ወደ ሮም ሰዎች 9
9
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደ መረጠ
1በክርስቶስ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ኅሊናዬም እንደማልዋሽ ይመሰክርልኛል። 2ትልቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቤ አለ፤ 3በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑት ወገኖቼ ስል እኔ ከክርስቶስ ተለይቼ የእግዚአብሔር ርግማን ቢደርስብኝ በወደድኩ ነበር። 4እነርሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ልጆቹ አደረጋቸው፤ ክብሩን ገለጠላቸው፤ ቃል ኪዳን ገባላቸው፤ ሕግን ሰጣቸው፤ እውነተኛውን የአምልኮ ሥርዓት አሳያቸው፤ የተስፋውንም ቃል ሰጣቸው። #ዘፀ. 9፥4። 5እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!
6ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ቃል ተሽሮአል ማለት አይደለም፤ የእስራኤል ዘር በሙሉ እውነተኞች እስራኤላውያን አይደሉም። 7እንዲሁም የአብርሃም ዘር ሁሉ የአብርሃም ልጆች ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አብርሃምን “ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ ነው” ስላለው ነው፤ #ዘፍ. 21፥12። 8ስለዚህ በሥጋ የተወለዱት የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን ዘር ሆነው የሚቈጠሩት የተስፋው ቃል ልጆች ብቻ ናቸው። 9ይህም እግዚአብሔር የሰጠው የተስፋ ቃል “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ እመጣለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” የሚል ነበር። #ዘፍ. 18፥10።
10ይህም ብቻ ሳይሆን ርብቃ የነገድ አባታችን ከሆነው ከይስሐቅ መንታ ልጆችን በፀነሰች ጊዜ፥ 11የእግዚአብሔር ምርጫ በሥራ ሳይሆን በጥሪ መሆኑን ለመግለጥ ሁለቱ ልጆች ከመወለዳቸውና ክፉም ሆነ ደግ ከማድረጋቸው በፊት 12እግዚአብሔር ርብቃን “ታላቁ ለታናሹ ተገዢ ይሆናል” አላት። #ዘፍ. 25፥23። 13ይህም “ያዕቆብን ወደድኩ ዔሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። #ሚል. 1፥2-3።
14እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለት እንችላለን? እግዚአብሔር ያዳላል ማለትስ ከቶ አንችልም! 15እግዚአብሔር ሙሴን “ልምረው የምፈልገውን እምረዋለሁ፥ ልራራለት የምፈልገውንም እራራለታለሁ” ብሎታል። #ዘፀ. 33፥19። 16ስለዚህ የእግዚአብሔር ምርጫ የሚገኘው በሰው ፈቃድና በሰው ሥራ ሳይሆን በእግዚአብሔር ምሕረት ነው። 17በዚህ ምክንያት በቅዱስ መጽሐፍ ስለ ግብጽ ንጉሥ “በአንተ ኀይሌን ለማሳየትና ስሜም በዓለም ሁሉ ላይ እንዲታወቅ ለማድረግ አንተን አንግሼሃለሁ” የሚል ቃል ተጽፎአል። #ዘፀ. 9፥16። 18ስለዚህ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ይምረዋል፤ የሚፈልገውንም እልኸኛ ያደርገዋል።
የእግዚአብሔር ቊጣና ምሕረት
19ስለዚህ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመቃወም ማንም አይችልም፤ ታዲያ፥ እርሱ ሰዎችን በክፉ ሥራቸው ለምን ይወቅሳቸዋል” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል። 20አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን? #ኢሳ. 29፥16፤ 45፥9። 21ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዐይነት የሸክላ ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ ሌላውን ለተራ አገልግሎት አድርጎ ለመሥራት ሥልጣን የለውምን?
22እግዚአብሔር ቊጣውን ለማሳየትና ኀይሉንም ለመግለጥ ፈልጎ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቊጣ ዕቃዎች ብዙ ታግሦአቸውስ እንደ ሆነ ምን ታውቃለህ? 23ይህንንም ያደረገው አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው ለምሕረት ዕቃዎች የክብሩን ብዛት ለመግለጥ ነው። 24እኛን የምሕረት ዕቃዎቹንም ከአይሁድ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም ጠርቶናል። 25ይህም በነቢዩ በሆሴዕ እንዲህ እንደ ተባለ ነው፦
“የእኔ ሕዝብ ያልነበረውን ‘ሕዝቤ!’ ብዬ እጠራዋለሁ፤
ያልተወደደውንም ሕዝብ ‘የተወደደ!’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ #ሆሴዕ 2፥23።
26እነርሱ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ስፍራ
‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” #ሆሴዕ 1፥10።
27ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ “የእስራኤል ልጆች ቊጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢበዛ እንኳ ከእነርሱ የሚድኑት ጥቂቶች ብቻ ናቸው። 28ጌታ ሳይዘገይ በፍጥነት በዓለም ላይ ፍርዱን ይሰጣል።” #ኢሳ. 10፥22-23። 29እንዲሁም ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ የሰዶምና የገሞራ ከተሞች እንደ ጠፉ እኛም በጠፋን ነበር” ሲል አስቀድሞ ተናግሮአል። #ኢሳ. 1፥9።
30እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፤ ይህም ጽድቅ ከእምነት የሚገኘው ነው። 31ነገር ግን ጽድቅ የሚያስገኘውን ሕግ ይከተሉ የነበሩት እስራኤላውያን ሕግን ለመፈጸም ባለመቻላቸው ወደ ጽድቅ አልደረሱም። 32“ስለምን ወደ ጽድቅ አልደረሱም?” ቢባል እነርሱ ጽድቅን ለማግኘት የፈለጉት በእምነት ሳይሆን በሥራ ስለ ሆነ ነው፤ ስለዚህ በማሰናከያ ድንጋይ ተሰናከሉ፤ 33ይህም፦
“እነሆ፥ ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤
ይህም ድንጋይ ሰዎችን በማሰናከል የሚጥል አለት ነው፤
በእርሱ የሚያምን ግን አያፍርም”
ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
Currently Selected:
ወደ ሮም ሰዎች 9: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997