ኦሪት ዘኊልቊ 5
5
ያልነጹ ሰዎች
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበትን፥ ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውንና ሬሳ በመንካት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር ያወጡ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ፤ 3በመካከላቸው እኔ የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ፥ እነዚህን ያልነጹ ሰዎች ሁሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ከመካከላችሁ ወጥተው እንዲባረሩ አድርጉ።” 4እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እስራኤላውያን ከሰፈሩ አስወጡአቸው።
ስለ በደል ካሳ
5እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ #ዘሌ. 6፥1-7። 6“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ ከወንዶችም ሆኑ ከሴቶች ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ባለመገኘት በማንም ሰው ላይ በደል ቢፈጽም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው። 7ኃጢአቱን ይናዘዝ፤ ስለ በደል ሊከፈል በሚገባው ዋጋ ላይ ከመቶ ኻያ እጅ በመጨመር ለተበደለው ሰው ካሳ ይስጥ። 8ያ ሰው ቢሞትና ካሳውንም የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን በካህኑ አማካይነት ስጦታው ለእግዚአብሔር ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም ስለ በደል የሚከፈል ዋጋ መሰጠት ያለበት፥ በደል የሠራው ሰው ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትነት ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋር ተጨማሪ በመሆን ነው። 9በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ልዩ ስጦታ ሁሉ ስጦታውን ለሚቀበለው ካህን ድርሻ ይሆናል። 10እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው ልዩ ስጦታ የራሱ የሰውዬው ነው፤ ለካህኑ ከሰጠ ግን የካህኑ ይሆናል።”
በባሎቻቸው ስለሚጠረጠሩ ሴቶች
11ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ 12“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ የአንድ ሰው ሚስት ጠባይዋ ተበላሽቶ በእርሱ ላይ እምነተቢስ ልትሆን ትችላለች፤ 13ባልዋም ሳያውቅ ከሌላ ወንድ ጋር በመተኛት ምንም ሳይታወቅባት ራስዋን አርክሳ ይሆናል፤ እጅ ከፍንጅም ባለመያዝዋ በእርስዋ ላይ መስካሪ አይኖርም፤ 14ራስዋን ባረከሰች፥ ወይም ራስዋን ሳታረክስ በጥርጣሬ በሚስቱ ላይ የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢመጣ፥ 15ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ ስለ እርስዋ የሚፈልገውንም አንድ ኪሎ የገብስ ዱቄት ቊርባን ያምጣ፤ የቅናት ቊርባን ማለት በደልን የሚገልጥ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት።
16“ካህኑ ሴትዮዋን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ያድርግ፤ 17የተቀደሰ ውሃ በሸክላ ዕቃ ይቅዳ፤ ከመገናኛው ድንኳን ወለል ጥቂት ዐፈር ወስዶ በውሃው ውስጥ ይጨምረው። 18ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ። 19ከዚያም ካህኑ እንዲህ ብሎ ያስምላት፦ ከባልሽ ጋር እያለሽ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የተኛ ባይሆን፥ ራስሽንም ባታረክሺ ርግማን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውሃ ነጻ ሁኚ። 20ነገር ግን ከባልሽ ጋር እያለሽ ከሌላ ወንድ ጋር በመተኛት ራስሽን ያረከስሽ ከሆነ፥ 21ካህኑ ሴቲቱን እንዲህ ብሎ የመርገም መሐላ ያስሞላት፦ ‘እግዚአብሔር ጭንሽን እያሰለሰለና ሆድሽን እየነፋ በሕዝብሽ መካከል ለመሓላና ለእርግማን የተገባሽ ያድርግሽ፤ 22ይህም ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ ማሕፀንሽንም ያኰማትረው።’ ሴትዮዋም ‘አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ’ ብላ ትመልሳለች።
23“ከዚህ በኋላ ካህኑ ይህን የእርግማን ቃል ይጽፈዋል፤ ጽሕፈቱንም አጥቦ የመራራ ውሃ ባለበት ዕቃ ውስጥ ይጨምረዋል። 24ሴትዮዋ ብርቱ ሕመም የሚያስከትልባትን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ከማድረጉ በፊት፥ 25ካህኑ የዱቄቱን መባ ከሴትዮዋ እጅ ወስዶ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ የተለየ መሥዋዕት ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቅርበው። 26ከዚህም በኋላ ከእህሉ ቊርባን አንድ እፍኝ ወስዶ የመታሰቢያ ቊርባን ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በመጨረሻም ሴትዮዋ ውሃውን እንድትጠጣው ያድርግ። 27ሴትዮዋ ራስዋን እያረከሰች በባልዋ ላይ ያመነዘረች ከሆነች፥ ውሃው ብርቱ ሥቃይን ያስከትልባታል፤ ይኸውም ሆድዋ ያብጣል፤ ማሕፀንዋም ይኰማተራል፤ ስምዋም በሕዝብዋ መካከል የተረገመ ሆኖ ይቀራል፤ 28ምንም በደል ያልሠራች ንጽሕት ሆና ከተገኘች ግን ምንም ጒዳት አይደርስባትም፤ ልጆችንም መውለድ ትችላለች።
29-30“አንድ ሰው ሚስቱ በእርሱ ላይ እንዳመነዘረችበት ቢጠረጥርና ቅናት ቢያድርበት የሚፈጽመው የሕግ ሥርዓት የሚከተለው ነው፦ ይኸውም ሴትዮዋን በመሠዊያው ፊት ለፊት እንድትቆም ያደርግና ካህኑ ከላይ የተጠቀሰውን ሥርዓት ይፈጽምባታል፤ ወይም የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢያድርና ሚስቱን ቢጠራጠር ወደ መሠዊያው ፊት አምጥቶአት ካህኑ ይህን የሕግ ሥርዓት ይፈጽምባት፤ 31ባልየውም ከበደል ነጻ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ያመነዘረች ሆና ከተገኘች ግን በበደልዋ ምክንያት የሚመጣባትን ፍዳ ትቀበላለች።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኊልቊ 5: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997