3። 39ምሳ የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነችና ምን ዐይነት ኃጢአተኛ እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤” ሲል በልቡ አሰበ።
40ኢየሱስም፦ “ስምዖን ሆይ፥ አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ፤” አለው።
እርሱም፦ “መምህር ሆይ! እሺ ንገረኝ!” አለው።
41ኢየሱስም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንዱ አምስት መቶ ዲናር ሌላው ደግሞ ኀምሳ ዲናር ተበደሩ፤ #7፥41 ዲናር፦ የአንድ የቀን ሠራተኛ የአንድ ቀን ደመወዝ ነው። 42ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ቢያቅታቸው አበዳሪው ዕዳቸውን ተወላቸው፤ ታዲያ፥ ከሁለቱ ባለዕዳዎች፥ አበዳሪውን አብልጦ የሚወድ የትኛው ይመስልሃል?” አለው።
43ስምዖንም፦ “ብዙ ዕዳ የቀረለት ሰው አብልጦ የሚወደው ይመስለኛል፤” ሲል መለሰ።
ኢየሱስም “መልስህ ልክ ነው፤” አለው።
44ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው። 45አንተ ስትቀበለኝ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን እኔ ወደ ቤትህ ከገባሁ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም፤ 46አንተ ራሴን ዘይት እንኳ አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሮቼን ሽቶ ቀባች፤ 47ስለዚህ ብዙ ስለ ወደደች ብዙ ኃጢአትዋ ይቅር ተብሎላታል እልሃለሁ፤ ኃጢአቱ በጥቂት ይቅር የሚባልለት ግን የሚወደውም በጥቂቱ ነው።”
48ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሴትዮዋን፥ “ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል፤” አላት።
49ከእርሱ ጋር በማእድ ይበሉ የነበሩትም “ኃጢአትን እንኳ ይቅር የሚል ይህ ማነው?” እያሉ በልባቸው ያስቡ ጀመር።
50ኢየሱስ ግን ሴትዮዋን፥ “እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ!” አላት።
Currently Selected:
የሉቃስ ወንጌል 7: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997