የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 67

67
የምስጋና መዝሙር
1እግዚአብሔር ይማረን፥ ይባርከንም፤
የፊቱ ብርሃን በላያችን ይብራ።
2ዓለም በሙሉ የአንተን መንገድ፥
ሕዝቦችም የአንተን አዳኝነት ይወቁ።
3አምላክ ሆይ፥ ሕዝቦች ያመስግኑህ፤
ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
4ለሕዝቦች በቅንነት ስለምትፈርድና
የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ስለምትመራ፤
መንግሥታት ደስ ይበላቸው፤
በሐሤትም እልል ይበሉ።
5አምላክ ሆይ! ሕዝቦች ያመስግኑህ፤
ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
6በዚያን ጊዜ ምድር ፍሬ ትሰጣለች፤
እግዚአብሔር አምላካችን ይባርከናል።
7እግዚአብሔር ስለሚባርከንም
በምድር ዳርቻ ያሉ ሁሉ ይፈሩታል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ