የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መኃልየ መኃልይ መግቢያ

መግቢያ
“መኀልየ መኀልይ” የተባለው መጽሐፍ የፍቅር ቅኔዎች ቅንብር ነው፤ ከእነዚህም ቅኔዎች አብዛኞቹ የተጻፉት በመዝሙር መልክ ሲሆን፥ ወንዱ ለሴቲቱ፥ ሴቲቱም ለወንድየው ያቀረቡአቸው ናቸው። መጽሐፉ በአንዳንድ ትርጒሞች “መኀልየ መኀልይ” ወይም “ከመዝሙሮች መካከል በጣም ውብ የሆነ መዝሙር” በመባል ይታወቃል፤ በሌሎች ትርጒሞች ደግሞ “የሰሎሞን መዝሙር” በመባል ይታወቃል፤ ይህም የሆነው በዕብራይስጡ ቅጂ የሰሎሞን መሆኑ ስለ ተገለጠ ነው።
ይህ መዝሙር በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ፍቅር የሚያመለክቱ ምሳሌዎችን የያዘ ነው፤ አይሁድ ግን “በእግዚአብሔርና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያለውን ፍቅር የሚያመለክቱ ምሳሌዎችን የያዘ ነው” ይላሉ።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ፍቅር ከወይን ጠጅ ይሻላል (1፥1—2፥7)
ፍቅር ሁሉን ነገር ውብ ያደርጋል። (2፥8—3፥5)
ጋብቻ (3፥6—4፥5)
የጋብቻ ኅብረት (4፥6—5፥16)
ፍቅር ከሁሉ ይመርጣል። (6፥1—7፥6)
እኔና አንተ ብቻ (7፥7—8፥4)
የፍቅር ውዳሴ (8፥5-14)

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ