መጽሐፈ መዝሙር 75
75
(ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ በሚል የዜማ ቃና የአሳፍ መዝሙር)
የእግዚአብሔር ፈራጅነት
1አምላክ ሆይ፥ እናመሰግንሃለን፤
አንተ ወደ እኛ ስለ ቀረብክ
ለስምህ ምስጋና እናቀርባለን፤
ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ እንናገራለን።
2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
“ፍርድ የምሰጥበትን ጊዜ ወስኛለሁ፤
በዚያን ጊዜ በትክክል እፈርዳለሁ።
3ምድር ስትናወጥ፥
በውስጥዋ ያሉትም ሕያዋን ፍጥረቶች ቢንቀጠቀጡም እንኳ
እኔ የምድርን መሠረት አጸናለሁ።
4ትዕቢተኞችን ‘አትታበዩ’
ክፉዎችን ‘አታምፁ’ እላቸዋለሁ፤
5በእግዚአብሔር ላይ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤
ወይም በትዕቢት አትናገር።”
6ፍርድ ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፥
ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፤
7በአንዱ ላይ የሚፈርድ፥
ሌላውን ነጻ የሚያወጣ፥
ትክክለኛ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው።
8እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ
የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤
በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤
እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
9እኔ ግን ስለ ያዕቆብ አምላክ ከመናገር
ስለ ክብሩም ከመዘመር ከቶ አልቈጠብም።
10እርሱ የክፉዎችን ኀይል ይሰብራል፤
የጻድቃን ኀይል ግን እየጨመረ ይሄዳል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 75: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 75
75
(ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ በሚል የዜማ ቃና የአሳፍ መዝሙር)
የእግዚአብሔር ፈራጅነት
1አምላክ ሆይ፥ እናመሰግንሃለን፤
አንተ ወደ እኛ ስለ ቀረብክ
ለስምህ ምስጋና እናቀርባለን፤
ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ እንናገራለን።
2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
“ፍርድ የምሰጥበትን ጊዜ ወስኛለሁ፤
በዚያን ጊዜ በትክክል እፈርዳለሁ።
3ምድር ስትናወጥ፥
በውስጥዋ ያሉትም ሕያዋን ፍጥረቶች ቢንቀጠቀጡም እንኳ
እኔ የምድርን መሠረት አጸናለሁ።
4ትዕቢተኞችን ‘አትታበዩ’
ክፉዎችን ‘አታምፁ’ እላቸዋለሁ፤
5በእግዚአብሔር ላይ ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤
ወይም በትዕቢት አትናገር።”
6ፍርድ ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፥
ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፤
7በአንዱ ላይ የሚፈርድ፥
ሌላውን ነጻ የሚያወጣ፥
ትክክለኛ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው።
8እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ
የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤
በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤
እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
9እኔ ግን ስለ ያዕቆብ አምላክ ከመናገር
ስለ ክብሩም ከመዘመር ከቶ አልቈጠብም።
10እርሱ የክፉዎችን ኀይል ይሰብራል፤
የጻድቃን ኀይል ግን እየጨመረ ይሄዳል።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997