1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ
መግቢያ
የጢሞቴዎስ የትውልድ ስፍራ በታናሽይቱ እስያ በምትገኘው በኢቆንዮን ነበር። እናቱም አይሁዳዊት ስትሆን አባቱ ደግሞ የግሪክ ሰው ነበር (ሐሥ 16፥ 1-3)። እርሱ ጳውሎስ መንፈሳዊ ልጅ ሲሆን፥ በመጀመርያውና በሁለተኛው የወንጌል ስብከት ጉዞው አብሮት የሠራ ደቀመዝሙር ነበር። በ 63 ዓ.ም. ገደማ ጳውሎስ በመቄዶንያ ሳለ በኤፌሶን ለሚገኘው ጢሞቴዎስ የመጀመርያውን መልእክት ጻፈለት። በዚህ መልእክት ጳውሎስ ስለ አይሁድ እምነት በመዳንና በእውቀት ላይ ስላለው ግንኙነት፥ ስለ ጋብቻና ስለ ሐሰተኛ ትምህርቶች ያብራራል። በተጨማሪም የአንድ ቤተ ክርስቲያን እረኛ መወጣት ስላለበት ኃላፊነትና ግዴታ ይገልጻል። በዚህ መልእክት ጳውሎስ ሐሰተኛና ከንቱ ትምህርት የሚያስተምሩትን አስተማሪዎች እንዲገሥጽ ለጢሞቴዎስ ትእዛዝ ይመክረዋል። በተጨማሪም ከክርስትያን ማኅበርና ከቤተ ክርስትያኒቱ ሽማግሌዎች ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖረው እንደሚገባ ይገልጻል። እንዲሁም በቤተ ክርስትያን ሥር ለሚረዱ መበለቶች ደንቦችንና መመሪያወችን ያወጣል። ኤጲስ ቆጶስና ድያቆን ለመሆን ስለሚያስፈልጉ መመዘኛዎች፥ በባሮችና በጌቶቻቸው መካከል ሊኖር ስለሚገባ ግንኙነትና ሀብታሞች በኅብረተሰቡ ውስጥ ስላለባቸው ኃላፊነት ያወሳል።
ይህ መልእክት የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች እውነተኛ የወንጌል አስተምሮንና አኗኗር እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ያሳያል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-2)
ስለ ቤተ ክርስቲያንና አገልጋዮችዋ (1፥3—3፥16)
ለጢሞቴዎስ ስለ አገልግሎቱ የተሰጠ ትምህርት (4፥1—6፥21)
ምዕራፍ
Currently Selected:
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ