መጽሐፈ መዝሙር 24
24
ታላቁ ንጉሥ
1ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥
የእግዚአብሔር ናቸው፤
ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ
የእርሱ ናቸው። #1ቆሮ. 10፥26።
2ምድርን በባሕር ላይ የመሠረተው፥
ከውሃ በላይም ያጸናው እርሱ ነው።
3ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤
በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል።
4ይህን ማድረግ የሚችል፥
እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥
ጣዖትን የማያመልክ፥
ዋሽቶ የማይምል ነው። #ማቴ. 5፥8።
5እንዲህ ዐይነቱ ሰው
ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር
በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል።
6ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡና
የያዕቆብን አምላክ ፊት የሚሹ
እንደዚህ ያሉት ሰዎች ናቸው።
7እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤
የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ
እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
8ይህ የክብር ንጉሥ ማነው?
እርሱ ብርቱና ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።
እርሱ በጦርነት ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።
9እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ
የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ
እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
ይህ የክብር ንጉሥ
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 24: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 24
24
ታላቁ ንጉሥ
1ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥
የእግዚአብሔር ናቸው፤
ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ
የእርሱ ናቸው። #1ቆሮ. 10፥26።
2ምድርን በባሕር ላይ የመሠረተው፥
ከውሃ በላይም ያጸናው እርሱ ነው።
3ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤
በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል።
4ይህን ማድረግ የሚችል፥
እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥
ጣዖትን የማያመልክ፥
ዋሽቶ የማይምል ነው። #ማቴ. 5፥8።
5እንዲህ ዐይነቱ ሰው
ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር
በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል።
6ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡና
የያዕቆብን አምላክ ፊት የሚሹ
እንደዚህ ያሉት ሰዎች ናቸው።
7እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤
የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ
እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
8ይህ የክብር ንጉሥ ማነው?
እርሱ ብርቱና ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።
እርሱ በጦርነት ኀያሉ እግዚአብሔር ነው።
9እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ
የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ
እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ።
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
ይህ የክብር ንጉሥ
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997