መጽሐፈ መዝሙር 1
1
ክፍል አንድ
(መዝ. 1—41)
የደግ ሰውና የክፉ ሰው አካሄድ
1በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥
የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥
ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።
2እንዲህ ያለው ሰው፥
በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፤
ቀንና ሌሊትም ያሰላስለዋል።
3እርሱም፦
ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥
ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥
በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤
የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል። #ኤር. 17፥8።
4ክፉዎች ግን እንደዚህ አይደሉም፤
እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።
5ስለዚህ ክፉ ሰዎች
በፍርድ ቀን ከፍርድ አይድኑም፤
ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ አይገኙም።
6ስለዚህ እግዚአብሔር የጻድቃንን አካሄድ ያውቃል፤
የክፉ ሰዎች አካሄድ ግን የሚያመራው ወደ ጥፋት ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 1: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997