2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1
1
ሰላምታ
1 #
የሐዋ. 18፥1። በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፥ በመላው አካይያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤
2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
ጳውሎስ ከብዙ ችግር በኋላ ለእግዚአብሔር ያቀረበው ምስጋና
3የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ። 4እኛ በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንድንችል፥ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል። 5የክርስቶስ ሥቃይ ስለ እኛ እንደ መብዛቱ፥ መጽናናታችንም በክርስቶስ በኩል ይበዛልናል። 6መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል እናንተም በትዕግሥት መታገስ በመቻላችሁ፥ ስለ መጽናናታችሁ ነው። 7ሥቃያችንን እንደ ተካፈላችሁ እንዲሁም መጽናናታችንን ደግሞ እንደምትካፈሉ እናውቃለንና፥ ተስፋችን ስለ እናንተ ጽኑ ነው።
8 #
1ቆሮ. 15፥32። ወንድሞች ሆይ! በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን ብታውቁት እንወዳለን፤ በሕይወታችን ተስፋ እስክመቁረጥ የሚያደርስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር። 9በእርግጥም፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ የሞት ፍርድ እንደተላለፈብን በውስጣችን ተሰምቶን ነበር። 10እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል። 11እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ ስትደግፉን፤ በብዙዎች ጸሎት ስለ ተሰጠን ስጦታ ብዙ ሰዎች ስለ እኛ ምስጋና ያቀርባሉ።
ጳውሎስ የጉዞውን ዕቅድ እንደ ለወጠ
12ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው። 13ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን የተለየ ነገር አንጽፍላችሁም፥ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። 14እኛን በከፊል እንደተረዳችሁን፥ በጌታ ቀን እናንተ በእኛ እንደምትመኩ ሁሉ እኛም በእናንተ እንመካለን።
15በዚህም እርግጠኛ ስለነበርኩ፥ በእጥፍ እንድትጠቀሙ አስቀድሜ ወደ እናንተ መምጣት ፈልጌ ነበር። 16#የሐዋ. 19፥21።ወደ መቄዶንያ ስሄድ በእናንተ በኩል አድርጌ ልጐበኛችሁና፥ ከመቄዶንያም በእናንተ በኩል ተመልሼ ወደ ይሁዳ እንድትልኩኝ ዐቅጄ ነበር። 17ይህን ማድረግ በመፈለጌ የተከፈለ ሐሳብ አሳይቼ ይሆን? ወይስ በእኔ ዘንድ “አዎን፥ አዎን” እና “አይደለም፥ አይደለም” ማለት እንዲሁ በሰብአዊ መመዘኛ በልማድ ይሆን? 18እግዚአብሔር የታመነ የሆነውን ያህል በእርግጥ እኛ ለእናንተ የምንናገረው ቃል “አዎን” እና “አይደለም” አይሆንም። 19#የሐዋ. 18፥5።ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ፥ እኔም፥ በመካከላችሁ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ “አዎን” እና “አይደለም” አልነበረም፤ ነገር ግን በእርሱ ሁልጊዜ “አዎን” ሆኖአል። 20እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ “አዎን” ማለት የእርሱ ነው፤ ስለዚህ ስለ እግዚአብሔር ክብር በእኛ ስለሚነገረው “አሜን” የምንለው እርሱ በኩል ነው። 21ነገር ግን በክርስቶስ ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፤ 22ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።
23እኔ ግን ራርቼላችሁ እንደገና ወደ ቆሮንቶስ እንዳልመጣሁ፥ በነፍሴ ላይ እግዚአብሔርን ለምስክርነት እጠራለሁ። 24እምነታችሁ ምክንያት አድርገን እናንተን ገዢዎች አይደለንም፤ ይልቁን በእምነታችሁ ጸንታችሁ ቆማችኋልና ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን።
Currently Selected:
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ