መጽሐፈ ምሳሌ 2
2
ከጥበብ የሚገኝ በረከት
1ልጄ ሆይ! የማስተምርህን ተቀበል፤ ትእዛዞቼንም በልብህ አኑር። 2የጥበብን ቃል አድምጥ፤ በጥንቃቄም አስተውለው። 3ማስተዋልን ጥራ፤ ለዕውቀትም ድምፅህን ከፍ አድርግ። 4ብር ወይም የተሰወረ ሀብት ለማግኘት ጥረት የምታደርገውን ያኽል ተግተህ ጥበብን ፈልጋት። 5ይህን ሁሉ ብታደርግ እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደ ሆነ ታውቃለህ፤ የአምላክንም ዕውቀት ታገኛለህ። 6ጥበብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም የሚገኙት ከእርሱ ዘንድ ነው። 7እርሱ ለቀጥተኞች መልካም ጥበብን ይሰጣል፤ በተግባራቸው ነቀፋ ለሌለባቸው ጋሻቸው ነው። 8የፍትሕን ሂደት ይከታተላል፤ በታማኝነት የሚያገለግሉትንም ይጠብቃል።
9እኔ የምልህን ሁሉ ብትሰማ፥ ቀጥተኛ፥ ትክክልና ቅን የሆነውን መንገድ ትገነዘባለህ፤ ልታደርገው የሚገባህንም መልካም ነገር ሁሉ ታውቃለህ። 10ጠቢብ ትሆናለህ፤ ዕውቀትም ደስታን ይሰጥሃል። 11አርቆ ማስተዋል ይጠብቅሃል፤ መገንዘብም ከክፉ ነገር ይከላከልልሃል። 12ጥበብ ከክፉ ሰዎች መንገድና ከጠማማ ንግግራቸው ያድንሃል። 13እንደነዚህ ዐይነት ሰዎች በኃጢአት ጨለማ ውስጥ ለመኖር የጽድቅን መንገድ የተዉ ናቸው። 14እነርሱን ደስ የሚያሰኛቸው ቀናውን ነገር ማጣመምና ተንኰል የተሞላበት ክፉ ሥራ መሥራት ነው። 15እነርሱ እምነት የማይጣልባቸውና ጠማሞች ናቸው።
16እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ። 17እንደዚህ ያለችው ሴት ለልጅነት ባልዋ ያላትን ታማኝነት የምታጓድልና በእግዚአብሔር ፊት የገባችውንም ቃል ኪዳን የምትዘነጋ ናት። 18ወደ እርስዋ ቤት ብታመራ ጒዞህ ወደ ሞት ይሆናል፤ ወደ እርስዋ መሄድ ወደ ሙታን ዓለም እንደ መውረድ ነው። 19ወደ እርስዋ የሚሄድ ሁሉ አይመለስም፤ የሕይወትንም ጐዳና ማግኘት አይችልም። 20ስለዚህ የመልካም ሰዎችን ምሳሌነት ልትከተልና የደጋግ ሰዎችንም አካሄድ ልትጠብቅ ይገባሃል። 21በዚህች ምድር መኖር የሚችሉት ልበ ቅኖችና ደጋግ ሰዎች ናቸው። 22ክፉ ሰዎችን ግን እግዚአብሔር ከምድር ላይ በሞት ይነጥቃቸዋል፤ ከዳተኞችንም እንደ አረም ነቃቅሎ ያጠፋቸዋል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997