መጽሐፈ መዝሙር 38
38
በጭንቅ ጊዜ የሚቀርብ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤
በኀይለኛ ቊጣህም አትቅጣኝ።
2በፍላጻዎችህ ወግተኸኛል፤
በብርቱ እጅህም መተኸኛል።
3ከቊጣህ የተነሣ ሥጋዬ ደኅንነት የለውም።
በኃጢአቴም ምክንያት መላ ሰውነቴ ጤንነት የለውም።
4በደሌ በራሴ ላይ ተጭኖአል፤
እርሱም ለመሸከም ከምችለው በላይ ነው።
5በሞኝነት ካደረግሁት ስሕተት የተነሣ
ቊስሌ በስብሶ ይሸታል።
6ጐበጥኩ፤ እጅግም እያጐነበስኩ ሄድኩ፤
ቀኑን ሙሉ በትካዜ አሳለፍኩ።
7ትኲሳት ወገቤን እያቃጠለው ነው፤
ሁለመናዬም ጤና አጣ።
8ደክሜአለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤
ከልቤ ጭንቀት የተነሣም እቃትታለሁ።
9ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤
የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።
10ልቤ በፍጥነት ይመታል፤ ኀይሌም ደክሞአል፤
ዐይኖቼም ብርሃን አጥተዋል።
11ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሕመሜን ተጸየፉ፤
ዘመዶቼም ከእኔ ራቁ፤
12ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤
ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤
በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።
13እኔ ግን ሊሰማ እንደማይችል ደንቆሮ፥
ለመናገር እንደማይችል ድዳ ሰው ነኝ።
14በእውነትም እንደማይሰማና
መልስ ለመስጠት እንደማይችል ሰው ሆኜአለሁ።
15እግዚአብሔር ሆይ! በአንተ እተማመናለሁ፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተም መልስ ትሰጠኛለህ።
16“ጠላቶቼ እኔን በንቀት ዐይን እንዲመለከቱኝ
ወይም እግሬን ሲያዳልጠው ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አታድርግ!” ብዬ እለምናለሁ።
17ፋታ ከማይሰጠው ሕመሜ የተነሣ
ተዝለፍልፌ ልወድቅ ተቃርቤአለሁ።
18በደሌን እናዘዛለሁ፤
ኃጢአቴም አስጨንቆኛል።
19ያለ ምክንያት ጠላት የሆኑብኝ ኀያላን ናቸው፤
በስሕተትም የሚጠሉኝ ብዙዎች ናቸው።
20እኔ ደግ ሥራ በመሥራቴ
በመልካም ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ፤
በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥተዋል።
21እግዚአብሔር ሆይ! አትተወኝ፤
አምላኬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ።
22አዳኜ አምላኬ ሆይ!
ፈጥነህ እርዳኝ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 38: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 38
38
በጭንቅ ጊዜ የሚቀርብ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አትገሥጸኝ፤
በኀይለኛ ቊጣህም አትቅጣኝ።
2በፍላጻዎችህ ወግተኸኛል፤
በብርቱ እጅህም መተኸኛል።
3ከቊጣህ የተነሣ ሥጋዬ ደኅንነት የለውም።
በኃጢአቴም ምክንያት መላ ሰውነቴ ጤንነት የለውም።
4በደሌ በራሴ ላይ ተጭኖአል፤
እርሱም ለመሸከም ከምችለው በላይ ነው።
5በሞኝነት ካደረግሁት ስሕተት የተነሣ
ቊስሌ በስብሶ ይሸታል።
6ጐበጥኩ፤ እጅግም እያጐነበስኩ ሄድኩ፤
ቀኑን ሙሉ በትካዜ አሳለፍኩ።
7ትኲሳት ወገቤን እያቃጠለው ነው፤
ሁለመናዬም ጤና አጣ።
8ደክሜአለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤
ከልቤ ጭንቀት የተነሣም እቃትታለሁ።
9ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤
የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።
10ልቤ በፍጥነት ይመታል፤ ኀይሌም ደክሞአል፤
ዐይኖቼም ብርሃን አጥተዋል።
11ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሕመሜን ተጸየፉ፤
ዘመዶቼም ከእኔ ራቁ፤
12ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤
ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤
በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።
13እኔ ግን ሊሰማ እንደማይችል ደንቆሮ፥
ለመናገር እንደማይችል ድዳ ሰው ነኝ።
14በእውነትም እንደማይሰማና
መልስ ለመስጠት እንደማይችል ሰው ሆኜአለሁ።
15እግዚአብሔር ሆይ! በአንተ እተማመናለሁ፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተም መልስ ትሰጠኛለህ።
16“ጠላቶቼ እኔን በንቀት ዐይን እንዲመለከቱኝ
ወይም እግሬን ሲያዳልጠው ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አታድርግ!” ብዬ እለምናለሁ።
17ፋታ ከማይሰጠው ሕመሜ የተነሣ
ተዝለፍልፌ ልወድቅ ተቃርቤአለሁ።
18በደሌን እናዘዛለሁ፤
ኃጢአቴም አስጨንቆኛል።
19ያለ ምክንያት ጠላት የሆኑብኝ ኀያላን ናቸው፤
በስሕተትም የሚጠሉኝ ብዙዎች ናቸው።
20እኔ ደግ ሥራ በመሥራቴ
በመልካም ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ፤
በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥተዋል።
21እግዚአብሔር ሆይ! አትተወኝ፤
አምላኬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ።
22አዳኜ አምላኬ ሆይ!
ፈጥነህ እርዳኝ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997