የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 14

14
የሰዎች ክፋት
1ሞኞች በልባቸው፦ “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤
እንደነዚህ ያሉት የተበላሹ ናቸው፤
አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤
ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም።
2አስተዋዮችና አምላክን የሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ ያይ ዘንድ፥
እግዚአብሔር ከሰማይ ወደታች ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3ነገር ግን ሁሉም ባዝነዋል፤
ሁሉም በአንድነት ተበላሽተዋል፤
ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም። #ሮም 3፥10-12።
4“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን?
ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ
ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤
እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
5እግዚአብሔር የሚገኘው ከጻድቃን ጋር ስለ ሆነ
እነርሱ በፍርሃት ይሸበራሉ።
6እናንተ የድኾችን ዕቅድ ብታሰናክሉም እንኳ
እግዚአብሔር ለእነርሱ መጠጊያቸው ይሆናል።
7ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፤
የያዕቆብ ልጆች ይደሰታሉ፤
የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ