መጽሐፈ መዝሙር 103
103
የእግዚአብሔር ፍቅር
1ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም
በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
2ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
ቸርነቱንም አትርሺ!
3ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይላል፤
ሕመሜንም ሁሉ ይፈውሳል።
4ወደ መቃብር ከመውረድ ይጠብቀኛል፤
በፍቅርና በምሕረትም ይባርከኛል።
5በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤
እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።
6እግዚአብሔር በሚሠራው ሁሉ ጻድቅ ነው፤
ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል።
7ዕቅዱን ለሙሴ ገለጠለት፤
የእስራኤል ሕዝቦች አስደናቂ ሥራዎቹን እንዲያዩ አደረገ።
8እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው።
በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው። #ያዕ. 5፥11።
9ዘወትር የሚገሥጽ አይደለም፤
ቊጣውም ለዘለዓለም አይቈይም።
10በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤
በበደላችንም ልክ አልከፈለንም።
11ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል
እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
12ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያኽል
እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ከእኛ ያርቀዋል።
13አባት ለልጆቹ የሚራራላቸውን ያኽል
እግዚአብሔርም የሚፈሩትን ይራራላቸዋል።
14እግዚአብሔር ከምን እንደ ተፈጠርን ያውቃል፤
ዐፈር መሆናችንንም ያስታውሳል።
15የሰው ሕይወት እንደ ሣር ነው፤
እንደሚያድግና እንደሚያብብ እንደ ዱር አበባ ነው።
16የዱር አበባ ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ወዲያው ይጠፋል፤
በዚያ ስፍራ እንደ ነበረ እንኳ አይታወቅም።
17ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ
ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤
ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።
18ይህንንም የሚያደርገው
ቃል ኪዳኑን ቢጠብቁ፥
ትእዛዙንም በታማኝነት ቢፈጽሙ ነው።
19የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው፤
የእርሱም ገዢነት በሁሉም ላይ ነው።
20ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤
እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ
እግዚአብሔርን አመስግኑ።
21አገልጋዮቹ የሆናችሁ፥ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ፥
እናንተ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን አመስግኑ!
22በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 103: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 103
103
የእግዚአብሔር ፍቅር
1ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም
በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
2ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
ቸርነቱንም አትርሺ!
3ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይላል፤
ሕመሜንም ሁሉ ይፈውሳል።
4ወደ መቃብር ከመውረድ ይጠብቀኛል፤
በፍቅርና በምሕረትም ይባርከኛል።
5በጐልማሳነቴ ሕይወቴን በመልካም ነገር ሁሉ ይሞላታል፤
እንደ ንስርም ወጣትነቴን ያድሳል።
6እግዚአብሔር በሚሠራው ሁሉ ጻድቅ ነው፤
ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል።
7ዕቅዱን ለሙሴ ገለጠለት፤
የእስራኤል ሕዝቦች አስደናቂ ሥራዎቹን እንዲያዩ አደረገ።
8እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው።
በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው። #ያዕ. 5፥11።
9ዘወትር የሚገሥጽ አይደለም፤
ቊጣውም ለዘለዓለም አይቈይም።
10በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤
በበደላችንም ልክ አልከፈለንም።
11ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል
እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
12ምሥራቅ ከምዕራብ የሚርቀውን ያኽል
እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ከእኛ ያርቀዋል።
13አባት ለልጆቹ የሚራራላቸውን ያኽል
እግዚአብሔርም የሚፈሩትን ይራራላቸዋል።
14እግዚአብሔር ከምን እንደ ተፈጠርን ያውቃል፤
ዐፈር መሆናችንንም ያስታውሳል።
15የሰው ሕይወት እንደ ሣር ነው፤
እንደሚያድግና እንደሚያብብ እንደ ዱር አበባ ነው።
16የዱር አበባ ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ወዲያው ይጠፋል፤
በዚያ ስፍራ እንደ ነበረ እንኳ አይታወቅም።
17ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ
ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤
ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።
18ይህንንም የሚያደርገው
ቃል ኪዳኑን ቢጠብቁ፥
ትእዛዙንም በታማኝነት ቢፈጽሙ ነው።
19የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው፤
የእርሱም ገዢነት በሁሉም ላይ ነው።
20ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤
እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ
እግዚአብሔርን አመስግኑ።
21አገልጋዮቹ የሆናችሁ፥ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ፥
እናንተ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን አመስግኑ!
22በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997