ትንቢተ ዘካርያስ 5
5
ነቢዩ ዘካርያስ በራእይ ያየው ጥቅል የብራና መጽሐፍ
1እንደገናም ስመለከት አንድ የተጠቀለለ መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አየሁ፤ 2መልአኩም “ምን ታያለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፤ እኔም “ርዝመቱ ዐሥር ሜትር፤ ስፋቱም አምስት ሜትር የሆነ፥ አንድ የተጠቀለለ የብራና መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አያለሁ” አልኩት።
3እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የተጠቀለለው መጽሐፍ በውስጡ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚመጣው ርግማን ተጽፎበታል፤ የተጠቀለለው መጽሐፍ በአንድ በኩል ‘ሌባ ሁሉ ከምድር ይወገዳል’ የሚል ሲሆን፥ በሌላ በኩል ‘በመሐላ ሐሰት የሚናገር ሁሉ ይጠፋል’ ይላል። 4የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ‘ይህን ርግማን እልካለሁ፤ ወደ እያንዳንዱ ሌባና በስሜ ምሎ በሐሰት ወደሚናገር ሰው ቤት ይገባል፤ በገባበትም ጊዜ በዚያ ቈይቶ ቤታቸውን ሁሉ ያፈራርሰዋል’ ይላል።”
ነቢዩ ዘካርያስ በቅርጫት ውስጥ ስላለች ሴት ያየው ራእይ
5መልአኩም እንደገና ወደ እኔ መጥቶ “የሚመጣው ነገር ምን እንደ ሆነ ተመልከት!” አለኝ።
6እኔም “ይህ ነገር ምንድን ነው?” አልኩት። እርሱም “በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚሠራውን ኃጢአት የሚያመለክት ቅርጫት ነው” አለኝ።
7ቅርጫቱ ከእርሳስ የተሠራ መክደኛ ነበረው፤ እኔም እያየሁት መክደኛው ተከፈተ፤ እነሆም በቅርጫቱ ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር።
8መልአኩም “እነሆ ይህች ሴት የዐመፅ ምሳሌ ነች” ከአለኝ በኋላ ወደ ታች ገፍቶ ወደ ቅርጫቱ ውስጥ አስገባት፤ ክዳኑንም መልሶ ገጠመው። 9ቀና ብዬ ስመለከት እነሆ ሁለት ሴቶች እየበረሩ ወደ እኔ መጡ፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ብርቱዎች ነበሩ። እነርሱም ያንን ቅርጫት ከመሬት አንሥተው ወደ ሰማይ ይዘውት በረሩ።
10እኔም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ “ቅርጫቱን ወዴት ነው የሚወስዱት?” ብዬ ጠየቅሁት።
11እርሱም “ወደ ሰናዖር ወስደው ቤት ሊሠሩለት ነው፤ ቤቱ ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ቅርጫቱን በዚያ ያኖሩታል” አለኝ።
Currently Selected:
ትንቢተ ዘካርያስ 5: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997