መጽሐፈ መዝሙር 77
77
የመጽናኛ ጸሎት
1እርሱ ይሰማኝ ዘንድ
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤
አሁንም ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ።
2በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤
ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ
ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤
ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
3ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እተክዛለሁ፤
በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ይዝላል።
4ሌሊቱን ሙሉ አነቃኸኝ፤
ጭንቀቴም ስለ በዛ መናገር አልቻልኩም።
5ስላለፉት ቀኖች አስባለሁ፤
ጥንት ስለ ነበሩት ዓመቶችም አስታውሳለሁ።
6ሌሊቱን የማነጋው በጥልቅ ሐሳብ ነው፤
ሳሰላስል ሳለሁ ራሴን የምጠይቀው እንዲህ እያልኩ ነው፤
7“እግዚአብሔር ለዘወትር ይጥለናልን?
ከእንግዲህስ ወዲህ ለእኛ ቸርነት አያደርግምን?
8እኛን ማፍቀሩንስ ፈጽሞ ትቶአልን?
ቃል ኪዳኑስ ከእንግዲህ ወዲህ አይጸናምን?
9እግዚአብሔር ምሕረት ማድረጉን ረስቶአልን?
ቊጣውስ ርኅራኄውን ገታውን?”
10ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ያስጨነቀኝ
በታላቁ ኀይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው።
11እግዚአብሔር ሆይ!
ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤
ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል።
12ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤
ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ።
13አምላክ ሆይ፥
አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤
እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው?
14ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤
አንተ በሕዝቦች መካከል ኀይልህን አሳይተሃል።
15በኀይልህ የያዕቆብና የዮሴፍ ዘሮች
የሆኑትን ሕዝብህን ተቤዥተሃል።
16አምላክ ሆይ!
ውሃው አንተን ባየ ጊዜ ፈራ፤
ጥልቅ ባሕሮችም ተንቀጠቀጡ።
17ደመናዎች ዝናብን አዘነቡ፤
ነጐድጓድ በሰማይ አስገመገመ፤
የመብረቅ ፍላጻዎችህም ከላይ ከሰማይ አንጸባረቁ።
18የነጐድጓድህ ጩኸት በዐውሎ ነፋስ አስተጋባ፤
የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ፤
ምድር ተናወጠች፥ ተንቀጠቀጠችም።
19መንገድህ በባሕር መካከል ነበር፤
ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበር፤
ነገር ግን የእግርህ ዱካ አልተገኘም።
20እረኛ የበጎችን መንጋ እንደሚመራ፥
አንተም በሙሴና በአሮን አማካይነት ሕዝብህን መራህ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 77: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 77
77
የመጽናኛ ጸሎት
1እርሱ ይሰማኝ ዘንድ
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤
አሁንም ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ።
2በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤
ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ
ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤
ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
3ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እተክዛለሁ፤
በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ይዝላል።
4ሌሊቱን ሙሉ አነቃኸኝ፤
ጭንቀቴም ስለ በዛ መናገር አልቻልኩም።
5ስላለፉት ቀኖች አስባለሁ፤
ጥንት ስለ ነበሩት ዓመቶችም አስታውሳለሁ።
6ሌሊቱን የማነጋው በጥልቅ ሐሳብ ነው፤
ሳሰላስል ሳለሁ ራሴን የምጠይቀው እንዲህ እያልኩ ነው፤
7“እግዚአብሔር ለዘወትር ይጥለናልን?
ከእንግዲህስ ወዲህ ለእኛ ቸርነት አያደርግምን?
8እኛን ማፍቀሩንስ ፈጽሞ ትቶአልን?
ቃል ኪዳኑስ ከእንግዲህ ወዲህ አይጸናምን?
9እግዚአብሔር ምሕረት ማድረጉን ረስቶአልን?
ቊጣውስ ርኅራኄውን ገታውን?”
10ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ያስጨነቀኝ
በታላቁ ኀይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው።
11እግዚአብሔር ሆይ!
ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤
ባለፉት ዘመናት ያደረግኻቸው ተአምራት ትዝ ይሉኛል።
12ሥራዎችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤
ለድርጊቶችህም ከፍ ያለ ግምት እሰጣለሁ።
13አምላክ ሆይ፥
አንተ የምታደርገው ሁሉ ቅዱስ ነው፤
እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማነው?
14ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤
አንተ በሕዝቦች መካከል ኀይልህን አሳይተሃል።
15በኀይልህ የያዕቆብና የዮሴፍ ዘሮች
የሆኑትን ሕዝብህን ተቤዥተሃል።
16አምላክ ሆይ!
ውሃው አንተን ባየ ጊዜ ፈራ፤
ጥልቅ ባሕሮችም ተንቀጠቀጡ።
17ደመናዎች ዝናብን አዘነቡ፤
ነጐድጓድ በሰማይ አስገመገመ፤
የመብረቅ ፍላጻዎችህም ከላይ ከሰማይ አንጸባረቁ።
18የነጐድጓድህ ጩኸት በዐውሎ ነፋስ አስተጋባ፤
የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ፤
ምድር ተናወጠች፥ ተንቀጠቀጠችም።
19መንገድህ በባሕር መካከል ነበር፤
ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበር፤
ነገር ግን የእግርህ ዱካ አልተገኘም።
20እረኛ የበጎችን መንጋ እንደሚመራ፥
አንተም በሙሴና በአሮን አማካይነት ሕዝብህን መራህ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997