መጽሐፈ መዝሙር 45
45
የፍቅር ቅኔ
1ልቤ መልካም ርእስን ያፈልቃል፤
ጽሑፌም የሚያተኲረው በንጉሡ ላይ ነው፤
አንደበቴም እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው።
2አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤
ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።
3በክብርና በግርማ የተሞላህ
ኀያል ንጉሥ ሆይ፥
ሰይፍህን ታጠቅ።
4ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ
ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ፤
ኀይልህም ታላላቅ ድሎችን ያስገኛል።
5ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤
የጠላቶችህንም ልብ ይወጋሉ፤
መንግሥታትም ተሸንፈው በእግርህ ሥር ይወድቃሉ።
6አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የጸና ነው።
በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው።
7አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤
ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤
ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ
የደስታን ዘይት ቀባህ። #ዕብ. 1፥8-9።
8ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ
በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤
በዝሆን ጥርስ በተጌጠው
ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
9በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥
የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤
ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ
ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ
ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።
10አንቺ ልጄ ሆይ!
የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤
ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
11በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤
ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው።
12የጢሮስ ሰዎች ስጦታ ያመጡልሻል፤
ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።
13በቤተ መንግሥት የተቀመጠችው ልዕልት አጊጣለች
ልብስዋም በወርቅ አሸብርቆአል።
14ጌጠኛ ልብስዋንም ተጐናጽፋ
ወደ ንጉሡ ትቀርባለች፤
ሚዜዎችዋ የሆኑ ልጃገረዶችም ያጅቡአታል፤
15በደስታና በሐሤትም
አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ።
16ንጉሥ ሆይ!
በቀድሞ አባቶችህ ተተክተው የሚነግሡ
ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤
አንተም በምድር ሁሉ ላይ ልዑላን አድርገህ ትሾማቸዋለህ።
17እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤
ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 45: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 45
45
የፍቅር ቅኔ
1ልቤ መልካም ርእስን ያፈልቃል፤
ጽሑፌም የሚያተኲረው በንጉሡ ላይ ነው፤
አንደበቴም እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው።
2አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤
ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።
3በክብርና በግርማ የተሞላህ
ኀያል ንጉሥ ሆይ፥
ሰይፍህን ታጠቅ።
4ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ
ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ፤
ኀይልህም ታላላቅ ድሎችን ያስገኛል።
5ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፤
የጠላቶችህንም ልብ ይወጋሉ፤
መንግሥታትም ተሸንፈው በእግርህ ሥር ይወድቃሉ።
6አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የጸና ነው።
በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው።
7አንተ መልካሙን ነገር ትወዳለህ፤
ክፉውን ነገር ትጠላለህ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤
ከሌሎች ነገሥታትም ይበልጥ
የደስታን ዘይት ቀባህ። #ዕብ. 1፥8-9።
8ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ
በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤
በዝሆን ጥርስ በተጌጠው
ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል።
9በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥
የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤
ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ
ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ
ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።
10አንቺ ልጄ ሆይ!
የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤
ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ።
11በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤
ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው።
12የጢሮስ ሰዎች ስጦታ ያመጡልሻል፤
ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።
13በቤተ መንግሥት የተቀመጠችው ልዕልት አጊጣለች
ልብስዋም በወርቅ አሸብርቆአል።
14ጌጠኛ ልብስዋንም ተጐናጽፋ
ወደ ንጉሡ ትቀርባለች፤
ሚዜዎችዋ የሆኑ ልጃገረዶችም ያጅቡአታል፤
15በደስታና በሐሤትም
አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ።
16ንጉሥ ሆይ!
በቀድሞ አባቶችህ ተተክተው የሚነግሡ
ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤
አንተም በምድር ሁሉ ላይ ልዑላን አድርገህ ትሾማቸዋለህ።
17እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤
ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997