መጽሐፈ መዝሙር 28
28
(የዳዊት መዝሙር)
ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1መከታዬ እግዚአብሔር ሆይ!
ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ስማ!
አንተ ካልሰማኸኝ ግን ወደ መቃብር ከሚወርዱት
እንደ አንዱ መሆኔ ነው።
2ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እጄን አንሥቼ
ለእርዳታ በምጮኽበት ጊዜ እባክህ ጸሎቴን ስማኝ።
3የክፋትን ሥራ ከሚሠሩ ክፉ ሰዎች ጋር አትውሰደኝ፤
እነርሱ ከጐረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይነጋገራሉ፤
በልባቸው ግን ተንኰል አለ።
4ስለ ፈጸሙት በደል ተገቢ ዋጋቸውን ክፈላቸው፤
በእጃቸው ስለ ፈጸሙት ክፉ ሥራ ፍረድባቸው፤
ተገቢ ቅጣታቸውንም ስጣቸው። #ራዕ. 22፥12።
5እነርሱ ለእግዚአብሔር አድራጎትና ለእጁ ሥራ
ትኲረት ስለማይሰጡ እርሱ ይሰባብራቸዋል፤
እንደገናም አይገነባቸውም።
6የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማኝ
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
7እግዚአብሔር ኀይሌና ጋሻዬ ነው፤
ስለሚረዳኝና ደስ ስለሚያሰኘኝም
በእርሱ እተማመናለሁ፤
በመዝሙሮቼም አመሰግነዋለሁ።
8እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፤
ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥም የመዳኛ ከለላው ነው።
9አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤
የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤
ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 28: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 28
28
(የዳዊት መዝሙር)
ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1መከታዬ እግዚአብሔር ሆይ!
ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ስማ!
አንተ ካልሰማኸኝ ግን ወደ መቃብር ከሚወርዱት
እንደ አንዱ መሆኔ ነው።
2ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እጄን አንሥቼ
ለእርዳታ በምጮኽበት ጊዜ እባክህ ጸሎቴን ስማኝ።
3የክፋትን ሥራ ከሚሠሩ ክፉ ሰዎች ጋር አትውሰደኝ፤
እነርሱ ከጐረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይነጋገራሉ፤
በልባቸው ግን ተንኰል አለ።
4ስለ ፈጸሙት በደል ተገቢ ዋጋቸውን ክፈላቸው፤
በእጃቸው ስለ ፈጸሙት ክፉ ሥራ ፍረድባቸው፤
ተገቢ ቅጣታቸውንም ስጣቸው። #ራዕ. 22፥12።
5እነርሱ ለእግዚአብሔር አድራጎትና ለእጁ ሥራ
ትኲረት ስለማይሰጡ እርሱ ይሰባብራቸዋል፤
እንደገናም አይገነባቸውም።
6የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማኝ
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
7እግዚአብሔር ኀይሌና ጋሻዬ ነው፤
ስለሚረዳኝና ደስ ስለሚያሰኘኝም
በእርሱ እተማመናለሁ፤
በመዝሙሮቼም አመሰግነዋለሁ።
8እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፤
ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥም የመዳኛ ከለላው ነው።
9አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤
የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤
ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997