የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3

3
በመጨረሻዎቹ ቀኖች የሚሆነው የሰዎች ክፉ ጠባይ
1ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ቀኖች የሚያስጨንቁ ጊዜያት እንደሚመጡ ይህን እወቅ። 2ሰዎች እንዲህ ይሆናሉና፤ ራሳቸውን የሚወዱ፥ ገንዘብን ወዳጆች፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ 3ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ 4ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተወጠሩ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፥ 5የሃይማኖትን መልክ የያዙ ነገር ግን ኃይሉን የካዱ ሆነው ይገኛሉ፤ እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ራቅ። 6ከእነርሱም መካከል በየቤቱ እየተሽሎኮሎኩ በመግባት የኃጢአታቸው ሸክም የከበደባቸውንና በልዩ ልዩ ምኞትም ውስጥ የሚዋዠቁትን ደካማ ሴቶችን የሚያጠምዱ ይገኙባቸዋል። 7እንዲህ ያሉት ሴቶች ግን ሁልጊዜ እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ከቶ ሊደርሱ የማይችሉ ናቸው። 8#ዘፀ. 7፥11።ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው በእምነትም ረገድ ተፈትነው የወደቁ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ። 9ዳሩ ግን እነዚያ ሁለቱ ተቃዋሚዎች እንደሆኑት እንዲሁ የእነዚህም ሰዎች ሞኝነት ለሁሉም ሰው ስለሚገለጥ አይሳካላቸውም።
ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የሰጠው የመጨረሻ ምክር
10አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን ዓላማዬንም፥ እምነቴንም፥ ትዕግሥቴንም፥ ፍቅሬንም፥ መጽናቴንም፥ 11#የሐዋ. 13፥14-52፤ የሐዋ. 14፥1-7፤ የሐዋ. 14፥8-20።ስደቴንም፥ መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና የታገሥሁትን ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ። 12በእርግጥም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ለመኖር የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። 13ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አስመሳዮች እያታለሉና እየተታለሉ ከክፋት ወደ ባሰ ክፋት ይሄዳሉ። 14አንተ ግን በተማርህበትና በጽኑ ባመንኸበት ነገር ሳትናወጥ ኑር፤ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ 15እንዲሁም ከሕፃንነትህ አንሥቶ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ወደሚገኘው መዳን የሚመራህን ጥበብ ሊሰጡህ የሚያስችሉትን ቅዱስ መጻሕፍትን አውቀሃልና። 16ቅዱስ መጸሐፍ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሣሽነት የተገለጠ ነው፤ እንዲሁም ለማስተማርና ለመገሠጽ፥ ስሕተትንም ለማረም፥ ሰውንም በጽድቅ መንገድ ለማለማመድ ያገለግላል፤ 17በዚህም የእግዚአብሔር ሰው በችሎታው ፍጹም እንዲሆንና ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ይጠቅማል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ