የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 128

128
ለእግዚአብሔር በመታዘዝ የሚገኝ በረከት
1እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን
በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው።
2ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤
ደስታና ሀብትም ታገኛለህ።
3ሚስትህ በቤትህ እንደ ፍሬያማ የወይን ተክል ትሆናለች፤
ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ለምለም ቅርንጫፎች ይሆናሉ።
4እግዚአብሔርን የሚፈራ
እንደዚህ የተባረከ ይሆናል።
5እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ!
የኢየሩሳሌምን ብልጽግና በሕይወትህ ዘመን ሁሉ
እንድታይ ያድርግህ!
6የልጆችህን ልጆች ለማየት
እንድትበቃ ያድርግህ!
ሰላም ከእስራኤል ጋር ይሁን!

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ