መጽሐፈ መዝሙር 70
70
ርዳታን ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
(የመዝሙር 40፥13-17 ተመሳሳይ)
1አምላክ ሆይ! አድነኝ!
እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህም እርዳኝ!
2ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ ግራም ይጋቡ፤
የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
3እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ
ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
4አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤
ሐሴትም ያድርጉ፤
ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ
ዘወትር “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።
5እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤
አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤
እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ
አትዘግይ!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 70: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 70
70
ርዳታን ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
(የመዝሙር 40፥13-17 ተመሳሳይ)
1አምላክ ሆይ! አድነኝ!
እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህም እርዳኝ!
2ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይፈሩ ግራም ይጋቡ፤
የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
3እሰይ! እሰይ! እያሉ የሚያፌዙብኝ ሁሉ
ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
4አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤
ሐሴትም ያድርጉ፤
ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ
ዘወትር “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።
5እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤
አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤
እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ
አትዘግይ!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997