መጽሐፈ ምሳሌ 12
12
1ዕውቀትን የሚወድ ሰው ከስሕተት መታረምን ይወዳል፤
ተግሣጽን የሚጠላ ግን ጅል ሰው ነው።
2ደግ ሰው ከእግዚአብሔር ሞገስን ያገኛል፤
ክፉ ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች ግን እርሱ ይፈርድባቸዋል።
3ማንም ሰው በክፋት ጸንቶ ሊቆም አይችልም።
የእውነተኞች ሰዎች መሠረት ግን አይናወጥም
4አስተዋይ ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤
ባልዋን የምታሳፍር ሴት ግን አጥንትን እንደሚያደቅ በሽታ ናት።
እንደሚጐዳ ነቀርሳ በሽታ ትሆንበታለች።
5የእውነተኞች ሰዎች ሐሳብ የቀና ነው፤
የክፉዎች ምክር ግን አታላይነት ነው።
6ክፉዎች ሰውን ለማጥፋት በንግግራቸው ያጠምዳሉ፤
የቀጥተኞች ንግግር ግን ያድናቸዋል።
7ዐመፀኞች ወድቀው ደብዛቸው ይጠፋል
የደጋግ ሰዎች ትውልድ ግን ጸንቶ ይኖራል።
8ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፤
አስተሳሰቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
9ሀብታም መስሎ በችግር ከሚኖር ሰው ይልቅ፥
ተራ ሰው መስሎ እየሠራ ኑሮውን የሚያሸንፍ ይሻላል።
10ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤
የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።
11ትጉህ ገበሬ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረዋል፤
በከንቱ ምኞት መጠመድ ግን ሞኝነት ነው።
12የክፉ ሰዎች ምኞት ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ነው፤
ደጋግ ሰዎች ግን እንደ መልካም ተክል መልካም ፍሬን ያፈራሉ።
13ክፉን ሰው የራሱ ክፉ ንግግር ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል።
ደግ ሰው ግን ከመከራ ያመልጣል።
14የምታገኘው በረከት የመልካም ንግግርህና ሥራህ ውጤት ነው፤
በዚህ ዐይነት ተገቢ ዋጋህን ታገኛለህ።
15ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ሁልጊዜ ትክክል የሆኑ ይመስላቸዋል፤
ጠቢባን ግን መልካም ምክርን ይቀበላሉ።
16የሞኝ ቊጣ ወዲያው ይታወቃል፤
ብልኅ ሰው ግን በእርሱ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ ችላ ይላል።
17እውነትን የሚናገር ሁሉ የታመነ ምስክርነትን ይሰጣል፤
ሐሰተኛ ምስክር ግን ሰውን ያታልላል።
18ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደ ሰይፍ ያቈስላል፤
በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል።
19እውነት ግን ጸንታ ትኖራለች።
ሐሰት ዘላቂነት የለውም፤
20ክፋትን በሚያቅዱ ሰዎች ልብ ተንኰል አለ፤
ሰላም የሚገኝበትን ነገር የሚመክሩ ግን ደስታን ያገኛሉ።
21ደጋግ ሰዎች ምንም ክፉ ነገር አይገጥማቸውም፤
ክፉዎች ግን መከራ ይበዛባቸዋል።
የሚያተርፉት ነገር የለም።
22እግዚአብሔር ሐሰተኛ አንደበትን ይጸየፋል፤
በእውነተኞች ሰዎች ግን ይደሰታል።
23አስተዋይ ሰዎች “ዐዋቂዎች ነን” እያሉ አይመጻደቁም፤
ሞኞች ግን “ዐዋቂዎች ነን” በማለት ድንቊርናቸውን ይገልጣሉ።
24በሥራ ትጉህ መሆን ገዢ ያደርጋል፤
ሰነፍ መሆን ግን ተገዢ ያደርጋል።
25በሐሳብ መጨነቅ ሐዘንን ያመጣል፤
በጎ ንግግር ግን ያስደስታል።
26እውነተኛ ሰው ወዳጁን በመምከር ወደ ቅን መንገድ ይመራዋል፤
የዐመፀኞች መንገድ ግን ከእውነት የሚያርቅ ነው።
27ሰነፍ ከሆንክ የምትመኘውን ማግኘት አትችልም፤
በትጋት ከሠራህ ግን ትበለጽጋለህ።
28እውነተኛነት የሕይወት መንገድ ነው፤
ክፋት ግን የሞት መንገድ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 12: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ ምሳሌ 12
12
1ዕውቀትን የሚወድ ሰው ከስሕተት መታረምን ይወዳል፤
ተግሣጽን የሚጠላ ግን ጅል ሰው ነው።
2ደግ ሰው ከእግዚአብሔር ሞገስን ያገኛል፤
ክፉ ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች ግን እርሱ ይፈርድባቸዋል።
3ማንም ሰው በክፋት ጸንቶ ሊቆም አይችልም።
የእውነተኞች ሰዎች መሠረት ግን አይናወጥም
4አስተዋይ ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤
ባልዋን የምታሳፍር ሴት ግን አጥንትን እንደሚያደቅ በሽታ ናት።
እንደሚጐዳ ነቀርሳ በሽታ ትሆንበታለች።
5የእውነተኞች ሰዎች ሐሳብ የቀና ነው፤
የክፉዎች ምክር ግን አታላይነት ነው።
6ክፉዎች ሰውን ለማጥፋት በንግግራቸው ያጠምዳሉ፤
የቀጥተኞች ንግግር ግን ያድናቸዋል።
7ዐመፀኞች ወድቀው ደብዛቸው ይጠፋል
የደጋግ ሰዎች ትውልድ ግን ጸንቶ ይኖራል።
8ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፤
አስተሳሰቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
9ሀብታም መስሎ በችግር ከሚኖር ሰው ይልቅ፥
ተራ ሰው መስሎ እየሠራ ኑሮውን የሚያሸንፍ ይሻላል።
10ደግ ሰው ለቤቱ እንስሳት ይራራል፤
የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።
11ትጉህ ገበሬ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረዋል፤
በከንቱ ምኞት መጠመድ ግን ሞኝነት ነው።
12የክፉ ሰዎች ምኞት ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ነው፤
ደጋግ ሰዎች ግን እንደ መልካም ተክል መልካም ፍሬን ያፈራሉ።
13ክፉን ሰው የራሱ ክፉ ንግግር ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል።
ደግ ሰው ግን ከመከራ ያመልጣል።
14የምታገኘው በረከት የመልካም ንግግርህና ሥራህ ውጤት ነው፤
በዚህ ዐይነት ተገቢ ዋጋህን ታገኛለህ።
15ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ሁልጊዜ ትክክል የሆኑ ይመስላቸዋል፤
ጠቢባን ግን መልካም ምክርን ይቀበላሉ።
16የሞኝ ቊጣ ወዲያው ይታወቃል፤
ብልኅ ሰው ግን በእርሱ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ ችላ ይላል።
17እውነትን የሚናገር ሁሉ የታመነ ምስክርነትን ይሰጣል፤
ሐሰተኛ ምስክር ግን ሰውን ያታልላል።
18ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደ ሰይፍ ያቈስላል፤
በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል።
19እውነት ግን ጸንታ ትኖራለች።
ሐሰት ዘላቂነት የለውም፤
20ክፋትን በሚያቅዱ ሰዎች ልብ ተንኰል አለ፤
ሰላም የሚገኝበትን ነገር የሚመክሩ ግን ደስታን ያገኛሉ።
21ደጋግ ሰዎች ምንም ክፉ ነገር አይገጥማቸውም፤
ክፉዎች ግን መከራ ይበዛባቸዋል።
የሚያተርፉት ነገር የለም።
22እግዚአብሔር ሐሰተኛ አንደበትን ይጸየፋል፤
በእውነተኞች ሰዎች ግን ይደሰታል።
23አስተዋይ ሰዎች “ዐዋቂዎች ነን” እያሉ አይመጻደቁም፤
ሞኞች ግን “ዐዋቂዎች ነን” በማለት ድንቊርናቸውን ይገልጣሉ።
24በሥራ ትጉህ መሆን ገዢ ያደርጋል፤
ሰነፍ መሆን ግን ተገዢ ያደርጋል።
25በሐሳብ መጨነቅ ሐዘንን ያመጣል፤
በጎ ንግግር ግን ያስደስታል።
26እውነተኛ ሰው ወዳጁን በመምከር ወደ ቅን መንገድ ይመራዋል፤
የዐመፀኞች መንገድ ግን ከእውነት የሚያርቅ ነው።
27ሰነፍ ከሆንክ የምትመኘውን ማግኘት አትችልም፤
በትጋት ከሠራህ ግን ትበለጽጋለህ።
28እውነተኛነት የሕይወት መንገድ ነው፤
ክፋት ግን የሞት መንገድ ነው።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997