መጽሐፈ መዝሙር 68
68
የድል መዝሙር
1እግዚአብሔር ይነሣ!
ጠላቶቹም ይበተኑ!
የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ!
2ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ አብንናቸው፤
ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚያልቅ ክፉዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ!
3ደጋግ ሰዎች ግን ደስ ይበላቸው፤
በፊቱም ሐሴት ያድርጉ፤
በደስታም ይፈንጥዙ!
4ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤
በደመናዎች ላይ ለሚጓዘው መንገድ አዘጋጁ፤
ስሙ እግዚአብሔር ነው፤
በፊቱ ደስ ይበላችሁ! #68፥4 በደመናዎች ላይ፦ ወይም “በምድረ በዳ”።
5በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ
አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤
ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው።
6መጠጊያ ላጡ ብቸኞች የሚኖሩበትን ቤት ይሰጣቸዋል፤
እስረኞች ነጻ ወጥተው በብልጽግና እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤
ዐመፀኞች ግን በሚያቃጥል በረሓ ይኖራሉ።
7አምላክ ሆይ! ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፥
በበረሓም አብረሃቸው በተጓዝህ ጊዜ፥
8የሲና አምላክ በመምጣቱ፥
የእስራኤል አምላክ በመገለጡ፥
ምድር ተናወጠች፤ ሰማይም ዝናብን አዘነበ። #ዘፀ. 19፥18።
9ብዙ ዝናብ እንዲዘንብ አደረግህ፤
ያረጀውን መሬትህን አደስህ፤
10ሕዝቦችህም መኖሪያቸውን በዚያ አደረጉ፤
በቸርነትህም ለድኾች የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አዘጋጀህላቸው።
11እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጠ፤
ብዙ ሴቶችም ዜናውን አሠራጩ፤
12እንዲህም አሉ፦
“ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ወደ ኋላቸው ሸሹ!
በቤት የቀሩ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ፤
13በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት
ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ
አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው
ማዕድናዊ ርግቦችን አገኙ፤
14ሁሉን የሚችል አምላክ ነገሥታትን በበታተነ ጊዜ
በረዶ በጻልሞን ተራራዎች ላይ እንዲዘንብ አደረገ።
15“የባሳን ተራራ ብዙ ወጣ ገባ የሆነና
ግርማ ያለው ተራራ ነው።
16እናንተ ባለ ብዙ ወጣ ገብ ተራራዎች፥
እግዚአብሔር ሊኖርበት ወደ መረጠው ተራራ
በቅናት የምትመለከቱት ለምንድን ነው?
በዚያ እኮ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖርበታል።
17“እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቈጠሩት
ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ይመጣል።
18እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥
ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ
ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤
ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ። #ኤፌ. 4፥8።
19“ሸክማችንን በየቀኑ የሚያቀልልንና እኛን የሚያድን
እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን።
20አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤
ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን ጌታ እግዚአብሔር ነው።
21በእርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ ይቀጠቅጣል፤
በጠጒር የተሸፈነ አናታቸውን ይሰባብራል።”
22ጌታ እንዲህ ይላል፤
“ጠላቶችህን ከባሳንና ከጥልቅ ባሕር መልሼ አመጣቸዋለሁ።
23አንተ ደማቸውን ረግጠህ ታልፋለህ፤
ውሾችህም ደም ይልሳሉ።”
24አምላክ ሆይ! የድል አድራጊነትህ ሰልፍ በሁሉም ይታያል፤
የእኔ ንጉሥና አምላክ በክብር አጀብ ወደ መቅደሱ
ሲገባ ይታያል።
25ዘማሪዎች ከፊት፥ ሙዚቀኞች ከኋላ፥
አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል፥
ሆነው ይታያሉ።
26እነርሱም፦ “በሕዝቡ ጉባኤ መካከል አምላክን አመስግኑ!
በእስራኤል ጉባኤ መካከል
እግዚአብሔርን አመስግኑ!” ይላሉ።
27በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤
ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ።
በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።
28አምላክ ሆይ! ኀይልህን ግለጥ፤
ከዚህ በፊት እኛን ያዳንክበትን ብርታትህን አሳይ።
29በዚህ ዐይነት በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ
ነገሥታት መባን ያመጡልሃል።
30በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤
ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤
ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤
ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።
31መልክተኞች ከግብጽ ይመጣሉ፤
ኢትዮጵያም እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
32የዓለም መንግሥታት ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ፤
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።
33ከሰማያት በላይ ወዳለው ሰማይ ለሚወጣው ዘምሩ፤
በሚያስገመግም ብርቱ ድምፅ ሲናገርም አድምጡት።
34ግርማው በእስራኤል ላይ፥
ኀይሉም በሰማይ ላይ ስለ ሆነ
የአምላክን ኀይል ዐውጁ።
35የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር
ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤
እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል።
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 68: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 68
68
የድል መዝሙር
1እግዚአብሔር ይነሣ!
ጠላቶቹም ይበተኑ!
የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ!
2ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ አብንናቸው፤
ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚያልቅ ክፉዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ!
3ደጋግ ሰዎች ግን ደስ ይበላቸው፤
በፊቱም ሐሴት ያድርጉ፤
በደስታም ይፈንጥዙ!
4ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤
በደመናዎች ላይ ለሚጓዘው መንገድ አዘጋጁ፤
ስሙ እግዚአብሔር ነው፤
በፊቱ ደስ ይበላችሁ! #68፥4 በደመናዎች ላይ፦ ወይም “በምድረ በዳ”።
5በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ
አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤
ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው።
6መጠጊያ ላጡ ብቸኞች የሚኖሩበትን ቤት ይሰጣቸዋል፤
እስረኞች ነጻ ወጥተው በብልጽግና እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤
ዐመፀኞች ግን በሚያቃጥል በረሓ ይኖራሉ።
7አምላክ ሆይ! ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፥
በበረሓም አብረሃቸው በተጓዝህ ጊዜ፥
8የሲና አምላክ በመምጣቱ፥
የእስራኤል አምላክ በመገለጡ፥
ምድር ተናወጠች፤ ሰማይም ዝናብን አዘነበ። #ዘፀ. 19፥18።
9ብዙ ዝናብ እንዲዘንብ አደረግህ፤
ያረጀውን መሬትህን አደስህ፤
10ሕዝቦችህም መኖሪያቸውን በዚያ አደረጉ፤
በቸርነትህም ለድኾች የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አዘጋጀህላቸው።
11እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጠ፤
ብዙ ሴቶችም ዜናውን አሠራጩ፤
12እንዲህም አሉ፦
“ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ወደ ኋላቸው ሸሹ!
በቤት የቀሩ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ፤
13በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት
ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ
አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው
ማዕድናዊ ርግቦችን አገኙ፤
14ሁሉን የሚችል አምላክ ነገሥታትን በበታተነ ጊዜ
በረዶ በጻልሞን ተራራዎች ላይ እንዲዘንብ አደረገ።
15“የባሳን ተራራ ብዙ ወጣ ገባ የሆነና
ግርማ ያለው ተራራ ነው።
16እናንተ ባለ ብዙ ወጣ ገብ ተራራዎች፥
እግዚአብሔር ሊኖርበት ወደ መረጠው ተራራ
በቅናት የምትመለከቱት ለምንድን ነው?
በዚያ እኮ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይኖርበታል።
17“እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቈጠሩት
ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ይመጣል።
18እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥
ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ
ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤
ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ። #ኤፌ. 4፥8።
19“ሸክማችንን በየቀኑ የሚያቀልልንና እኛን የሚያድን
እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን።
20አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው፤
ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን ጌታ እግዚአብሔር ነው።
21በእርግጥ እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ ይቀጠቅጣል፤
በጠጒር የተሸፈነ አናታቸውን ይሰባብራል።”
22ጌታ እንዲህ ይላል፤
“ጠላቶችህን ከባሳንና ከጥልቅ ባሕር መልሼ አመጣቸዋለሁ።
23አንተ ደማቸውን ረግጠህ ታልፋለህ፤
ውሾችህም ደም ይልሳሉ።”
24አምላክ ሆይ! የድል አድራጊነትህ ሰልፍ በሁሉም ይታያል፤
የእኔ ንጉሥና አምላክ በክብር አጀብ ወደ መቅደሱ
ሲገባ ይታያል።
25ዘማሪዎች ከፊት፥ ሙዚቀኞች ከኋላ፥
አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል፥
ሆነው ይታያሉ።
26እነርሱም፦ “በሕዝቡ ጉባኤ መካከል አምላክን አመስግኑ!
በእስራኤል ጉባኤ መካከል
እግዚአብሔርን አመስግኑ!” ይላሉ።
27በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤
ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ።
በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።
28አምላክ ሆይ! ኀይልህን ግለጥ፤
ከዚህ በፊት እኛን ያዳንክበትን ብርታትህን አሳይ።
29በዚህ ዐይነት በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ
ነገሥታት መባን ያመጡልሃል።
30በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤
ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤
ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤
ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።
31መልክተኞች ከግብጽ ይመጣሉ፤
ኢትዮጵያም እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
32የዓለም መንግሥታት ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ፤
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።
33ከሰማያት በላይ ወዳለው ሰማይ ለሚወጣው ዘምሩ፤
በሚያስገመግም ብርቱ ድምፅ ሲናገርም አድምጡት።
34ግርማው በእስራኤል ላይ፥
ኀይሉም በሰማይ ላይ ስለ ሆነ
የአምላክን ኀይል ዐውጁ።
35የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር
ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤
እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል።
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997