1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 31
31
የሳኦል መሞት
1 #
2ሳሙ. 1፥1-16፤ 4፥4፤ 1ዜ.መ. 10፥1-12። በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይ የወደቁትን ጥለው ሸሹ። 2#1ሳሙ. 14፥49፤ 28፥19፤ 1ዜ.መ. 10፥2-3።ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን አጥብቀው ተከታተሉ፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፥ አቢናዳብንና ማልኪሹዓን ገደሉ። 3ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፤ ቀስተኞችም አገኙት፥ በቀስታቸውም ወግተው ክፉኛ አቆሰሉት። 4#1ሳሙ. 24፥6፤ መሳ. 9፥54፤ 1ዜ.መ. 10፥4።ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥ “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝ፥ እንዳያዋርዱኝም፥ አንተው ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፥ እምቢ አለው። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። 5#1ሳሙ. 10፥1፤ 26፥9፤ 2መቃ. 14፥42።ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ፥ እርሱም እንደዚሁ በሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ። 6ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ፥ አብረውት የነበሩ ሰዎች ሁሉና ጋሻ ጃግሬው የሞቱት በዚያኑ ቀን ነበር። 7በሸለቆው ማዶና ከዮርዳኖስ ባሻገር ያሉ እስራኤላውያን የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። 8በማግስቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ለመግፈፍ ሲመጡ፥ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገቿቸው። 9#1ሳሙ. 17፥54፤ 2ሳሙ. 1፥20፤ 2መቃ. 15፥35።ከዚያም የሳኦልን ራስ ቆርጠው፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈው፥ የምሥራቹን በየቤተ ጣዖቶቻቸውና በሕዝባቸው መካከል እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤም ምድር ሁሉ መልክተኞች ላኩ። 10የጦር መሣሪያውን በአስታሮት ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖሩት፤ ሬሳውን ደግሞ በቤት ሻን ግንብ ላይ አንጠለጠሉት። 11#1ሳሙ. 11፥1-11፤ 2ሳሙ. 2፥4-7፤ 21፥12-14።በገለዓድ የሚኖሩ የያቤሽ ሰዎችም ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉበትን ነገር በሰሙ ጊዜ፥ 12ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹንም ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ አምጥተው አቃጠሉ። 13ከዚያም ዐጥንቶቻቸውን ወስደው በኢያቢስ ባለው ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 31: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ