ኦሪት ዘኊልቊ 10
10
ከብር የተሠሩት መለከቶች
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2“ሕዝቡን በአንድነት ለመሰብሰብም ሆነ ከሰፈር ለመቀስቀስ የሚያገለግሉ ሁለት መለከቶችን ከተቀጠቀጠ ብር ሥራ። 3ሁለቱም መለከቶች በሚነፉበት ጊዜ መላው ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በአንተ ዙሪያ ይሰብሰቡ፤ 4አንድ መለከት በሚነፋበት ጊዜ ግን የእስራኤል የነገድ አለቆች ብቻ በአንተ ዙሪያ ይሰብሰቡ። 5በአንድ መለከት ረዘም ላለ ጊዜ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ሲሰማ በስተ ምሥራቅ የሰፈሩት ነገዶች ጒዞ ይጀምሩ። 6ለሁለተኛ ጊዜ የማስጠንቀቂያውን ድምፅ ስታሰማ በስተደቡብ የሰፈሩት ሰፋሪዎች ጒዞ ይጀምሩ፤ በዚህም ዐይነት የማስጠንቀቂያ የመለከት ድምፅ የሚነፋው፥ ሰፈር ለቆ ጒዞ በሚጀመርበት ጊዜ ይሆናል። 7ማኅበሩን በአንድነት እንዲሰበሰቡ ለማድረግ መለከት ትነፋለህ፤ ነገር ግን የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አታሰማም፤ 8መለከቶቹን የሚነፉት ካህናቱ የአሮን ልጆች ይሆናሉ፤ ይህም ለልጅ ልጆቻችሁ የሚተላለፍ ቋሚ ሥርዓት ይሆናል።
9“በአገራችሁ ላይ ጦርነት አንሥቶ አደጋ የጣለባችሁን ጠላት ለመከላከል ስትሄዱ በእኔ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትታወሱ በመለከቶቻችሁ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ንፉ፤ እኔ አምላካችሁም አድናችኋለሁ። 10እንዲሁም በደስታ በዓሎቻችሁ፥ ማለት በወር መጀመሪያና በሌሎችም የተወሰኑ በዓሎቻችሁ፥ በሚቃጠል መሥዋዕትና በአንድነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ትነፋላችሁ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ስለ እናንተ አስታዋሾች ይሆናሉ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
የእስራኤላውያን ከሲና መነሣት
11ሕዝቡ ከግብጽ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ከምስክሩ ድንኳን በላይ የረበበው ደመና ተነሣ፤ 12እስራኤላውያንም ጒዞአቸውን በየወገናቸው ቀጥለው ከሲና ምድረ በዳ ወጡ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ዐረፈ።
13እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ጒዞ ጀመሩ፤ 14በይሁዳ ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙት በዓሚናዳብ ልጅ በነአሶን መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው በመጀመሪያ ተጓዙ፤ 15የይሳኮር ነገድ መሪ የጹዓር ልጅ ናትናኤል ነበር፥ 16የዛብሎን ነገድ መሪ የሔሎን ልጅ ኤሊአብ ነበር።
17ከዚህ በኋላ ድንኳኑ ተነቅሎ፥ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌርሾንና የሜራሪ ጐሣዎች ተጓዙ።
18ቀጥሎም በሮቤል ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙት በሸዴኡር ልጅ በኤሊጹር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤ 19የስምዖን ነገድ መሪ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል ነበር፤ 20የጋድ ነገድ መሪ የደዑኤል ልጅ ኤልያሳፍ ነበር።
21ከዚህ በኋላ የሌዋዊው የቀዓት ጐሣ የሆኑት ሰዎች ንዋያተ ቅድሳትን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ወደሚቀጥለው ሰፈር ከመድረሳቸው በፊት ድንኳኑ እንደገና መተከል ነበረበት። 22ቀጥሎም በኤፍሬም ነገድ ክፍል ዓርማ ሥር የሚገኙት በዓሚሁድ ልጅ በኤሊሻማዕ መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤ 23የምናሴ ነገድ መሪ የጴዳጹር ልጅ ገማልኤል ነበር፤ 24የብንያም ነገድ መሪ የጊድዖኒ ልጅ አቢዳን ነበር።
25በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ። 26የአሴር ነገድ መሪ የዖክራን ልጅ ፋግዒኤል ነበር፤ 27የንፍታሌም ነገድ መሪ የዔናን ልጅ አሒራዕ ነበር። 28እንግዲህ እስራኤላውያን ሰፈር ለቀው በየቡድናቸው የሚጓዙት በዚህ ቅደም ተከተል ነበር።
29ሙሴ የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ፥ ሆባብን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊሰጠን ቃል ወደገባልን ምድር ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበለጽግ ቃል ገብቶልናል፤ ስለዚህ አንተም ከእኛ ጋር አብረህ ሂድ፤ መልካም እናደርግልሃለን” አለው።
30ሖባብም “አይሆንም፤ እኔ ወደ ትውልድ አገሬና ወደ ዘመዶቼ እሄዳለሁ” አለው።
31ሙሴም እንዲህ አለው፤ “እባክህ ከእኛ ተለይተህ አትሂድ፤ በበረሓ ጒዞአችን የት መስፈር እንደሚገባን ታውቃለህ፤ የመንገድ መሪ ትሆንልናለህ፤ 32ከእኛ ጋር አብረህ ብትሄድ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ ለአንተም እናካፍልሃለን።”
የሕዝቡ ጒዞ መጀመር
33ሕዝቡ የተቀደሰው ተራራ ያለበትን የሲናን ምድረ በዳ ትተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት የሚሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ በፊታቸው ተጓዘ። 34ከእያንዳንዱ ሰፈር ሲለቁ የእግዚአብሔር ደመና በቀን ይጋርዳቸው ነበር።
35የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር። #መዝ. 68፥1። 36የቃል ኪዳኑም ታቦት ጒዞውን ባቆመ ጊዜ “በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት ወደ እስራኤላውያን ሕዝብ ተመለስ” ይል ነበር።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 10: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997