መኃልየ መኃልይ 2
2
1እኔ እንደ ሳሮን ጽጌረዳና
በሸለቆ ውስጥ እንደሚበቅል የሱፍ አበባ ነኝ።
ሙሽራው
2ውዴ በሴቶች መካከል ስትታይ
በእሾኽ መካከል እንደሚታይ የሱፍ አበባ ናት።
ሙሽራይቱ
3ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር
በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤
እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤
ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።
4ወደ ምግብ አዳራሹ አስገባኝ፤
ፍቅሩንም እንደ ሰንደቅ ዓላማ በእኔ ላይ ከፍ ከፍ አደረገ።
5እኔ በፍቅሩ ተይዤ ስለ ታመምኩ
ዘቢብ እየመገባችሁ አበረታቱኝ፤
በፖም ፍሬም አስደስቱኝ።
6ግራ እጁን ያንተርሰኛል፤
በቀኝ እጁም ያቅፈኛል።
7እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ!
ፍቅር ራሱ ፈቅዶ እስኪነሣ ድረስ
ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት፤
በፈጣን አጋዘንና በምድረ በዳ ዋልያ ስም
ዐደራ እላችኋለሁ።
ሁለተኛ መዝሙር
ፍቅር ሁሉንም ነገር ውብ ያደርጋል
ሙሽራይቱ
8ውዴ በተራሮችና በኮረብቶች ላይ እየዘለለና እየተወረወረ ሲመጣ
ድምፁ ይሰማል።
9ውዴ፥ ዋልያ ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል፤
እነሆም ከቤታችን ቅጽር አጠገብ ቆሞአል፤
በመስኮትም ወደ ውስጥ ይመለከታል፤
በዐይነ ርግቡ ቀዳዳ በኩል አሾልኮ ይቃኛል።
10ውዴ እንዲህ ይለኛል፥
ሙሽራው
ውዴ ሆይ! ተነሺ፤
የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ፤
11እነሆ፥ ክረምቱ አልፎአል፤
ዝናቡም ቆሞአል፤
12በየመስኩ አበባዎች መታየት ጀምረዋል፤
የዜማ ወራት ደርሶአል፤
የርግቦችም ዜማ በምድራችን ይሰማል።
13በለስ ማፍራት ጀምሮአል፤
የወይን ተክልም አብቦአል፤
የአበባውም ሽታ ምድርን ሞልቶታል፤
ስለዚህ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤
የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ።
14አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ
እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤
እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤
ድምፅሽንም ልስማው፤
ድምፅሽ አስደሳች ነው፤
ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።
የሙሽራይቱ ወንድሞች
15ወይናችን አብቦአል፤
ስለዚህ የወይን ተክላችንን እንዳያጠፉብን
ቀበሮዎችን፥ እነኛን ትናንሽ ቀበሮዎችን አጥምዳችሁ ያዙልን።
ሙሽራይቱ
16ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤
በአሸንድዬ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።
17የሌሊቱ ጨለማ እስከሚወገድ፤
የማለዳው ነፋስ እስከሚነፍስ፤
ውዴ ሆይ! እንደ ዋልያ ወይም እንደ አጋዘን ግልገል
በገደላማ ተራራዎች ላይ እየሮጥክ ተመለስ።
Currently Selected:
መኃልየ መኃልይ 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መኃልየ መኃልይ 2
2
1እኔ እንደ ሳሮን ጽጌረዳና
በሸለቆ ውስጥ እንደሚበቅል የሱፍ አበባ ነኝ።
ሙሽራው
2ውዴ በሴቶች መካከል ስትታይ
በእሾኽ መካከል እንደሚታይ የሱፍ አበባ ናት።
ሙሽራይቱ
3ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር
በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤
እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤
ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ።
4ወደ ምግብ አዳራሹ አስገባኝ፤
ፍቅሩንም እንደ ሰንደቅ ዓላማ በእኔ ላይ ከፍ ከፍ አደረገ።
5እኔ በፍቅሩ ተይዤ ስለ ታመምኩ
ዘቢብ እየመገባችሁ አበረታቱኝ፤
በፖም ፍሬም አስደስቱኝ።
6ግራ እጁን ያንተርሰኛል፤
በቀኝ እጁም ያቅፈኛል።
7እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ!
ፍቅር ራሱ ፈቅዶ እስኪነሣ ድረስ
ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት፤
በፈጣን አጋዘንና በምድረ በዳ ዋልያ ስም
ዐደራ እላችኋለሁ።
ሁለተኛ መዝሙር
ፍቅር ሁሉንም ነገር ውብ ያደርጋል
ሙሽራይቱ
8ውዴ በተራሮችና በኮረብቶች ላይ እየዘለለና እየተወረወረ ሲመጣ
ድምፁ ይሰማል።
9ውዴ፥ ዋልያ ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል፤
እነሆም ከቤታችን ቅጽር አጠገብ ቆሞአል፤
በመስኮትም ወደ ውስጥ ይመለከታል፤
በዐይነ ርግቡ ቀዳዳ በኩል አሾልኮ ይቃኛል።
10ውዴ እንዲህ ይለኛል፥
ሙሽራው
ውዴ ሆይ! ተነሺ፤
የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ፤
11እነሆ፥ ክረምቱ አልፎአል፤
ዝናቡም ቆሞአል፤
12በየመስኩ አበባዎች መታየት ጀምረዋል፤
የዜማ ወራት ደርሶአል፤
የርግቦችም ዜማ በምድራችን ይሰማል።
13በለስ ማፍራት ጀምሮአል፤
የወይን ተክልም አብቦአል፤
የአበባውም ሽታ ምድርን ሞልቶታል፤
ስለዚህ ውዴ ሆይ! ተነሺ፤
የእኔ ውብ ሆይ! ነይ አብረን እንሂድ።
14አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ
እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤
እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤
ድምፅሽንም ልስማው፤
ድምፅሽ አስደሳች ነው፤
ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።
የሙሽራይቱ ወንድሞች
15ወይናችን አብቦአል፤
ስለዚህ የወይን ተክላችንን እንዳያጠፉብን
ቀበሮዎችን፥ እነኛን ትናንሽ ቀበሮዎችን አጥምዳችሁ ያዙልን።
ሙሽራይቱ
16ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤
በአሸንድዬ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።
17የሌሊቱ ጨለማ እስከሚወገድ፤
የማለዳው ነፋስ እስከሚነፍስ፤
ውዴ ሆይ! እንደ ዋልያ ወይም እንደ አጋዘን ግልገል
በገደላማ ተራራዎች ላይ እየሮጥክ ተመለስ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997