መጽሐፈ መዝሙር 121
121
እግዚአብሔር ጠባቂአችን መሆኑ
1እኔ ወደ ተራራዎች እመለከታለሁ፤
ታዲያ፥ ርዳታ የማገኘው ከወዴት ነው?
2ርዳታዬ የሚመጣው ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ
ከእግዚአብሔር ነው።
3ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ
እንድትሰናከል አያደርግህም።
4የእስራኤል ጠባቂ ከቶ አያንቀላፋም፤
ፈጽሞም አይተኛም።
5እግዚአብሔር ጠባቂህ ነው፤
በቀኝህም ሆኖ ያጠላልሃል።
6ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት
ጒዳት አያደርሱብህም።
7እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል፤
ሕይወትህንም በሰላም ይጠብቃል።
8ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና
ወደ ቤትህም ስትመለስ
ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 121: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997