ትንቢተ አሞጽ 2
2
1 #
ኢሳ. 15፥1—16፥14፤ 25፥10-12፤ ኤር. 48፥1-47፤ ሕዝ. 25፥8-11፤ ሶፎ. 2፥8-11። ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የኤዶምያስን ንጉሥ ዐፅም አመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎአልና ስለ ሦስት የሞዓብ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። 2በሞዓብ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የቂርዮትንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ መካከል ይሞታል፤ 3ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፥ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ፥” ይላል ጌታ።
በይሁዳ ላይ የተደረገ ፍርድ
4ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የጌታን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉአቸው ሐሰቶቻቸው አስተዋቸዋልና ስለ ሦስት የይሁዳ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። 5በይሁዳ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”
በእስራኤል ላይ የተደረገ ፍርድ
6ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጻድቁን ስለ ብር፥ ችግረኛውንም ስለ አንድ ጥንድ ጫማ ሸጠዋልና ስለ ሦስት የእስራኤል ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም። 7የድሆችን ራስ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ የትሑታንንም መንገድ ያጣምማሉ፤ ቅዱሱንም ስሜን ለማርከስ አባትና ልጅ ወደ አንዲት ሴት ይገባሉ፤ 8በመሠዊያውም ሁሉ አጠገብ ለመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ ይተኛሉ፤ በአምላካቸውም ቤት ውስጥ በካሣ የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ። 9#ዘዳ. 3፥8-11።“እኔ ግን ቁመቱ እንደ ዝግባ ቁመት፥ ብርታቱም እንደ ባሉጥ#2፥9 እንደ ዋርካ የሚመስል ዛፍ ነው። ዛፍ የነበረውን አሞራዊውን ከፊታቸው ደመሰስሁ፤ ፍሬውንም ከላዩ፥ ሥሩንም ከታቹ አጠፋሁ። 10እኔም ከግብጽም ምድር አወጣኋችሁ፥ የአሞራዊውንም ምድር እንድትወርሱ በምድረ በዳም አርባ ዓመት መራኋችሁ። 11#ዘኍ. 6፥1-8።ከወንድ ልጆቻችሁም ነቢያትን፥ ከጉልማሶቻችሁም ናዝራውያንን አስነሣሁ፤ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ይህ በእውነት እንደዚህ አይደለምን?” ይላል ጌታ። 12እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችሁ፤ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ፥ ብላችሁ አዘዛችሁ። 13“እነሆ፥ እህል የተሞላ ሠረገላ እንደሚያደቅቅ፥ እንዲሁም እኔ በመሬታችሁ ላይ አደቅቃችኋለሁ። 14ፈጣኑ ሯጭ መሸሽ ሳይችል ይጠፋል፥ ብርቱውም በብርታቱ አይበረታም፥ ኃያሉም ነፍሱን አያድንም፤ 15ቀስተኛውም አይቆምም፥ ፈጣኑም ሯጭ አያመልጥም፥ ፈረሰኛውም ነፍሱን አያድንም፤ 16በዚያ ቀን በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥” ይላል ጌታ።
Currently Selected:
ትንቢተ አሞጽ 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ