2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8
8
በልግስና ስለ መስጠት
1 #
ሮሜ 15፥26። ወንድሞች ሆይ! በመቄዶንያ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ 2በብዙ መከራ እየተፈተኑም ቢሆን ደስታቸው እጥፍ ድርብ ነበር፤ የድህነታቸው መጠን ቢበዛም ልግስናቸው የበዛ ነበር። 3እንደ ዐቅማቸው መጠን፥ ዐቅማቸውም የሚያልፍ እንኳን፥ ወደው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁ። 4ለቅዱሳን በሚደረገው አገልግሎት እነርሱም ተሳታፊ የመሆንን ጸጋ እንዲያገኙ እኛን አጥብቀው ይለምኑ ነበር፤ 5አስቀድመው ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፥ ከዚያም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለእኛም ሰጡ፥ እንጂ እኛ አስበንበት ያደረግነው አይደለም። 6ስለዚህም ቲቶ አስቀድሞ በእናንተ መካከል የጀመረውን ይህንን የቸርነት ከፍጻሜ እንዲያደርሰው ለምነነው ነበር። 7ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነት፥ በቃል፥ በእውቀት፥ በትጋት፥ እንዲሁም ለእኛ በፍቅራችሁ ልቃችሁ እንደተገኛችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ልቃችሁ ተገኙ።
8ይህንን የምለው ትእዛዝ እንደምሰጥ ሆኜ አይደለም፤ ነገር ግን ሌሎች ከሚያሳዩት ትጋት አንጻር የፍቅራችሁን እውነተኛነት ለመመርመር ነው። 9የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ። 10በዚህም ጉዳይ ምክሬን እለግሳችኋለሁ፤ ከአምና ጀምራችሁ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመስጠት በማሰብም ቀዳሚ ነበራችሁ፤ 11አሁንም እንዳዐቅማችሁ መጠን ለማድረግ ያላችሁ ጉጉት እንደ ሐሳባችሁ እንዲሆንላችሁ የጀመራችሁትን ከፍጻሜ አድርሱት። 12በጎ ፈቃድ ቢኖር፥ ባለው ባለው መጠን ተቀባይነት ይኖረዋል እንጂ የሌላውን አይጠበቅበትም።#ዘፀ. 16፥18። 13በናንተ ላይ ጫና ይብዛ ለሌሎች ደግሞ ዕረፍት ይሁን ማለቴ አይደለም፤ ነገር ግን ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው። 14የእነርሱ ትርፍ ደግሞ የእናንተን ጉድለት እንዲሞላ፥ በዚህም ያላችሁን እኩል እንዲሆን፥ የአሁኑ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጉድለት ይሙላ።
15 #
ዘፀ. 16፥18። “ብዙ ያከማቸ አላተረፈም፤
ጥቂትም ያከማቸ አላጎደለም።”
ተብሎ እንደተጻፈው።
ቲቶና ጓደኞቹ
16ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤ 17እርሱ ምክራችንን ብቻ አይደለም የተቀበለው፥ ከቀድሞው የበለጠ በመትጋት፥ ወዶ ወደ እናንተ ይመጣል። 18ከእርሱም ጋር ስለ ወንጌል ስብከት በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም እንልካለን፤ 19ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል። 20እኛም ስለምናገለግለው ስለዚህ የቸርነት ስጦታ ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን፤ 21#ምሳ. 3፥4።ምክንያቱም በጌታ ፊት ብቻ ያልሆነ፥ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን ስለምናስብ ነው። 22በብዙ ነገር ተፈትኖና በብዙ ጉዳዮች ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር ልከነዋል። አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከበፊት ይልቅ እጅግ ትጉህ ነው። 23ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፥ እናንተን ለማገልገል አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖር፥ የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው። 24እንግዲህ ስለ ፍቅራችሁና ስለ እናንተ ያለን ትምክህት ማረጋገጫ እንዲሆነን በአብያተ ክርስቲያናት ፊት ይህን ለእነርሱ በግልጽ አሳዩ።
Currently Selected:
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ