1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11
11
1 #
1ቆሮ. 4፥16፤ ፊልጵ. 3፥17። እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።
በአምልኮት ጊዜ ራስን ስለ መከናነብ
2ወንድሞች ሆይ! በሁሉ ስለምታስቡኝና እኔ ያስተላለፍኩላችሁን ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ። 3ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ። 4ራሱን ተከናንቦ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ ሁሉ ራሱን ያዋርዳል። 5ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል ትቆጠራለችና። 6ሴትም ራስዋን የማትከናነብ ከሆነ ደግሞ ጠጉርዋን ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን። 7#ዘፍ. 1፥26፤27።ወንድ የእግዚአብሔር መልክና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት። 8#ዘፍ. 2፥18-23።ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና። 9ሴት ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም። 10በዚህ ምክንያት፥ በመላእክትም ምክንያት ሴት በራስዋ ሥልጣን#11፥10 አንዳንድ ትርጉሞች “መከናነቢያ” ይላሉ ሊኖራት ይገባል። 11ነገር ግን በጌታ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ፥ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም። 12ሴት ከወንድ እንደ ሆነች ሁሉ ወንድ ደግሞ ከሴት የሚገኝ ነውና፤ ነገር ግን ሁሉም ከእግዚአብሔር ነው። 13በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትከናነብ ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን? 14ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? 15ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር አይደለምን? ምክንያቱም ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታል። 16ማንም ግን ሊከራከር ቢፈልግ፥ እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለ ልማድ የለንም።
ስለ ቅዱስ ቁርባን
(ማቴ. 26፥26-29፤ ማር. 14፥22-25፤ ሉቃ. 22፥14-20)
17ነገር ግን ይህን ትእዛዝ ስሰጥ አላመሰግናችሁም፤ ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለሚሻል ሳይሆን ለሚከፋ በመሆኑ ነው። 18በመጀመሪያ እንደ ማኅበር ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መለያየት እንዳለ እሰማለሁና፤ በከፊል ያን አምናለሁ። 19ትክክል የሆኑት እነማን እንደ ሆኑ ተለይተው እንዲታወቁ በመካከላችሁ መለያየት መኖሩ ግድ ነውና። 20በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ የምትበሉት የጌታ እራት አይደለም። 21ስትበሉ እያንዳንዱ የራሱን እራት ይበላል፤ አንዱም ይራባል ሌላው ደግሞ ይሰክራል። 22ኧረ ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትንቃላችሁን? ወይስ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።
23እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ለእናንተ ደግሞ ያስተላለፍኩላችሁ ይህ ነው፦ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት ኅብስትን አንሥቶ፤ 24አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ። 25#ዘፀ. 24፥8፤ ኤር. 31፥31-34፤ ዘፀ. 24፥6-8።እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ። 26ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
27ስለዚህ ያልተገባ ሆኖ ሳለ ይህን ኅብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። 28ሰው ግን ራሱን ይመርምር፤ እንዲሁም ከኅብስቱ ይብላ፤ ከጽዋውም ይጠጣ፤ 29ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላል፤ ይጠጣልም። 30በዚሁ ምክንያት ከእናንተ መካከል ብዙዎች የደከሙና የታመሙ አሉ፥ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል። 31በራሳችን ላይ ብንፈርድ ኖሮ ግን ባልተፈረደብንም ነበር። 32ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።
33ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! ለመብላት በተሰበሰባችሁ ጊዜ እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ። 34ማንም የራበው ቢኖር፥ ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ፥ በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር በመጣሁ ጊዜ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።
Currently Selected:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ