የዮሐንስ ራእይ 7
7
መቶ አርባ አራት ሺህ የእስራኤል ሰዎች
1ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማእዘኖች ቆመው አየሁ፤ እነርሱ በምድርም ሆነ በባሕር ወይም በዛፍ ላይ ምንም ነፋስ እንዳይነፍስ ከአራቱ አቅጣጫ የሚመጡትን የምድር ነፋሶች ያዙ። #ኤር. 49፥36፤ ዳን. 7፥2፤ ዘካ. 6፥5። 2የሕያው አምላክን ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክም ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ ምድርንና ባሕርን እንዲጐዱ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ 3“በአምላካችን አገልጋዮች ግንባር ላይ ማኅተም እስክናትምባቸው ድረስ፥ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጒዱ” ብሎ ጮኸ። #ሕዝ. 9፥4፤6። 4የታተሙትንም ሰዎች ቊጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ የታተሙት ሰዎች ቊጥር መቶ አርባ አራት ሺህ ነበር። 5ከይሁዳ ነገድ የታተሙት ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሮቤል ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከጋድ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ 6ከአሴር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከምናሴ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ 7ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ 8ከዛብሎን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከዮሴፍ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከብንያም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ።
ነጭ ልብስ የለበሱ ብዙ ሕዝቦች
9ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችን አየሁ፤ እነርሱ ከሕዝብና ከነገድ፥ ከወገንና ልዩ ልዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሁሉ የተውጣጡ ነበሩ፤ እነዚህ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤ 10በታላቅ ድምፅ እየጮኹም፥
“ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው
የአምላካችንና የበጉ ነው!” ይሉ ነበር።
11መላእክቱ ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም እንስሶች ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑ ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ 12እንዲህም አሉ፦
“አሜን! ውዳሴ፥ ገናናነት፥ ጥበብ፥
ምስጋና፥ ክብር፥ ኀይል፥ ብርታት
ለአምላካችን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።”
13ከሽማግሌዎቹ አንዱ ወደ እኔ መለስ ብሎ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱ እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ?” አለኝ።
14እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤ #ዳን. 12፥1፤ ማቴ. 24፥21፤ ማር. 13፥19። 15ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሆነው ሌሊትና ቀን በመቅደሱ ያገለግሉታል፤ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም መጠለያቸው ይሆናል። 16ከእንግዲህ ወዲህ አይርባቸውም፤ አይጠማቸውም፤ ፀሐይ አይመታቸውም፤ ሙቀት አያገኛቸውም፤ #ኢሳ. 49፥10። 17በዙፋኑ መካከል ያለው በግ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤ እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ይጠርግላቸዋል።” #መዝ. 23፥1፤ ሕዝ. 34፥23፤ መዝ. 23፥2፤ ኢሳ. 49፥10፤ 25፥8።
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ 7: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997