መጽሐፈ መዝሙር 36
36
የኃጢአተኞች ክፋት፥ የእግዚአብሔር ቸርነት
1ክፉ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ክፋትን ያስባል፤
እግዚአብሔርን ከቶ አይፈራም፤ አያከብረውምም። #ሮም 3፥18።
2ክፉ ሰው ክፋቱ ስለሚያቈላምጠው
ኃጢአቱን ለማየትም ሆነ ለመጥላት አይፈልግም።
3ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤
መልካም ሥነ ምግባርን ሁሉ መረዳት አቃተው።
4በመኝታውም ላይ ሳለ ተንኰልን ያቅዳል፤
ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል።
ክፉውን ነገር አያስወግድም።
5እግዚአብሔር ሆይ፥
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ እስከ ሰማይ፥
እውነተኛነትህም እስከ ደመና ይደርሳል።
6እግዚአብሔር ሆይ፥
ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤
ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤
ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።
7አምላክ ሆይ!
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!
ሰዎች በአንተ ጥበቃ ሥር ይከለላሉ።
8በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤
አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ።
9አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤
ከአንተም ብርሃን የተነሣ ብርሃን እናያለን፤
10ለሚያውቁህ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ አይቋረጥባቸው፤
አዳኝነትህም ለልበ ቅኖች ይቀጥል።
11የትዕቢተኞች እግር እንዲረግጠኝ፥
የክፉዎች እጅ እንዲአባርረኝ አታድርግ።
12ክፉዎች እንዴት እንደ ወደቁ እይ።
እነሆ ተጥለዋል፤ መነሣትም አይችሉም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 36: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 36
36
የኃጢአተኞች ክፋት፥ የእግዚአብሔር ቸርነት
1ክፉ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ክፋትን ያስባል፤
እግዚአብሔርን ከቶ አይፈራም፤ አያከብረውምም። #ሮም 3፥18።
2ክፉ ሰው ክፋቱ ስለሚያቈላምጠው
ኃጢአቱን ለማየትም ሆነ ለመጥላት አይፈልግም።
3ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤
መልካም ሥነ ምግባርን ሁሉ መረዳት አቃተው።
4በመኝታውም ላይ ሳለ ተንኰልን ያቅዳል፤
ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል።
ክፉውን ነገር አያስወግድም።
5እግዚአብሔር ሆይ፥
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ እስከ ሰማይ፥
እውነተኛነትህም እስከ ደመና ይደርሳል።
6እግዚአብሔር ሆይ፥
ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤
ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤
ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።
7አምላክ ሆይ!
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!
ሰዎች በአንተ ጥበቃ ሥር ይከለላሉ።
8በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤
አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ።
9አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤
ከአንተም ብርሃን የተነሣ ብርሃን እናያለን፤
10ለሚያውቁህ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ አይቋረጥባቸው፤
አዳኝነትህም ለልበ ቅኖች ይቀጥል።
11የትዕቢተኞች እግር እንዲረግጠኝ፥
የክፉዎች እጅ እንዲአባርረኝ አታድርግ።
12ክፉዎች እንዴት እንደ ወደቁ እይ።
እነሆ ተጥለዋል፤ መነሣትም አይችሉም።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997