1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5
5
የእግዚአብሔርን መንጋ ስለ መጠበቅ
1እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር አብሬ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የሆንኩ፥ የክርስቶስም መከራ ምስክር የሆንኩ፥ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፥ በመካከላችሁ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ። 2#የሐዋ. 20፥28፤ ቲቶ 1፥7፤ ዮሐ. 21፥15-17።ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤ 3በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው ለመንጋው መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በኃይል በመግዛት አይሁን። 4#ጥበ. 5፥15-16፤ 1ቆሮ. 9፥25፤ 2ጢሞ. 4፥8፤ ያዕ. 1፥12።የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይደበዝዘውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ። 5#ምሳ. 3፥34።እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
6 #
ኢዮብ 22፥29፤ ያዕ. 4፥10፤ ማቴ. 23፥12፤ ሉቃ. 14፥11፤ 18፥14። እንግዲህ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ ሥር ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ። 7#መዝ. 55፥23፤ ማቴ. 6፥25-33፤ ሉቃ. 12፥22-31፤ ፊልጵ. 4፥6፤ ሲራ. 2፥1-18።እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 8#1ተሰ. 5፥6።በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል። 9በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ይህን ዓይነት መከራ እንደሚቀበሉ በማወቅ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። 10#ሮሜ 8፥18፤ 2ቆሮ. 4፥17።በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ እርሱ ራሱ ያበረታችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ያቆማችኋል፤ ይመሠርታችኋልም። 11ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብርና ኃይል ለእርሱ ይሁን! አሜን።
የመጨረሻ ሰላምታና ቡራኬ
12እንደ ታማኝ ወንድም በምቆጥረው በስልዋኖስ በኩል፥ ልመክራችሁና ጸንታችሁ የምትቆሙበት ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልገልጽላችሁ በማለት፥ ይህን አጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ። 13ከእናንተ ጋር የተመረጠችው፥ በባቢሎን ያለችው ቤተ ክርስቲያን፥ ልጄ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 14#ሮሜ 16፥16፤ 1ቆሮ. 16፥20፤ 2ቆሮ. 13፥12።በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን።
Currently Selected:
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ