ትንቢተ አብድዩ 1
1
በኤዶም ላይ የሚደርስ ቅጣት
1አብድዩ ያየው ራእይ፦ እግዚአብሔር አምላክ ኤዶምን በተመለከተ አብድዩን ልኮአል፤ የሰማነውም የእግዚአብሔር መልእክት፦ “እኔ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ አደጋ እንዲጥሉ በማዘዝ ወደ ሕዝቦች መልእክተኛ ልኬአለሁ!” የሚል ነው።
2እግዚአብሔር ኤዶምን እንዲህ ይላል፦
“እነሆ በአሕዛብ መካከል ደካማ አደርግሃለሁ፤
እጅግም የተናቅህ ትሆናለህ።
3የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤
በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤
የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤
‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ።
4ነገር ግን እንደ ንስር ወደ ላይ ብትበር፥
መኖሪያህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፥
ከዚያ አወርድሃለሁ። ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”
5“ሌቦች ወይም ቀማኞች በሌሊት ቢመጡ፥
የሚበቃቸውን ያኽል ብቻ ይወስዳሉ፤
የወይን ምርትንም የሚሰበስቡ ቃርሚያ ይተዋሉ፤
የአንተ ጠላቶች ግን ፈጽሞ ያጠፉሃል።
6እናንተ የዔሳው ዘሮች ቤታችሁ ተበርብሯል፤
እነሆ ሀብታችሁ በሙሉ ተዘርፎአል።
7የቃል ኪዳን ጓደኞችህ ሁሉ አታለሉህ፤
ከሀገርህም አስወጥተው አሳደዱህ፤
ወዳጆችህ በአንተ ላይ በጠላትነት ተነሡብህ፤
ያንተን እንጀራ የበሉ ወጥመድ ዘረጉብህ፤
ይህን ሁሉ ሲያደርጉብህ ግን አንተ አልደረስክበትም።
8“በዚያን ጊዜ ከኤዶም ጥበበኞችን፥
ከዔሳው ተራራ ዕውቀትን አጠፋለሁ።
9በኤዶም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይገደላሉ፤
የቴማንም ጀገኖች በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።”
ኤዶም የሚቀጣበት ምክንያት
10“የወንድምህን የያዕቆብን ዘሮች በግፍ ስለ ገደልክ፥
ትዋረዳለህ፤ ለዘለዓለምም ትጠፋለህ።
11ጠላቶቻቸው በሮቻቸውን ሰባብረው፥
ሀብታቸውን ሁሉ በዘረፉበት ቀን፥
አንተ በዳር ቆመህ ትመለከት ነበር፤
አንተ እኮ ኢየሩሳሌምን በዕጣ ከተከፋፈሉአት ሰዎች በምንም አትሻልም።
12በይሁዳ አገር በሚኖሩ ወንድሞችህ ላይ በደረሰው መከራ፥
ልትደሰት ባልተገባህም ነበር፤
በጥፋታቸው ቀን ሐሤት ልታደርግና
በጭንቀታቸውም ቀን በእነርሱ ላይ ልትታበይ ባልተገባህም ነበር።
13በችግራቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር ልትገባ ባልተገባህ ነበር፤
በመከራቸውም ቀን በይሁዳ ሕዝብ ጥፋት ለመደሰት መተባበር አይገባህም ነበር፤
በመጥፊያቸው ቀን የእነርሱን ንብረት መዝረፍ ባልተገባህም ነበር።
14የሚሸሹትን ለመግደል በመስቀልኛ መንገድ ላይ
ባላደባህባቸውም ነበር፤
የተረፉትንም በመከራቸው ቀን ለጠላት አሳልፈህ
መስጠት ባልተገባህም ነበር።” #ኢሳ. 34፥5-17፤ 63፥1-6፤ ኤር. 49፥7-22፤ ሕዝ. 25፥12-14፤ 35፥1-15፤ አሞጽ 1፥11-12፤ ሚል. 1፥2-5።
የእግዚአብሔር ፍርድ በአሕዛብ ላይ
15“እኔ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ የምፈርድበት
ቀን ደርሶአል፤
ኤዶም ሆይ! እንደ ሥራህ ዋጋህን ታገኛለህ፤
የምትፈጽመው ክፉ ሥራ በራስህ ላይ ይመለሳል።
16ሕዝቤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ
የመከራ ጽዋ ጠጥተዋል፤
በዙሪያው ያሉት አሕዛብ ሁሉ ከዚህ የከፋ የመከራ ጽዋ ይጠጣሉ፤
የጠጡትም ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።”
የእስራኤል ድል
17“በጽዮን ተራራ ከጥፋት የሚያመልጡ ይገኛሉ፤
የጽዮን ተራራም የተቀደሰች ትሆናለች፤
የያዕቆብም ሕዝብ ተወስዶባቸው የነበረውን ንብረት መልሰው ይወስዳሉ።
18የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥
የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥
የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤
እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና
የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ።
ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
19“ከይሁዳ በስተደቡብ ያሉ ሕዝቦች
የኤዶምን ምድር ይወርሳሉ፤
በምዕራብ ተራራዎች ግርጌ በሚገኘው ቆላማ ስፍራ
የሚኖሩ ሕዝቦች የፍልስጥኤምን ምድር ይይዛሉ፤
የኤፍሬምንና የሰማርያንም ግዛት ይወስዳሉ፤
የብንያም ሰዎችም የገለዓድን ምድር ይወርሳሉ።
20በስደት ላይ የነበሩት የሰሜን እስራኤል ሕዝብ ሖላ ከሚባል አገር
ተመልሰው የከነዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ፤
በሰፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ስደተኞች
በስተ ደቡብ ያሉትን ከተሞች ይይዛሉ።
21የዳኑት የኢየሩሳሌም ሰዎች
በጽዮን ተራራ ላይ ሆነው ኤዶምን ይገዛሉ፤
መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።”
Currently Selected:
ትንቢተ አብድዩ 1: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
ትንቢተ አብድዩ 1
1
በኤዶም ላይ የሚደርስ ቅጣት
1አብድዩ ያየው ራእይ፦ እግዚአብሔር አምላክ ኤዶምን በተመለከተ አብድዩን ልኮአል፤ የሰማነውም የእግዚአብሔር መልእክት፦ “እኔ እግዚአብሔር በኤዶም ላይ አደጋ እንዲጥሉ በማዘዝ ወደ ሕዝቦች መልእክተኛ ልኬአለሁ!” የሚል ነው።
2እግዚአብሔር ኤዶምን እንዲህ ይላል፦
“እነሆ በአሕዛብ መካከል ደካማ አደርግሃለሁ፤
እጅግም የተናቅህ ትሆናለህ።
3የልብህ ትዕቢት አታሎሃል፤
በጠንካራ አለት በተመሸገ ከተማ ውስጥ ትኖራለህ፤
የምታድርበትም ቤት በከፍተኞች ተራራዎች ላይ የተሠራ ነው፤
‘ካለሁበት ስፍራ ማን ሊያወርደኝ ይችላል?’ በማለት ትመካለህ።
4ነገር ግን እንደ ንስር ወደ ላይ ብትበር፥
መኖሪያህንም በከዋክብት መካከል ብታደርግ፥
ከዚያ አወርድሃለሁ። ይህን እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”
5“ሌቦች ወይም ቀማኞች በሌሊት ቢመጡ፥
የሚበቃቸውን ያኽል ብቻ ይወስዳሉ፤
የወይን ምርትንም የሚሰበስቡ ቃርሚያ ይተዋሉ፤
የአንተ ጠላቶች ግን ፈጽሞ ያጠፉሃል።
6እናንተ የዔሳው ዘሮች ቤታችሁ ተበርብሯል፤
እነሆ ሀብታችሁ በሙሉ ተዘርፎአል።
7የቃል ኪዳን ጓደኞችህ ሁሉ አታለሉህ፤
ከሀገርህም አስወጥተው አሳደዱህ፤
ወዳጆችህ በአንተ ላይ በጠላትነት ተነሡብህ፤
ያንተን እንጀራ የበሉ ወጥመድ ዘረጉብህ፤
ይህን ሁሉ ሲያደርጉብህ ግን አንተ አልደረስክበትም።
8“በዚያን ጊዜ ከኤዶም ጥበበኞችን፥
ከዔሳው ተራራ ዕውቀትን አጠፋለሁ።
9በኤዶም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይገደላሉ፤
የቴማንም ጀገኖች በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።”
ኤዶም የሚቀጣበት ምክንያት
10“የወንድምህን የያዕቆብን ዘሮች በግፍ ስለ ገደልክ፥
ትዋረዳለህ፤ ለዘለዓለምም ትጠፋለህ።
11ጠላቶቻቸው በሮቻቸውን ሰባብረው፥
ሀብታቸውን ሁሉ በዘረፉበት ቀን፥
አንተ በዳር ቆመህ ትመለከት ነበር፤
አንተ እኮ ኢየሩሳሌምን በዕጣ ከተከፋፈሉአት ሰዎች በምንም አትሻልም።
12በይሁዳ አገር በሚኖሩ ወንድሞችህ ላይ በደረሰው መከራ፥
ልትደሰት ባልተገባህም ነበር፤
በጥፋታቸው ቀን ሐሤት ልታደርግና
በጭንቀታቸውም ቀን በእነርሱ ላይ ልትታበይ ባልተገባህም ነበር።
13በችግራቸው ቀን ወደ ሕዝቤ በር ልትገባ ባልተገባህ ነበር፤
በመከራቸውም ቀን በይሁዳ ሕዝብ ጥፋት ለመደሰት መተባበር አይገባህም ነበር፤
በመጥፊያቸው ቀን የእነርሱን ንብረት መዝረፍ ባልተገባህም ነበር።
14የሚሸሹትን ለመግደል በመስቀልኛ መንገድ ላይ
ባላደባህባቸውም ነበር፤
የተረፉትንም በመከራቸው ቀን ለጠላት አሳልፈህ
መስጠት ባልተገባህም ነበር።” #ኢሳ. 34፥5-17፤ 63፥1-6፤ ኤር. 49፥7-22፤ ሕዝ. 25፥12-14፤ 35፥1-15፤ አሞጽ 1፥11-12፤ ሚል. 1፥2-5።
የእግዚአብሔር ፍርድ በአሕዛብ ላይ
15“እኔ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ የምፈርድበት
ቀን ደርሶአል፤
ኤዶም ሆይ! እንደ ሥራህ ዋጋህን ታገኛለህ፤
የምትፈጽመው ክፉ ሥራ በራስህ ላይ ይመለሳል።
16ሕዝቤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ
የመከራ ጽዋ ጠጥተዋል፤
በዙሪያው ያሉት አሕዛብ ሁሉ ከዚህ የከፋ የመከራ ጽዋ ይጠጣሉ፤
የጠጡትም ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።”
የእስራኤል ድል
17“በጽዮን ተራራ ከጥፋት የሚያመልጡ ይገኛሉ፤
የጽዮን ተራራም የተቀደሰች ትሆናለች፤
የያዕቆብም ሕዝብ ተወስዶባቸው የነበረውን ንብረት መልሰው ይወስዳሉ።
18የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥
የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥
የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤
እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና
የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ።
ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
19“ከይሁዳ በስተደቡብ ያሉ ሕዝቦች
የኤዶምን ምድር ይወርሳሉ፤
በምዕራብ ተራራዎች ግርጌ በሚገኘው ቆላማ ስፍራ
የሚኖሩ ሕዝቦች የፍልስጥኤምን ምድር ይይዛሉ፤
የኤፍሬምንና የሰማርያንም ግዛት ይወስዳሉ፤
የብንያም ሰዎችም የገለዓድን ምድር ይወርሳሉ።
20በስደት ላይ የነበሩት የሰሜን እስራኤል ሕዝብ ሖላ ከሚባል አገር
ተመልሰው የከነዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ፤
በሰፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ስደተኞች
በስተ ደቡብ ያሉትን ከተሞች ይይዛሉ።
21የዳኑት የኢየሩሳሌም ሰዎች
በጽዮን ተራራ ላይ ሆነው ኤዶምን ይገዛሉ፤
መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።”
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997