የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር መግቢያ

መግቢያ
መጽሐፈ መዝሙር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሁሉም የረዘመ ነው። እነዚህም መዝሙሮች በግለሰብ ወይም በኅብረት የሚዘመሩ ወይም የሚነበቡ ናቸው።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ መቶ ኀምሳ መዝሙሮች ይገኛሉ። አብዛኞቹንም የጻፋቸው ንጉሥ ዳዊት ነው። በረጅም ዘመናት ተሰባስበው ለእስራኤል ሕዝብ የአምልኮ ሥርዓት ዋኖቹ ሆኑ። አንዳንዶቹ መዝሙሮች ምን ዐይነት የሙዚቃ መሣሪያና ምን ዐይነት ቃና መከተል እንደሚገባው የመዘምራንን አለቃ ይመሩታል። ለምሳሌ መዝሙር 4 እና መዝሙር 45ን ይመለከቷል። ውዳሴ፥ ምስጋና፥ እምነት፥ ተስፋ፥ ስለ ኃጢአት ጸጸት፥ የእግዚአብሔር ታማኝነትና ርዳታውን የመሳሰሉት ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች በመዝሙሮቹ ውስጥ ተንጸባርቀዋል።
የመዝሙሮቹ ዋነኛው ማዕከላዊ ሐሳብ በእግዚአብሔር ላይ መታመን ነው። የመዝሙሮቹ ጸሐፊዎች እግዚአብሔርን በማመስገን ወይም ችግራቸውን በመግለጽ እውነተኛ ስሜታቸውን ያቀርባሉ።
በጥንታዊት እስራኤል መዝሙሮቹን በተለያዩ ሁኔታዎች ይጠቀሙባቸው ነበር። እነርሱም፦
1. እንደ መዝሙር 105 እግዚአብሔርን ለማመስገን፤
2. እንደ መዝሙር 13 ሐዘንን ለመግለጽ፤
3. እንደ መዝሙር 1 ለማስተማር፤
4. እንደ መዝሙር 72 የእስራኤል ነገሥታት በቅን እንዲፈርዱ ለመጸለይ፥
5. እንደ መዝሙር 47 እግዚአብሔር በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ያለውን ሥልጣን ለመግለጽ፥
6. እንደ መዝሙር 122 ፍቅርን ለኢየሩሳሌም ለመግለጽና፥
7. እንደ መዝሙር 126 በዓላትን ለማክበር ናቸው።
በእርግጥ ብዙዎች መዝሙሮች ከአንድ ዓላማ በላይ ሊኖራቸው ይችላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስብከቱና በትምህርቱ ብዙ ጊዜ በመዝሙሮች ይጠቀም ነበር። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችም በየጊዜው መጽሐፈ መዝሙርን ጠቅሰዋል። የቀድሞዎቹ ክርስቲያኖችም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔር ያደረገውን በጎ ነገር ለአምልኮ በመዝሙሮቹ ተጠቅመዋል። ለምሳሌ በመዝሙር 118 ውስጥ የሚገኘው ቊጥር 22 በአዲስ ኪዳን ውስጥ ስድስት ጊዜ ተጠቅሶአል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መጽሐፈ መዝሙር በአምስት ንዑሳን ክፍሎች ይከፈላል፦ አብዛኞቹ የመጀመሪያውና የሁለተኛው ክፍሎች የተጻፉት በንጉሥ ዳዊት ነው። የሦስተኛው ክፍል መዝሙሮች የተጻፉት አንድም በአሳፍ ነው፥ ወይም በቆሬ ልጆች ነው።
መዝሙር 120-134 የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት መዝሙሮች ናቸው ከዚህ ቀጥሎ አምስቱ የመጽሐፈ መዝሙር ንዑሳን ክፍሎች ቀርበዋል፦
መዝሙር 1-41
መዝሙር 42-72
መዝሙር 73-89
መዝሙር 90-106
መዝሙር 107-150

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ