መጽሐፈ ምሳሌ 10
10
የልዩ ልዩ የሰሎሞን ብሂሎች
1እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤
ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤
ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
2አግባብ ባልሆነ መንገድ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤
ቀጥተኛነት ግን ከሞት ያድናል።
3እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን እንዲራቡ አያደርግም፤
ክፉዎች ግን የተመኙትን እንዳያገኙ ያደርጋል።
4ስንፍና ያደኸያል፤
ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤
5ብልኅ ሰው መከሩን በወቅቱ ይሰበስባል፤
በመከር ወራት የሚተኛ ግን ውርደት ይደርስበታል።
6ደግ ሰው በረከትን ያገኛል፤
ክፉ ሰው ግን ዐመፀኛነቱን በመልካም አነጋገር ይሸፍናል።
7የጻድቅ ሰው መታሰቢያ ለበረከት ይሆናል
የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።
8በእውነት ጥበበኛ የሆነ ሰው ትእዝዞችን ይቀበላል፤
የሚለፈልፉ ሞኞች ግን ወደ ጥፋት ያመራሉ።
9በሁሉም ነገር ታማኝ ሰው ያለ ስጋት ይኖራል።
የጠማማ ሰው እርምጃ ግን ይጋለጣል።
10በሰው ላይ መጠቃቀስ ችግርን ያመጣል፤
በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል።
11የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፤
የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው።
12ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፤
ፍቅር ግን በደልን ሁሉ አይታ በይቅርታ ታልፋለች። #ያዕ. 5፥20፤ 1ጴጥ. 4፥8።
13በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች በማስተዋል ይናገራሉ።
ሞኞች ግን ቅጣት መቀበል የሚገባቸው ናቸው።
14ጠቢባን በሚቻላቸው ዘዴ ሁሉ ዕውቀትን ያከማቻሉ፤
ሞኞች በሚናገሩበት ጊዜ ግን ጥፋት መምጣቱ አይቀርም።
15ባለጸጋን ሀብቱ እንደ ምሽግ ሆኖ ይጠብቀዋል፤
ድኻውን ግን ድኽነቱ ያጠፋዋል።
16የደግ ሰው መልካም ሥራ ሕይወትን ያስገኝለታል፤
የክፉ ሰው ኃጢአት ግን ቅጣትን ያስከትልበታል።
17ተግሣጽን የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ያመራሉ፤
ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰዎች ግን አደጋ ላይ ይወድቃሉ።
18ጥላቻውን የሚሸፍን ሰው ሐሰተኛ ነው፤
ሐሜትንም የሚያሠራጭ ሰው ሞኝ ነው።
19ከብዙ ንግግር ውስጥ ስሕተት አይጠፋም፤
ስለዚህ አስተዋይ ሰው ብዙ ከመናገር ይቈጠባል።
20የደግ ሰው ንግግር እንደ ነጠረ ብር ነው፤
የክፉ ሰው አሳብ ግን ዋጋቢስ ነው።
21የደግ ሰው ንግግር ብዙ ሰዎችን ይጠቅማል፤
ሞኞች ግን ከማስተዋል ጒድለት የተነሣ ይሞታሉ።
22የእግዚአብሔር በረከት ሐዘንን የማይጨምር ብልጽግና ይሰጣል።
23ስሕተት በማድረግ መደሰት ሞኝነት ነው፤
በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች ደስ የሚላቸው ጥበብን በማግኘት ነው።
24ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤
ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል።
25ዐውሎ ነፋስ በሚነሣበት ጊዜ ክፉዎች ተጠርገው ይወሰዳሉ፤
ደጋግ ሰዎች ግን ዘወትር ጸንተው ይኖራሉ።
26ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ
ሰነፍ ሰውም ለአሠሪው እንደዚሁ ነው።
27እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤
ክፉዎች ግን ያለ ዕድሜያቸው በሞት ይቀጫሉ።
28የደጋግ ሰዎች ተስፋ ወደ ደስታ ይመራቸዋል፤
የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።
29የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን ከለላ ነው፤
ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው።
30ደጋግ ሰዎች ዘወትር ከስፍራቸው አይነቃነቁም፤
ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይኖሩም።
31ደጋግ ሰዎች ጥበብን ይናገራሉ፤
ጠማማ ነገር የምትናገር ምላስ ግን ትቈረጣለች።
32የደጋግ ሰዎች ንግግር ተስማሚ ነው፤
የክፉዎች ንግግር ግን ጠማማ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 10: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ ምሳሌ 10
10
የልዩ ልዩ የሰሎሞን ብሂሎች
1እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤
ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤
ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
2አግባብ ባልሆነ መንገድ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤
ቀጥተኛነት ግን ከሞት ያድናል።
3እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን እንዲራቡ አያደርግም፤
ክፉዎች ግን የተመኙትን እንዳያገኙ ያደርጋል።
4ስንፍና ያደኸያል፤
ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤
5ብልኅ ሰው መከሩን በወቅቱ ይሰበስባል፤
በመከር ወራት የሚተኛ ግን ውርደት ይደርስበታል።
6ደግ ሰው በረከትን ያገኛል፤
ክፉ ሰው ግን ዐመፀኛነቱን በመልካም አነጋገር ይሸፍናል።
7የጻድቅ ሰው መታሰቢያ ለበረከት ይሆናል
የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።
8በእውነት ጥበበኛ የሆነ ሰው ትእዝዞችን ይቀበላል፤
የሚለፈልፉ ሞኞች ግን ወደ ጥፋት ያመራሉ።
9በሁሉም ነገር ታማኝ ሰው ያለ ስጋት ይኖራል።
የጠማማ ሰው እርምጃ ግን ይጋለጣል።
10በሰው ላይ መጠቃቀስ ችግርን ያመጣል፤
በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል።
11የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፤
የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው።
12ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፤
ፍቅር ግን በደልን ሁሉ አይታ በይቅርታ ታልፋለች። #ያዕ. 5፥20፤ 1ጴጥ. 4፥8።
13በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች በማስተዋል ይናገራሉ።
ሞኞች ግን ቅጣት መቀበል የሚገባቸው ናቸው።
14ጠቢባን በሚቻላቸው ዘዴ ሁሉ ዕውቀትን ያከማቻሉ፤
ሞኞች በሚናገሩበት ጊዜ ግን ጥፋት መምጣቱ አይቀርም።
15ባለጸጋን ሀብቱ እንደ ምሽግ ሆኖ ይጠብቀዋል፤
ድኻውን ግን ድኽነቱ ያጠፋዋል።
16የደግ ሰው መልካም ሥራ ሕይወትን ያስገኝለታል፤
የክፉ ሰው ኃጢአት ግን ቅጣትን ያስከትልበታል።
17ተግሣጽን የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ያመራሉ፤
ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰዎች ግን አደጋ ላይ ይወድቃሉ።
18ጥላቻውን የሚሸፍን ሰው ሐሰተኛ ነው፤
ሐሜትንም የሚያሠራጭ ሰው ሞኝ ነው።
19ከብዙ ንግግር ውስጥ ስሕተት አይጠፋም፤
ስለዚህ አስተዋይ ሰው ብዙ ከመናገር ይቈጠባል።
20የደግ ሰው ንግግር እንደ ነጠረ ብር ነው፤
የክፉ ሰው አሳብ ግን ዋጋቢስ ነው።
21የደግ ሰው ንግግር ብዙ ሰዎችን ይጠቅማል፤
ሞኞች ግን ከማስተዋል ጒድለት የተነሣ ይሞታሉ።
22የእግዚአብሔር በረከት ሐዘንን የማይጨምር ብልጽግና ይሰጣል።
23ስሕተት በማድረግ መደሰት ሞኝነት ነው፤
በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች ደስ የሚላቸው ጥበብን በማግኘት ነው።
24ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤
ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል።
25ዐውሎ ነፋስ በሚነሣበት ጊዜ ክፉዎች ተጠርገው ይወሰዳሉ፤
ደጋግ ሰዎች ግን ዘወትር ጸንተው ይኖራሉ።
26ሆምጣጤ ጥርስን፥ ጢስ ዐይንን እንደሚጐዳ
ሰነፍ ሰውም ለአሠሪው እንደዚሁ ነው።
27እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤
ክፉዎች ግን ያለ ዕድሜያቸው በሞት ይቀጫሉ።
28የደጋግ ሰዎች ተስፋ ወደ ደስታ ይመራቸዋል፤
የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።
29የእግዚአብሔር መንገድ ለጻድቃን ከለላ ነው፤
ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው።
30ደጋግ ሰዎች ዘወትር ከስፍራቸው አይነቃነቁም፤
ክፉዎች ግን በምድር ላይ አይኖሩም።
31ደጋግ ሰዎች ጥበብን ይናገራሉ፤
ጠማማ ነገር የምትናገር ምላስ ግን ትቈረጣለች።
32የደጋግ ሰዎች ንግግር ተስማሚ ነው፤
የክፉዎች ንግግር ግን ጠማማ ነው።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997