የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5

5
ለ.በምእመናን መካከል የተደረገ ምግባረ ብልሹነት
1 # ዘዳ. 22፥30። በእርግጥ በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል፤ የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለ። 2እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ ልታዝኑ አይገባችሁም? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።
3እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ከእናንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠራውን እፈርድበታለሁ። 4ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር፥ በጌታችን ኢየሱስ ስም ተሰብስባችሁ፥ መንፈሴም አብሮችሁ ነው፥ 5እንደዚህ ያለው ሰው፥ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን እንድትድን፥ ሥጋው ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት።
6 # ገላ. 5፥9። መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁምን? 7#ዘፀ. 12፥5።እንግዲህ እርሾ እንደሌለበት እንደ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ፥ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤ 8#ዘፀ. 13፥7፤ ዘዳ. 16፥3።ስለዚህ ተንኰልና ክፋት በሞላበት በአሮጌ እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት የቅንነትና የእውነት ቂጣ በዓላችንን እናክብር።
9በመልእክቴ ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ ጻፍሁላችሁ። 10ይህም በጠቅላላው የዚህን ዓለም ሴሰኞችን፥ ወይም ገንዘብን የሚመኙትን ነጣቂዎችንም፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩትን ማለቴ አይደለም፤ እንዲህማ ቢሆን ከዓለም ልትወጡ ይገባችሁ ነበር። 11አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ስግብግብ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ። 12#ዘዳ. 13፥5፤ 17፥7።በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? 13በውጭ ባሉት ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ