መጽሐፈ መዝሙር 123

123
ምሕረት ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ በሰማይ ወደ ሆነው
ወደ አንተ እመለከታለሁ።
2እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ!
አገልጋዮችና ገረዶች የአሳዳሪዎቻቸውን እጅ እንደሚጠባበቁ ሁሉ
እኛም እስክትምረን ድረስ የአንተን ምሕረት
ለማግኘት እንጠባበቃለን።
3እግዚአብሔር ሆይ! ብዙ ስድብ ስለ ደረሰብን ማረን!
እባክህ ማረን!
4በትዕቢተኞች ብዙ መዋረድ፥
በትምክሕተኞችም ብዙ መናቅ ደርሶብናል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ