መጽሐፈ መዝሙር 89
89
የመከራ ጊዜ መዝሙር
1እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ዘወትር እዘምራለሁ፤
እውነተኛነትህንም ለትውልድ ሁሉ እገልጣለሁ።
2ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና
ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ።
3አንተ አስቀድመህ፦ “ከመረጥኩት ሰው ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፤
ለአገልጋዬ ለዳዊት የተስፋ ቃል ሰጠሁት” ብለህ ነበር፤
4የሰጠኸውም የተስፋ ቃል
“ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤
ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው። #2ሳሙ. 7፥12-16፤ 1ዜ.መ. 17፥11-14፤ መዝ. 132፥11፤ ሐ.ሥ. 2፥30።
5እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ
የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።
6በሰማይ እግዚአብሔርን የሚመስል የለም፤
ከሰማይ መላእክትም መካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚስተካከል የለም።
7በሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤ መካከል እግዚአብሔር የተፈራ ነው፤
በዙሪያውም ካሉት ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው።
8የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ!
እንደ አንተ ያለ ኀያል ማነው!
አንተ በሁሉ ነገር ታማኝ ነህ።
9አንተ የባሕሩን መናወጥ በሥልጣንህ ታዛለህ፤
ማዕበሉንም ጸጥ ታደርጋለህ።
10ረዓብ የተባለውን አውሬ ቀጥቅጠህ ገደልከው፤
በታላቁ ኀይልህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።
11ሰማይና ምድር የአንተ ናቸው፤
ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ።
12አንተ ሰሜንና ደቡብን ፈጠርክ፤
የታቦርና የሔርሞን ተራራዎች ለአንተ በደስታ ይዘምራሉ።
13ሥልጣንህ እጅግ የበረታ ነው፤
ኀይልህም እጅግ ታላቅ ነው።
14ጽድቅና ትክክለኛ ፍርድ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤
ፍቅርና ታማኝነት ከአንተ ጋር ናቸው።
15ጌታ ሆይ! የምስጋና መዝሙር የሚያቀርቡልህና
በቸርነትህ ብርሃን የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው።
16በስምህ ቀኑን ሙሉ ይደሰታሉ፤
የማዳን ኀይልህም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
17ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤
በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል።
18አምላካችንና ንጉሣችን የእስራኤል ቅዱስ ሆይ!
አንተ በእውነት ጋሻችን ነህ።
እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠው የተስፋ ቃል #1ነገ. 4፥31።
19አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ
እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤
“አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤
ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ።
20አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤
የተቀደሰ ዘይት ቀብቼም አነገሥኩት። #1ሳሙ. 13፥14፤ ሐ.ሥ. 13፥22፤ 1ሳሙ. 16፥12።
21እርሱን ለመርዳትና ለማበርታት፥
እኔ ዘወትር ከእርሱ ጋር ነኝ።
22ጠላት አይረታውም፤
ክፉም ሰው አያዋርደውም።
23ጠላቶቹን አደቅለታለሁ፤
የሚጠሉትንም ሁሉ ከፊቱ አጠፋለታለሁ።
24ታማኝነቴና ዘለዓለማዊ ፍቅሬ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ይሆናል።
በሥልጣኔም ብርቱ አደርገዋለሁ።
25ግዛቱንም በባሕርና በወንዞች ማዶ
በሚገኘው ምድር ላይ አደርግለታለሁ።
26እርሱም ‘አንተ አባቴና አምላኬ ነህ፤
አንተ አምባዬና አዳኜ ነህ’ ይለኛል።
27ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ እንዲሆን
የብኲርናን ማዕርግ እሰጠዋለሁ። #ራዕ. 1፥5።
28ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፤
ከእርሱም ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ከቶ አይፈርስም።
29ዙፋኑ እንደ ሰማይ የጸና ይሆናል፤
ዘሩም ለዘለዓለም ይነግሣል።
30“ነገር ግን የእርሱ ዘሮች ሕጌን ቢጥሱ፥
በሥርዓቴም ባይኖሩ፤
31ድንጋጌዎቼን ቢተላለፉና
ትእዛዞቼን ባይጠብቁ፥
32በኃጢአታቸው ምክንያት እቀጣቸዋለሁ፤
በበደላቸውም ምክንያት መከራ አመጣባቸዋለሁ።
33ነገር ግን ለዳዊት ያለኝ ፍቅር ከቶ አይገታም፤
ለእርሱ የሰጠሁትንም የተስፋ ቃል ከመፈጸም ወደ ኋላ አልልም።
34ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አላፈርስም፤
ለእርሱ ከሰጠሁትም የተስፋ ቃል አንዱን እንኳ አላስቀርም።
35“በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ በቅዱስ ስሜ
ስለ ማልኩ ለዳዊት ከቶ አልዋሽም።
36ትውልዱ አይቋረጥም፤
መንግሥቱንም ፀሐይ እስከምትኖርበት ዘመን እጠብቃለሁ።
37በሰማይ በእውነተኛነት እንደምትመሰክረው
እንደ ጨረቃም የጸና ይሆናል።”
በንጉሥ ዳዊት መሸነፍ ምክንያት የደረሰ ሐዘን
38አሁን ግን በመረጥከው ንጉሥ ላይ ተቈጥተሃል፤
ተለይተኸዋል፤ ጥለኸዋልም።
39ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤
ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል።
40ቅጽሮቹን አፈራርሰሃል፤
ምሽጎቹንም ደምስሰሃል።
41የመንገድ ተላላፊዎች ሁሉ ንብረቱን ይዘርፋሉ፤
የጐረቤቶቹ መሳለቂያ ሆኖአል።
42ድልን ለጠላቶቹ ሰጥተህ፥
እንዲደሰቱ አደረግኻቸው።
43የመዘዘውን ሰይፍ እንዲመልስ አድርገኸዋል፤
በጦርነትም አልረዳኸውም።
44በትረ መንግሥቱን ነጠቅኸው፤
ዙፋኑንም በመሬት ላይ ጣልክበት።
45ያለ ዕድሜው አስረጀኸው፤
በኀፍረትም ሸፈንከው።
46እግዚአብሔር ሆይ!
የምትሰወረው ለዘለዓለም ነውን?
ቊጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?
47ዕድሜዬ ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስብ፤
ሰውን ሁሉ የፈጠርከው ለከንቱ ነውን?
48ሰው ሞት ሳይደርስበት እንዲሁ ለመኖር እንዴት ይችላል?
ወደ መቃብር ሳይወርድ ሊቀርስ እንዴት ይችላል?
49ጌታ ሆይ!
የቀድሞዎቹ የፍቅርህ ማረጋገጫዎች የት አሉ?
ለዳዊት የሰጠኸውስ የተስፋ ቃል የት ነው?
50እኔ አገልጋይህ የቱን ያኽል እንደምሰደብ፥
የሕዝቦችን ሁሉ ስድብ ታግሼ እንደምኖር አስብ
51እግዚአብሔር ሆይ!
ጠላቶችህ የመረጥከውን ንጉሥ ይሰድባሉ፤
በሄደበት ሁሉ ያፌዙበታል።
52እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
አሜን! አሜን!
ክፍል አራት
(መዝ. 90—106)
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 89: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 89
89
የመከራ ጊዜ መዝሙር
1እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ዘወትር እዘምራለሁ፤
እውነተኛነትህንም ለትውልድ ሁሉ እገልጣለሁ።
2ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና
ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ።
3አንተ አስቀድመህ፦ “ከመረጥኩት ሰው ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፤
ለአገልጋዬ ለዳዊት የተስፋ ቃል ሰጠሁት” ብለህ ነበር፤
4የሰጠኸውም የተስፋ ቃል
“ዘርህ ለዘለዓለም ይነግሣል፤
ትውልድህንም ለዘለዓለም አጸናዋለሁ” የሚል ነው። #2ሳሙ. 7፥12-16፤ 1ዜ.መ. 17፥11-14፤ መዝ. 132፥11፤ ሐ.ሥ. 2፥30።
5እግዚአብሔር ሆይ! ሰማያት ድንቅ ሥራዎችህን ያመስግኑ
የሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤም ታማኝነትህን ከፍ ከፍ ያድርጉ።
6በሰማይ እግዚአብሔርን የሚመስል የለም፤
ከሰማይ መላእክትም መካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚስተካከል የለም።
7በሰማያዊው የቅዱሳን ጉባኤ መካከል እግዚአብሔር የተፈራ ነው፤
በዙሪያውም ካሉት ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው።
8የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ!
እንደ አንተ ያለ ኀያል ማነው!
አንተ በሁሉ ነገር ታማኝ ነህ።
9አንተ የባሕሩን መናወጥ በሥልጣንህ ታዛለህ፤
ማዕበሉንም ጸጥ ታደርጋለህ።
10ረዓብ የተባለውን አውሬ ቀጥቅጠህ ገደልከው፤
በታላቁ ኀይልህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።
11ሰማይና ምድር የአንተ ናቸው፤
ዓለምንና በውስጡ ያሉትን ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ።
12አንተ ሰሜንና ደቡብን ፈጠርክ፤
የታቦርና የሔርሞን ተራራዎች ለአንተ በደስታ ይዘምራሉ።
13ሥልጣንህ እጅግ የበረታ ነው፤
ኀይልህም እጅግ ታላቅ ነው።
14ጽድቅና ትክክለኛ ፍርድ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤
ፍቅርና ታማኝነት ከአንተ ጋር ናቸው።
15ጌታ ሆይ! የምስጋና መዝሙር የሚያቀርቡልህና
በቸርነትህ ብርሃን የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው።
16በስምህ ቀኑን ሙሉ ይደሰታሉ፤
የማዳን ኀይልህም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
17ገናናው ኀይልህ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤
በቸርነትህም ብርታታቸው እያደገ ይሄዳል።
18አምላካችንና ንጉሣችን የእስራኤል ቅዱስ ሆይ!
አንተ በእውነት ጋሻችን ነህ።
እግዚአብሔር ለዳዊት የሰጠው የተስፋ ቃል #1ነገ. 4፥31።
19አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ
እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤
“አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤
ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ።
20አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤
የተቀደሰ ዘይት ቀብቼም አነገሥኩት። #1ሳሙ. 13፥14፤ ሐ.ሥ. 13፥22፤ 1ሳሙ. 16፥12።
21እርሱን ለመርዳትና ለማበርታት፥
እኔ ዘወትር ከእርሱ ጋር ነኝ።
22ጠላት አይረታውም፤
ክፉም ሰው አያዋርደውም።
23ጠላቶቹን አደቅለታለሁ፤
የሚጠሉትንም ሁሉ ከፊቱ አጠፋለታለሁ።
24ታማኝነቴና ዘለዓለማዊ ፍቅሬ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ይሆናል።
በሥልጣኔም ብርቱ አደርገዋለሁ።
25ግዛቱንም በባሕርና በወንዞች ማዶ
በሚገኘው ምድር ላይ አደርግለታለሁ።
26እርሱም ‘አንተ አባቴና አምላኬ ነህ፤
አንተ አምባዬና አዳኜ ነህ’ ይለኛል።
27ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ እንዲሆን
የብኲርናን ማዕርግ እሰጠዋለሁ። #ራዕ. 1፥5።
28ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፤
ከእርሱም ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ከቶ አይፈርስም።
29ዙፋኑ እንደ ሰማይ የጸና ይሆናል፤
ዘሩም ለዘለዓለም ይነግሣል።
30“ነገር ግን የእርሱ ዘሮች ሕጌን ቢጥሱ፥
በሥርዓቴም ባይኖሩ፤
31ድንጋጌዎቼን ቢተላለፉና
ትእዛዞቼን ባይጠብቁ፥
32በኃጢአታቸው ምክንያት እቀጣቸዋለሁ፤
በበደላቸውም ምክንያት መከራ አመጣባቸዋለሁ።
33ነገር ግን ለዳዊት ያለኝ ፍቅር ከቶ አይገታም፤
ለእርሱ የሰጠሁትንም የተስፋ ቃል ከመፈጸም ወደ ኋላ አልልም።
34ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አላፈርስም፤
ለእርሱ ከሰጠሁትም የተስፋ ቃል አንዱን እንኳ አላስቀርም።
35“በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ በቅዱስ ስሜ
ስለ ማልኩ ለዳዊት ከቶ አልዋሽም።
36ትውልዱ አይቋረጥም፤
መንግሥቱንም ፀሐይ እስከምትኖርበት ዘመን እጠብቃለሁ።
37በሰማይ በእውነተኛነት እንደምትመሰክረው
እንደ ጨረቃም የጸና ይሆናል።”
በንጉሥ ዳዊት መሸነፍ ምክንያት የደረሰ ሐዘን
38አሁን ግን በመረጥከው ንጉሥ ላይ ተቈጥተሃል፤
ተለይተኸዋል፤ ጥለኸዋልም።
39ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤
ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል።
40ቅጽሮቹን አፈራርሰሃል፤
ምሽጎቹንም ደምስሰሃል።
41የመንገድ ተላላፊዎች ሁሉ ንብረቱን ይዘርፋሉ፤
የጐረቤቶቹ መሳለቂያ ሆኖአል።
42ድልን ለጠላቶቹ ሰጥተህ፥
እንዲደሰቱ አደረግኻቸው።
43የመዘዘውን ሰይፍ እንዲመልስ አድርገኸዋል፤
በጦርነትም አልረዳኸውም።
44በትረ መንግሥቱን ነጠቅኸው፤
ዙፋኑንም በመሬት ላይ ጣልክበት።
45ያለ ዕድሜው አስረጀኸው፤
በኀፍረትም ሸፈንከው።
46እግዚአብሔር ሆይ!
የምትሰወረው ለዘለዓለም ነውን?
ቊጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?
47ዕድሜዬ ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስብ፤
ሰውን ሁሉ የፈጠርከው ለከንቱ ነውን?
48ሰው ሞት ሳይደርስበት እንዲሁ ለመኖር እንዴት ይችላል?
ወደ መቃብር ሳይወርድ ሊቀርስ እንዴት ይችላል?
49ጌታ ሆይ!
የቀድሞዎቹ የፍቅርህ ማረጋገጫዎች የት አሉ?
ለዳዊት የሰጠኸውስ የተስፋ ቃል የት ነው?
50እኔ አገልጋይህ የቱን ያኽል እንደምሰደብ፥
የሕዝቦችን ሁሉ ስድብ ታግሼ እንደምኖር አስብ
51እግዚአብሔር ሆይ!
ጠላቶችህ የመረጥከውን ንጉሥ ይሰድባሉ፤
በሄደበት ሁሉ ያፌዙበታል።
52እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
አሜን! አሜን!
ክፍል አራት
(መዝ. 90—106)
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997